እየተስተዋለ ወገን !!
ይህ ፎቶ ዘወትር ሳልፍ የምመለከተው የመሪ 40/60 ኮንዶሚኒየም ባልኮኒ (በረንዳ) ላይ አንድ ተብሎ የተጀመረ በሮቶ ውሃ ማከማቸት እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ያለኝን ስጋት ለማፍራት ያነሳሁት ነው፡፡
እንደሚታወቀው የውሃ ችግራችን የማያሳስበን ነገር የለም። ለችግሩ የሚሰጠው መፍትሄ ግን ሌላ ችግር መፍጠር የለበትም።
ኗሪዎቹ ውሃ እያስቀመጡ ያሉት ለሰው መቆሚያ ተብሎ በተሰራ ተንጠልጣይ ወለል cantilever ( ምዝውጥ) ላይ ነው። ይህ ቦታ የመዋቅር ዲዛይኑ ሲሰራ ለሰው መንቀሳቀሻና መጠቀሚያ እንጂ እንዲህ በአንድ ቦታ የተከመረን የውሃ ክብደት ለመሸከም አይደለም።
ከርቀት እንደተመለከትኩት ብዙዎች ያስቀመጡት የውሃ ጋን ( water tanker) ከ 1000 ሊትር የሚያንስ አይመስልም ይህም ባልቀነጨረ መካከለኛ ሰው ክብደት ሲሰላ የ 15ሰው ያውም በትንሽ ቦታ ተደራርቦ ነው እኩሌታ ነው።
የአንዳንዶቹም ለቦታው ተመጥኖ የተሰራ መጠነ ክቡ (Diameter) አነስ ብሎ ቁመቱ ከፍ ብሎ የተሰራ ነው፡፡ ይህም በትንሽ ቦታ ላይ ከፍተኛ እፍግታ (pressure) በመፍጠር ስላቡ ሊቀነጠስና አደጋ ሊያስከትል ይችላል።
ክፉ ነገር ከማየታችን በፊት እባካችሁ በእንደዚህ አይነት ህንጻዎች ላይ የምትኖሩ ወገኖቻችን ክፉ ነገር ከመፈጠሩ በፊት ለውሃ ችግራችሁ የተሻለ መፍትሄ ፍጠሩ። ለምሳሌ ሁሉም ሰው የየራሱ ታንከር የሚሰቅልበትን ገንዘብ አዋጥቶ ትላልቅ ታንከሮች መሬት ላይ አስቀምጦ በ ፓምፕ ሽቅብ እየላከ ከላይ ወደ ታችም ለእያንዳንዱ አባወራ በእኩል እምቅ ሃይል (pressure) እንዲደርስ በማድረግ ሁሉም የተጠቀመበትን የሚከፍልበት ሲስተም መዘርጋት ይቻላል።
ከከተማ ውበትና ዘመናዊነት አንጻርም ዲሽን ታሳቢ ያደረገው መንግስታችን ውሃ ከማቅረብ ጋር የውሃ ታንከር በበረንዳ ላይ መስቀልን የጎሪጥ ቢመለከተው እንላለን።
እነዚህ ህንጻዎች ውስጥ መሃንዲሶች አይኖሩም ወይ? ወይስ ከትህትናቸው ብዛት ህንጻ ቀና ብለው አያዩም?
Via: ደሳለኝ ከበደ