Abdur-Razzaq||Al-Habeshi


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


والسلام على من اتبع الهدى!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




شرح أصول اعتقاد أهل السنة والجماعة من الكتاب والسنة وإجماع الصحابة والتابعين ومن بعدهم

.اسم المؤلف: هبة الله بن الحسن بن منصور الطبري اللالكائي أبو القاسم
تحقيق
#عادل_عبدالله_آل_حمدان
#عقيدة_ومذاهب_وأديان


☞የአህሉ ሱናን ዐቂዳን በሰፊው መረዳት ለፈለገ

☞ተቅሪርና ረድን በሚገባ ያስቀመጠ ኪታብ

📚አል-ሐፊዝ ሂበቱሏህ አል'ላለካኢይ


«እውነተኛ ወንድም እና ጓደኛ የሚታወቀው በመከራና ጭንቅ ግዜ ነው። በምቾትና በሰላሙ ግዜ ሁሉም ጓደኛ ነው። መጥፎና ክፉ ጓደኛ ማለት በመከራ ግዜ ጓደኛውን የሚከዳ ነው።»
✨ኢብኑ ሒባን
📚 ረውደቱ'ል ዑቀላእ
https://t.me/abdurezaq27


ከመልካም ስነምግባር በላይ ሚዛንን የሚያከብድ ታላቅ ተግባር የለም። የመልካም ስነምግባር ባልተቤት ይህ ተግባሩ ፆምና ሰላትን አበርክቶ የሚያበዛን ሰው ምንዳን ያደርሰዋል።

صحيح الجامع الصغير      ح 5726
https://t.me/abdurezaq27




ياليتني كنت فردًا من صحابتهِ

‏أو خادمًا عنده من أصغر الخدمِ

‏تجود بالدمع عيني حين أذكره

‏أما الفؤاد فللحوض العظيم ظمِي

‏ﷺ ﷺ ﷺ


በውስጥህ የምትይዛቸው እንደ ቂም፣ ቁጣና ጥላቻ ያሉ ስሜቶች አንተ ጠጥተሃቸው ሌላ ሰው እንዲሞት የምትጠብቅባቸው መርዞች ናቸው።


የስልጣኔን፣ የእውቀትንና የስነምግባርን ልህቀት አዋህዶ ወደ ተሃድሶ ሊመራን የሚችል ብቸኛው የምድራችን መፍትሄ ኢስላም ነው።


"የሒጃብ ቀን" ወይስ "የፈሳድ ቀን"?!

ኢስላም ራሱን የቻሉ ህልውናዎች ያሉት መሰረቱ የፀና በየግዜያቱ ልማድና ዘዬ በተከታዮቹ ከፍታና ዝቅታ ሙቀትና ቅሬታ የሚቀያየር እምነት አይደለም። መሰረታዊ ነጥቦቹን በየግዜው ብቅ ከሚሉ የከሀዲያን በቀል ተፅዕኖዎች ለመሸሽ በሚል ፈሊጥና ከዘመኑ ጋር እንራመድን ባዘለ ሙግት ፅኑ እሳቤው የሚገፈፍና በሸውራራ ምልከታና በዝንባሌዎች ማዕቀፍ የሚኮላሽ አይሆንም።

እርግጥ ነው ዘመናዊነትን ከኢስላም ጋር በማይጋጩ ነገሮች አጣጥመን ልንጠቀምበት ከዘመኑ ጋር ልንራመድ ህይወታችንን ልናቀልበትና ልናቀናበት ይገባል። ነገር ግን ኢስላምን ዘመናዊ እናድርገው ብለን ወደ ገደል የምንጎትተው እምነት ሊሆን በፍፁም አይችልም። አምላካችን አሏህ ይህን እምነት የደነገገውና የሰዎች መመሪያ ያደረገው እስከ ምፅዐት ቀን እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዘመናቶች በተሻገሩ ቁጥር ኢስላምን በታወረ ልቦናችን የምንዘምትበት በአጠረ እውቀታችን የምንጠራራበት እምነት አይደለም። ፋይሉ ከ1400 አመታት በፊት ተዘግቷል።

በአንፃሩ የምዕራባዊያን ተፅዕኖ ያስበረገጋቸው በኢስላም ቀና ማለት ያቃታቸው በስሜት አለንጋ የተገረፉ ስብዕናዎች ኢስላምን እናዘምነው በሚል ወይም ቅቡልነቱን እናግነነው በሚል ሸውራራ እይታ ማህበረሰቡን ከትክክለኛው የኢስላም እሳቤ ወደ ወረደው አዘቅት እያወረዱት የቆመበትን ምንጣፍ እየጎተቱን ይገኛሉ። እውነት ነው አላህ እንዲህ ማለቱ ፦

  "አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሀይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈፅሞ አይወዱም " አል-በቀራ 120

እነሆ ሒጃብና ሴቷ ላይ አንዳች ሀሳብ ልሰንዝር። ዘመኑ ተለዋዋጭነቱ ከብርሃን ፍጥነት በላይ በሆነበት ከዛሬ ነገ እየከነፈ ሙስሊሟ ሴት እየተንሸራተተች የት ነው ያለችው?  አንዱን ሲያስጥሏት እየወረደች አንዱን እያነሳች በመጨረሻም የእነሱን መንገድ በምልአተ ልቦናዋ ኮቴ በኮቴ እየተከተለች ትጓዝ ይዛለች። መታገል የመጀመሪያው ፈተና ላይ መሆኑን አላወቀችም። ድንበርህን አሳልፈህ ከሰጠህ ቡኃላ በሜዳህ ለሚጫወቱ አካላት መጫወቻ ትሆናለህ። አመቱን ሙሉ የሒጃብ ቀን ብለን ብናከብር የሒጃብን ልቅና በዚህ መንገድ ልናስጠብቀው በፍፁም አንችልም። ይባስ ብሎም ይህ አካሄድ ሴቶችን ከትክክለኛው የሒጃብ መፍሁምና ጭብጥ እያራቃቸው መጥቷል። ለዚህም ነው በየቦታው የቻይና ሱሪና ጠባብ ቀሚስ የታጠቁ ሙልጭልጭ ያለ ሂጃብ የለበሱ በጥቅሉ ማንነታቸው ግራ የገባቸው ሴቶች እንደ አሸን የፈሉት። ሀይ ባይ አጥተው ነውራችን የሆኑት። ግዜው በገፋ ቁጥር ነገሩም እየከፋ አበረታችና አጨብጫቢው እየፋፋ ሴቶችንም ለሐራም ማደኑም እየገፋ መጥቷል። 

ፀጉራቸውን እንኳን በተገቢው መልኩ ያልሸፈኑ ብጥስጣሽ ጨርቆችን ከአናታቸው ላይ ጣል ያደረጉ በሰፋፊ ልብሶች መሸፈን ያለበት አካላቸው በጠባብና ባለ ወገብ ማሰሪያ ቀሚሶች ያሰሩና አካላቸውን የማይሰትሩ ቀሚሶች ያጠለቁ ከዚህ ሲከፋም ጠባብ ሱሪዎች ታጥቀው ብቅ የሚሉ እህቶችን ሰብስቦ "የሒጃብ ቀን" እያሉ ማጃጃል ትልቅ ውርደት ነው። የንፁህ ሴት ልጅ ክብርና መገለጫ የሆነውን ጌታዋን የምታመልክበትን ዒባዳ የሒጃብ  fashion show በሚል ቀልድና ሞኝነት በወንዶች መንጋ መሀል ሲያመላልሷት  እንዲሁም ቧልትና ዛዛታ በበዛበት መድረክ ላይ ወንድና ሴት ፍጥረቶች ያለ ግርዶሽ አፋጠው በሜክአፕ፣ በሊፒስቲክና .....የተበከለ ፊት በቅጡ ያልተሰተረ ማንነት የተከማቸበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን ተብሎ ይሰየማል? በነሺዳ ስም የሚቅለሰለሱ ፓንክ ቁርጥ ሙንሺዶች የሚጣዱበት አብዛኞዎቹ ታዳሚያን ትክክለኛውን የሒጃብ መስፈርት ያላሟላ ሒጃብ ለብሰው የሚታደሙበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን መሰናዶ ሊሆን ይችላል? በዚህ የፈተና ነፋስ በከፍተኛ ፍጥነት በሚነፍስበት ዘመን እሳትና ጭድን አቀራርቦ ደህና ምክር እንኳን መስጠት ከባድ መፍሰዳ ያስከትላል በሚባልበት እውነታ ከዛዛታው መሀል  ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? ምን አልባት ፕሮግራሙን ኢስላማዊ ለማስመሰል አንዲት ሙሐደራ ቢጤ ነገር ጣል ሊያደርጉባት ይቻል ይሆናል ይህም መሰረቱ በወደቀ ቤት ላይ ሚስማር እንደመምታት ነው።

እውነታውን ስንመለከት "ዓለም አቀፍ የሂጃብ ቀን" ተብሎ በፌብራሪ 1 የሚከበረውን በዓል አንዲት በአሜሪካ የምትኖር ትውልዷ ባንግላዲሽ ዜግነቷ አሜሪካዊ የሆነች በ 11 አመቷ ወደ ሀገረ አሜሪካ ከቤተሰቦቿ ጋር ተሰዳ የምትኖር እንስት በሂጃቧ  ምክንያት በሚደርስባት ጫና ያስጀመረችው የሚዲያ ዘመቻ መሆኑ ነው። ማንም ቢሆን መልካም አላማን አንግቦ አንዳች ነገርን ይዞ በዲን ስም ከመነሳቱ በፊት በሸሪዓ ሚዛን ተለክቶና ተገምግሞ የኢስላም ሊቃውንቶችን ትክክለኛ ይሁኝታ ቁርኣንና ሐዲሥን አስደግፎ መስለሓና መፍሰዳው ታይቶ መሆን አለበት። የቢድዓ ጉዳይ ከሆነ ግን ምንም አይነት የቅቡልነት መንገድ አይኖረውም።

ሒጃብ አላህ ለሴቶች የደነገገው ጥበባዊና ፍትሓዊ የሆነ ሸሪዓዊ ልባስ ነው። አንዲት ሴት የጥብቅነትና የጨዋነት ምልክት ነው። በዚህ ርዕስ ላይ ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ የኢስላም ልሂቃንና ሰባኪያን ሴቶችን ስለ ትክክለኛው ሒጃብ ሊያስተምሩ የመዳኛ መንገድ መሆኑን ሊጠቁሙ የክብሯ፣ የሀሴቷና የልቅናዋ ሰበብ መሆኑን ሊያስገነዝቧት ይገባል።

ነገር ግን አመት ጠብቆ የሒጃብ ቀን ብሎ ማክበርና ከዚህም የባሰው ደግሞ የዛን እለት ብቻ ሒጃብ የሚለበስበትና የተለያዩ እምነት ተከታዮችም እንደ ተራ ፌስቲቫል ሒጃብ ያሉትን ጨርቅ ጣል አድርገው ሲቀልዱ በተነሱት ፎቶ ሶሻል ሚዲያዎችን ሲያጨናንቁ ማየት ከባድ የሆነ ቢድዓና በውስጡም ተዘርዝረው የማያልቁ መፍሰዳዎችን ያካተተ ነው። ይህን ተግባር በፅኑ የሚኮኑንበት ሌላው ምክንያት በተለያዩ ቀናት እንዳሻቸው ክብረ በዓል ከሚያሰናዱ ከሀዲያን ጋር መመሳሰል መንገዳቸውንም መከተል ስላለበት ነው። ኢስላምም ከተደነገጉለት በዓላት ውጪ የተለየ ክብር በዓላትን በየትኛውም መልኩ አያስተናግድም።

ይህን መሰል ነገሮችን የሚያከብሩ ሰዎች በብዛት መስለሓ አለው በሚል ሙግት መሆኑ እርግጥ ነው። ይህን ሲሉ መሰለሓና መፍሰዳን ሚዛን ላይ አስቀምጦ ለመገምገም የሚያስችል የሸሪዓ እውቀትና የቀደመ ኢስላማዊ ልቀትና ምጥቀት ላይ ያሉ ሰዎች አለመሆናቸው ደግሞ ያስተዛዝባል። መፍሰዳና መስለሓን በሸሪዓ ምልከታ፣ በረቀቀ ግምገማና እይታ አላህን ፈሪ በሆነ ልቦና ተመልክተው ብይን መስጠት ያለባቸው በዘርፉ የተካኑ የኢስላም ልሂቃን ብቻ ናቸው። ከዚህ ውጪ በዲን ስም ቢዝነሱን እያጧጧፈ መስለሓ አለው ለሚልሽ ባተሌ ጆሮ አትስጪ ማመዛዘን የሚችለውን ዐቅልሽ አታከራይው ይልቁንም ለዲንሽና ለክብርሽ ዋጋ ስጪ። የመፍሰዳው ብዛት  አለች የሚሏትን ጭላንጭል መስለሓ ላይ ቢቆለል አፍነው ይገሏት ነበር። ይህ የነሺዳና ዳንኪራ ጭብጨባ፣ በወንዶች መሀል በፋሺን ሾው ስም ያለ ዕፍረት የሒጃብን መስፈርት በማያሟላ በተጋጌጠና በተቆራረጠ የጨርቅ ቅጥልጣይ ልብስ መመላለስና መሰባበር፣ ኢኽቲላጥና ዛዛታ ሌሎችም ሙንከራቶች እውነት ወደ አላህ የሚያቃርበን ዒባዳ ነውን?  በፍፁም!!!

#yes_to_hijab_no_to_hijab_day
2022 feb 21

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/abdurezaq27


በብጫቂና በቁንጥርጣሪ ጨርቅ ራሷን ሸፍናና የተጣበበ ባለ ወገብ ማሰሪያ ቀሚስ አድርጋ የሒጃብ ቀን እያለች የምትጋጋጥ ምስኪና ታሳዝነኛለች።


⇡⇡⇡⇡⇧
☞ድንቅ በሆነ ተሕቂቅ የተዘጋጀ ከታዋቂው ቡሉጉል መራም ኪታብ ኪታቡ ሲያምን (የፆም ህግጋትን) የተነተነ ልዩ ጥንቅር።

🎙 ዶክተር ዐብዱልዓዚዝ አር'ረይስ
📚አንብቡት ✨






الطب النبوي - ابن القيم .pdf
13.1Мб
🍯ነብያዊ ህክምና ኢብኑል ቀይዪም




قصيدة من أعظم القصائد
እንደዚህም መስዕዋትነት አለ። እንደዚህም አይነት ርዕዮትና ተስፋ ተሀድሶም ይኖራል. ....

በአማርኛ መልሼ እገጥመው ነበር። መልዕክቱን እንዳላኮስሰው ሰጋሁና ተውኩት ከነግርማ ሞገሱ .......


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ፅናት የሚገኘው ብዙ ምክር በመስማት ሳይሆን፣ የሰሙትን በመተግበር ብቻ ነው።


"ሰዎች በሞት ላይ ያላቸውን እርግጠኝነት  የሚመስል ጥርጣሬን አይቼ አላውቅም። ልክ መሞታቸውን እንደሚጠራጠሩ አይነት ሆነው ለሞታቸው አይዘጋጁለትም።"

ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዐዚዝ

[الجامع لأحكام القرآن— القرطبي]

https://t.me/abdurezaq27



Показано 20 последних публикаций.