Adanech abiebie


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


ኢትዮጵያ ተሸንፋ አታውቅም ማሸነፍ በደማችን ያለ እውነት ነው! ሁሌም አሸናፊዎች ነን!
Ethiopia is defeated and you don't know how to win in our blood without truth! we are always winners!
🇪🇹🇪🇹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ🇪🇹🇪🇹
God bless Ethiopia

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


የትንሳኤ በዓልን የኮሪደር ልማት ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ፣ኮንትራክተሮች እንዲሁም አማካሪዎች ጋር በዓልን በስራ ቦታ አክብረናል።

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ ለማድረግ ቀን ከሌት ለምታደርጉት ትጋት እያመሰገንኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

Ayyaana du'aa ka'uu;hojjettoota misooma koriidarii irratti bobba'an waliin, koontiraaktaroota akkasumas gorsitoota waliin ayyaanicha bakka hojiitti kabajneerra.

Finfinnee akkuma maqaa ishee abaaboo miidhagduu taasisuuf halkanii fi guyyaa dadhabbii taasistaniif isin galateeffataa ayyanichi kan nagaa ,jaalalaa,gammachuu fi waliif yaaduu akka isiniif ta'un hawwa.

Ayyaana Gaarii!

Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Haa Eebbisu!

@adanechabiebie




ዛሬ 446 ቤቶችን ገንብተን ለአቅመ ደካሞች፣ ለሀገር ባለዉለታዎች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ የከተማችን ነዋሪዎች አስተላልፈናል።

በከተማችን ከህዝብ በምንሰበስበው ገቢ ከምናከናውናቸው ታላላቅ የልማት ስራዎች ጎን ለጎን በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶችን እና የተለያዩ ተቋማትን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን ኑሮ የሚያሻሽሉ ሰዉ ተኮር ስራዎችን እየሰራን የምንገኝ ሲሆን፣ በተለይ የተገፉ እና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት እድል ያጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እምባ ሲታበስ ማየት ደስታን ይሰጠናል።

ዛሬ ካስረከብናቸዉ 446 ቤቶች ዉስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ጎላጎል አካባቢ የሚገኙትን ቤቶች ግንባታ ያገዙን የገቢዎች ሚኒስቴርን፣ የጉምሩክ ኮሚሽንን እና የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን እንዲሁም ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶች እና ተቋማትን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

Har'a manneen 446 ijaarree harka qalleeyyiif, namoota oolmaa biyyarraa qabaniif fi jiraattota keenya rakkoolee hawaasaa garaagaraatiif saaxilamaniif dabarsineerra.

Magaalaa keenyatti galii uummata irraa sassaabnuun hojiiwwaan misooma rawwaannuun cinaatti abbootii qabeenyaa hayyamamoo fi dhaabbilee adda addaa qindeessuun hojiiwwan namarratti xiyyeeffatan, jireenya harka qalleeyyii fooyyessan hojjechuu irratti kan argamnu yemmuu ta'uu, keessattuu kutaa hawaasaa dhiibamanii fi carraa fayyadama haqa qabeessaa dhaban yeroo imimmaan irraa haqamu arguun gammachuu nuuf keena.

Manneen har'a eebbisne 446 keessaa ijaarsa manneen kutaa magaalaa Boolee nannawa golaagolitti argamanii kan nu gargaaran Ministeera Galiiwwanii, Komishinii Gumruukaa fi Abbaa Taayitaa bishaanii fi dhangala'oo magaalaa Finfinnee akkasumas tola ooltota abbootii qabeenyaa fi dhaabbilee biroos maqaa koo fi jiraattota keenyaatiin galateeffachuun barbaada.

Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Yaa Eebbisu

@adanechabiebie






በቀን 30 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::

ከለዉጡ ወዲህ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምሮ የመጨረስ አንዱ ማሳያ የሆነዉ ይህ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የከተማችንን የፍሳሽ ማጣራት አቅም ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት በቀን 48 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ወደ በቀን233 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ከፍ ማድረግ አስችሎናል::
ይህ የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማጣሪያ ፣ስርዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ።

ለአንድ ከተማ ወሳኝ ከሆኑ መሰረተ ልማቶች መካከል የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓትን ማዘመን ትልቅ ስራ ሲሆን ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ከመፍጠር አኳያ ያለው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡በመሆኑም ይህ የፍሳሽ ማጣሪያ ስራ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓታችንን የሚያዘምን፣ የከተማችን ነዋሪዎችን እና በአጎራባች አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎት የረዥም ጊዜ ቅሬታን ምላሽ የሚሰጥ ፣ከተማችንን ከብክለት የጸዳች፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ እዉንየሚያደርግ ነዉ።

ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ያደረጋችሁ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኮንትራክተርና አማካሪ ድርጅት ክፍለከተማው ከምንም በላይ በፈቃደኝነት ለልማት ከቦታው የተነሱ አርሶ አደሮችን በነዋሪው እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ



Показано 7 последних публикаций.