ትምህርት ቤቶችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንዲዘጉ የተወሰነው ውሳኔ የፊታችን ሰኞ ያበቃል።
ውሳኔው እንደሚራዘም የብዙዎች ግምት ቢሆንም መንግስት እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ያለው ነገር የለም።
የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ ነበር ኢትዮጵያ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ለ15 ቀናት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተነገረው።
ይህ ቀን የፊታችን ሰኞ የሚያበቃ ሲሆን የቫይረሱ ስርጭት እና ያስከተለው ስጋት እየጨመረ በመሆኑ ውሳኔው እንደሚራዘም ይጠበቃል።
ብዙዎች ይህ ውሳኔ እንደሚራዘም የሚጠብቁ ሲሆን ለምን ያህል ጊዜ ነው የሚራዘመው የሚለው ግን አሁንም አልታወቀም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት አቋም ምንድን ነው የሚለውን ለማጣራት የተለያዩ ተቋማትን ጠይቋል።
ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ኮማንድ ፖስት የተቋቋመ በመሆኑ መረጃዎችም ጥብቅ መሆናቸውን ተረድተናል።
ትምህርት ሚኒስቴር፣የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና ሌሎች የጤና ተቋማት መረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ሁሉም ተቋማት የኮሮና ቫይረስ ብሔራዊ ኮማንድ ፖስት ውሳኔን እየጠበቁ መሆኑን ነግረውናል።
መንግስት ዛሬ ከሰዓት ወይንም ነገ የቫይረሱን ስርጭት አስመልክቶ በቀጣይ ስለሚወሰዱ አጠቃላይ እርምጃዎች መግለጫ ሊሰጥ እንደሚችል ሰምተናል።
(ኢትዮ ኤፍ ኤም)
መጋቢት 18ቀን 2012 ዓ.ም
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot