#በኤፍራታ_በጎል
በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ተወለደ ጌታ/2/
ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሳያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ/2/
አዝ
________________
ዓለምን በእፍኙ ጨብጦ አዳኙ
በከብቶቹ ግርግም አቀፈችው ማርያም/2/
መጡ ሰብዐ ሠገል ሊሠግዱ ለልዑል
ዕጣን ለክህነቱ ወርቁን ለ
መንግስቱ/2/
አዝ________________
የመቅደሡ ናፍቆት በክንዱ መዘርጋት
ቤንሆር ተዋረደ መሲህ ተወለደ /2/
የጥሉ መንጦላይት ለይቶን ከገነት
ሕይወት
ን አገኘን ልደቱ አስታረቀን/2/
አዝ________________
ምድር ተፈወሠች አዳኟን ስላየች
ሠውና መላዕክት ተቀኙ በአንድነት ዘመሩ በአንድነት
በሠላም አለቃ ኩ
ነኔው ሊያበቃ
ስቃይ ሊመነገል ወለደችው ድንግል/2/
አዝ________________
ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሣያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ/2/
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
💚
@Addis_Mezmure 💚
💛
@Addis_Mezmure 💛
❤️
@Addis_Mezmure ❤️