ቤንጃሚን ፍራንክሊን በወጣትነቱ ተከራካሪና እዉነቱን በግድ ለማሳመን የሚጥር ሰዉ ነበር።
ታዲያ አንድ ቀን ከጓደኞቹ ጋር ሲከራከር አንድ ፌዘኛ ጓደኛዉ እንዲህ አለዉ።
"ቤን አስቸጋሪ ሰዉ እኮ ነህ። የሚቃወምህን ሰዉ በነገር ጥፊ ታጮለዋለህ። ጥረትህ የሰዎችን እምነት ለመቀየር ስለሆነ ማንም ሊሰማህ አይፈልግም። እንደዉም እንዳየሁት ከሆነ ጓደኞችህ ተዝናንተው የሚጫወቱት አንተ ሳትኖር ነዉ። እርግጥ ነዉ ብዙ ታዉቃለህ። ስለዚህም አንተን መምከር ያስቸግራል። እንዲያዉም ማንም ሰዉ ምንም ሊያስረዳህ አይሞክርም ምክንያቱም ሀይለኛ ክርክር እንደሚገጥመዉ አስቀድሞ ያዉቃል። ስለዚህም ከዚህ በኋላ ባለህ እወቀት ላይ የምትጨምር አይመስለኝም። የምታወቀዉ ደግሞ ትንሽ ነዉ።" ነበር ያለዉ
ቤንጃሚን አዋቂና ትልቅ ሰዉ ስለነበር ይህን የጓደኛዉን ትችት እንደ ዉርደት ከመቁጠር ይልቅ በፀጋ ተቀበለዉ።
"ከዚያ ቀን በኋላ " ይላል ቤንጃሚን የጓደኛዉ ንግግር እንዴት እንደቀየረዉ ሲናገር "የሰዎችን ሀሳብ ከመቃወምና እንደመጣልኝ በቃላት ከመዘርጠጥ ተቆጠብኩ። እረግጠኝነትን የሚገልጹ ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ 'እንደሚመስለኝ'፣' እንደምረዳዉ'፣ 'ሳስበዉ' የመሳሰሉ ቃላትን መጠቀም አዘወተርኩ። እንዲያዉም ከዚያ ጊዜ በኋላ ለ50አመታት ምንም አይነት ግትርነትን የሚገልጹ ቃላትን ተጠቅሜ አላዉቅም።" ነበር ያለዉ።
እኔ ብቻነኝ አዋቂ፣ እኔ ብቻ ነኝ ትክከል፣ እኔ ብቻ ነኝ ተናገሪ ብለዉ የሚያስቡ ሰዎች ካላቸዉ እዉቀት በላይ አይጨምሩም።
ስለዚህም በሀሳብ ልዕልና እንመን!!!!!