🖍የ2012 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዕጣ ፈንታ ምን ይሁን የሚለው የፌደራሉ መንግሥት ውሳኔ
እየተጠበቀ ነው፡፡
አሀዱ ቲቪ ከአገር ዐቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንደሰማው፤ ፈተናው በተያዘው ዓመት ይሰጥ ወይስ ይተላለፍ የሚለው ውሳኔ እየጠበቀ ነው፡፡
እንደሥራ ኃላፊዎቹ መረጃ ውሳኔው በ15 ቀናት ውስጥ ይታወቃልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በግንቦት መጨረሻ ይሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ወይም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በተያዘው
የትምህርት ዓመትም የተለመደ ጊዜውን ጠብቆ እንዲሰጥ እቅድ ተይዞ ነበር፡፡
ይሁንና በዓለም ዐቀፉ የኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸውና የመማር ማስተማሩ ሒደት በመስተጓጎሉ መርሃ ግብሩን ጠብቆ መሔድ አልተቻለም፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን እንደቴሌግራም ባሉ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ማስተማር እንዲቀጥሉ ቢልም ስኬታማ ሆኖ አልቀጠለም፡፡ ከዚህም አልፎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰዎች መሰብሰብ መከልከልም ተማሪዎች ቢዘጋጁ እንኳን ፈተናው በምንአግባብቶ ይሰጣል የሚለውን ምላሽ አልባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተናዎችን በቴሌግራም ገፁ አውጥቶ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲፈትሹ እያደረገ ነው፡፡ ዘገባው የአሀዱ ቲቪ ነው።
🇪🇹 @zizuman