🛑 የኢድ ሰላት በቤታችን ሆነን እንዴት እንስገድ?
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
📌 ሰላተል-ዒድ የተወሰኑ ሊቃውንት ግዴታ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ሱንና ነው ብለዋል።
📌 የዒድ ሰላት ሱንናም ይሁን ግዴታ ከተቻለ ተሰባስቦ ካልተቻለም ለየብቻ መስገዱ ተገቢና አስፈላጊ እንዲሁም የዲን መገለጫ ነው።
📌 በመሰረቱ ዒድ የሚሰገደው ለመስገጃነት በተዘጋጀ ገላጣና ወጣ ባለ ቦታ ሲሆን እንደሁኔታዎች መስጂድ ውስጥም ይሰገዳል።
📌 በተለያዩ ምክንያቶች ሜዳ ሄዶ ወይም መስጂድ መስገድ ያልቻለ ሰው ቤቱ ውስጥ በጀመዓም ይሁን ለብቻው ሰላተል-ዒድን መስገድ እንደሚችል ኢማሙ-ሽሻፊዒይን ጨምሮ የተለያዩ የዲን ሊቃውንት ገልጸዋል።
የዒድ ሰላት ሁለት ረክዓ ብቻ ሲሆን አዛንም ይሁን ኢቃም እንዲሁም ከፊትም ይሁን ከኋላ የሚሰገድ ሱንና የለውም።
🔖አፈጻጸሙ እንደሚከተለው ነው:-
የተለመደው ውዱእና መሰል የሰላት ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ በልብ የዒድ ሰላት መሆኑን ካወቁና ለመስገድም ከወሰኑ (ከነየቱ) በኋላ ወደ ቂብላ በመዞር :- ሁለት እጆችን ወደ ጆሮ ትይዩ በማንሳት "አላሁ አክበር" ይባላል።
ከዛም ከቻሉና ከፈለጉ የመክፈቻ ዱዓእ ተደርጎ ከዛም በተከታታይ እጅን እያነሱና እየመለሱ ሰባት ጊዜ "አላሁ አክበር" ይባላል።በየተክቢሩ መሃል ዝም ማለትም፣
سبحان الله، والحمد لله، ولا إله إلا الله، والله أكبر.
اللهم صل وسلم على محمد وعلى آل محمد.
📌 "ሱብሓነላህ ወልሐምዱ ሊላህ ወላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር።
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ አሊ ሙሐመድ" ማለትም ይቻላል።
📌 ከዛ ፋቲሓና ሱረቱል አዕላ (ሰቢሕ ኢስመ ረቢከል-አዕላ) ወይም የቻሉትን ሱራህ ድምጽን ከፍ በማድረግ ይቀራል።
ሁለተኛው ረክዓ ላይ ከሱጁድ ሲነሱ ከሚባለው ተክቢር ውጪ ከመጀመሪያው ረክዓ ተክቢር ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ አምስት ጊዜ ተክቢር ይደረግና ፋቲሓ ከዛም ሱረቱል-ጟሺየህ ወይም የሚችሉት ሱራህ ይቀራል።
📌 በዚህ መልኩ ሰላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ቤታቸው ውስጥ የሚሰግዱ ሰዎችም ቢሆን ከቻሉ አጠር ያለ ኹጥባህ ከቻሉ በዐረብኛ ካልቻሉም በራስ ቋንቋ ይደረጋል።
📌 የኹጥባ ዋና አላማና ክፍል፣ አላህን ማመስገን፣ ነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ፣ የቻሉትን ቢያንስ አንድ አንቀጽ ቁርኣን መቅራትና ከወቅቱ ጋር ተያያዥ የሆነ አጭር ምክር መለገስ ነው።
📌 እነሆ በዘመነ-ኮሮና በዚህ መልኩ ሁሉም በየቤቱ መላ ቤተሰቡን በመሰብሰብ የዒድን ሰላት መስገድ ይችላል።
🛑 ቤት ውስጥ ከመስገድ ይልቅ ለሚችልና ለሚመቸው ሰው ግቢ ውስጥ አንጥፎ መስገድም ይቻላል።ይህ የተሻለና ተመራጭም ሊሆን ይችላል።
የሰላተል ዒድ ወቅቱ ልክ እንደ ሰላት አዱሓ ነው። ጸሐይ ወጥታ ከፍ ብላ ከታየችበት ወቅት ጀምሮ ለዙህር 20 ደቂቃ አካባቢ እስኪቀረው ድረስ ባለው ጊዜ መሃል ነው።
በጊዜ ፈጥኖ መስገዱ ተመራጭ ነው።
📌 ይህ በእንዲህ እንዳለ ለዒድ አዲስ ወይም ንጹህ ልብስ መልበስ፣ ገላ መታጠብ፣ ሽቶ መጠቀምና በዒድ መደሰት ተወዳጅና አጅርም የሚያስገኝ ተግባር ነው።
📌 ሰላተል-ዒድ ከመሰገዱ በፊት ዘካተል-ፊጥርን መስጠት ግዴታ ሲሆን ከዒድ 2 ቀን አስቀድሞ መስጠትም ይቻላል።
▪️አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን
▪️የመጣውንም በሽታ በቃህ ይበልልን
አሚን
ምንጭ:–ኡስታዝ አህመድ ሸይኽ አደም
@zizuman