የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ7,400 በላይ አልጋዎች ያሏቸው ሁለት ግቢዎቹን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ መከላከል ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ለለይቶ ሕክምና ምቹ እንደሆኑ ያመነባቸውን የዘንዘልማ እና ይባብ ግቢዎች 925 ክፍሎች ለዚሁ ተግባር ዝግጁ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡
ዶክተር ፍሬው እንዳሉት በእነዚህ ክፍሎች 7 ሺህ 400 ተማሪዎች የሚስተናገዱባቸው የየራሳቸው አልጋዎችና ፍራሾች፣ የጋራ የንጽሕና መጠበቂያ ክፍሎች የተሟሉ ናቸው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ሁኔታዎችን እያዬ ካሉት ሰባት (7) ግቢዎች ሌሎችንም ለመሠል ተግባር ሊያመቻች እንደሚችልም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡
(አብመድ)