በአሜሪካ የሉዚያና ግዛት ነዋሪ የሆነው Darren James ማታ ሲተኛ የሚያውቀው በባንክ አካውንቱ ውስጥ ያለው ተቀማጭ ገንዘብ መቶምናምን ዶላር እንደሆነ ነበር ።
ልክ ሲነጋ ግን ነገሮች ተለዋወጡ ፡
ከባለቤቱና ከሁለት ልጆቹ ጋር የሚያገኛትን ደሞዝ አብቃቅቶ የሚኖረው ዳረን በአንድ ሌሊት. .. ሀምሳ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በማስመዝገብ ፡ የአለም 25 ኛው ቢሊየነር ሰው ሆነ ።
ነገሮቹን ሁሉ የለወጠው ከባንክ የተላከለት ቴክስት ነበር ። እና ከባለቤቱ ጋር ሆነው ቴክስቱን ደጋግመው አነበቡት ፡ የተላከው ቴክስት ስካም ወይም ፌክ እንዳልሆነ በደንብ አረጋገጡ ፡ እውነታው አንድ የማያውቁት ሰው በነሱ አካውንት ላይ ሀምሳ ቢሊየን ዶላር አስገብቶላቸዋል ።
➡️በህይወቴ ዘጠኝ ዜሮዎች ያሉት ይቅርና ፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብርም ኖሮኝ አያውቅም ፡ እና አንድ ዘመድ ይህን ብር እንዳስገባልኝ አሰብኩ ፡ ሆኖም ያን ያህል ብር ያለው ሰው ፈፅሞ አላውቅምና ፡ ጉዳዩን ለባንክ ማሳወቅና የተሳሳተ ብር እንደተላከልኝ ለመናገር ወሰንኩ ይላል ።
ሆኖም የዳረን ባለቤት ይህን ሀሳብ ተቃውማ ምን አስቸኮለህ የተሳሳተ ከሆነ ራሳቸው ይደውሉልናል ተረጋጋ አለችው ።
ዳረን በሀሳቧ አልተስማማም ፡ የገባለትን ገንዘብ ወደሌላ አካውንት ለማዛወርም አልሞከረም እና ወዲያው ወደባንክ ሄደ ፡ እውነቱን ነግሯቸው ለሱ የተላከም ከሆነ ለማወቅ ካልሆነም ፡ ለቢሊየነሩ ሰው መልሶ ምስጋና እና ገንዘቡን ለመለሰበት አንድ አስር ሚሊየን ብር ጉርሻ ሊሰጡት እንደሚችሉ እያሰበ ባንክ ደርሶ
✅ሀምሳ ቢሊየን ብር ወደባንክ አካውንቴ ገብቷል አላቸው ፡ ማናጀሩ ቢሮ ጠርቶ አናገረው ። እና ሁኔታውን እንደሚያጣሩ ነግረውት ከባንኩ ወጥቶ ጥቂት እርምጃ እንደተራመደ ፡ ሌላ ቴክስት በስልኩ ገባ ፡ ቴክስቱን አነበበው ፡ አሁን ያሎት ቀሪ ሂሳብ ( ጥቂት ) መቶ ብር ብቻ ነው ይላል ቴክስቱ ።
በድንገት በአካውንቱ ገብቶ ከአለም ቢሊየነሮች ተርታ በ25 ኛ ደረጃ ያስቀመጠው ገንዘብ ፡ ከመቅፅበት ከአካውንቱ ወጥቶ ተሰወረ ።
አስገራሚው ነገር ባንኩ ይህን በተመለከተ ምንም አይነት መግለጫም ሆነ ትክክለኛው የገንዘቡ ባለቤት በተመለከተ ምንም አልተናገረም ፡ ይህን በተመለከተ አስተያየት የሰጡ ሰወች ገንዘቡ ከክሪፕቶ ወይም ከህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ተናግረዋል ።
ለሰአታት ቢሊየነር ለሆነው ዳረን ጀምስም ጉርሻ ይቅርና ምስጋናም አልተሰጠውም ይላል ስናነብ አግኝተነው ያስገረመን ዘገባ ።