🟢በሰዓት ከ 320 ኪሎ ሜትር በላይ የሚበሩ "bullet train" የሚባሉ ባቡሮች ያሉት እዛ ነው! ጃፓኖች ጋር ባቡር ውስጥ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማውራት ሳይቀር እንደ ነውር ይቆጠራል! ጃፓን ውስጥ በምትስተናገድበት ሆቴል ወይም ሬስቶራንት ውስጥ "Tip "ለአስተናጋጅ መስጠት ነውር ነው። ለአንድ አስተናጋጅ "Tip"አስቀምጠህለት ብትሄድ እየሮጠ ተከትሎህ ይመልስልሃል! "ለምን?" ስትለው "...አንተን ማስተናገድ እና መንከባከብ ግዴታችን ነው፣ ስራችን ነው! ለዚህ ስራችን ደግሞ ደሞዝ ይከፈለናል! ስለዚህ ተጨማሪ ብር በ "Tip" መልክ መስጠት አይጠበቅብህም! ..." ይሉሃል!
🚢🚢🚢
✅እጅግ ሰው አክባሪ እና ትሁት ከመሆናቸው የተነሳ ማንኛውንም እቃ፣ ምግብ ወይም መጠጥ በሁለት እጃቸው እንጂ በአንድ እጃቸው በፍፁም አይቀበሉህም! እሱንም ከወገባቸው ጎንበስ ብለው ነው።የሚገርመው ቤት ውስጥ ውጪ የዋልክበትን ጫማ አድርጎ መግባት ነውር ነው። አይደለም ቤትህ አንዳንድ ምግብ ቤቶች ሳይቀር ተስተናጋጆች ጫማቸውን አድርገው እንዲገቡ አይፈቀድም! በር ላይ ሸበጥ/ሲሊፐር ስለሚቀመጥልህ ቀይረህ መግባት ግድ ነው።ከዓለማችን ብቁ ተማሪዎች ተርታ ይሰለፋሉ። 100% የሚሆነው የሃገሪቷ ወጣቷ በሚገባ ፊደል የቆጠረ እና ቀጥቅጦ የተማረ ነው።
🚢🚢🚢
✅ህፃናት ሃገራቸውን እንዲወዱ፣ ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰባቸውን እንዲያከብሩ ተድርገው ያድጋሉ! የጃፓን ትምህርት ቤቶች ውስጥ የፅዳት ሰራተኛ አይቀጠርም! "ለምን?" ካልከኝ ከትምህርት በኃላ ሁሉም መምህራን እና ተማሪዎች ለ 15 ደቂቃ ልብሳቸውን ቀይረው ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም ክፍሎች(መፀዳጃ ቤትን ጨምሮ) እኩል ያፀዳሉ! የጃፓን ተማሪዎች በሂሳብ፣ ፊዚክስ እና ቋንቋ መጎበዝ ግዴታቸው ነው። ተማሪዎች የፍቅር ግንኙነት መመስረት አይችሉም! እሱ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤት ውስጥ መሳሳምም ሆነ መተቃቀፍ አይቻልም፣ ያስቀጣል፣ አለፍ ካለም ያስባርራል!