በቀኝ ይሁን በግራ ወይም በጀርባ እና በሆዴ በየቱም አቅጣጫ ብተኛ እንቅልፍ እኔን ከድቶኛል። የከዳኝ እሱ ብቻ አይደለም ሁሉም በክህደቱ መርዞኛል። ሰዎች ከቤቴ ሊለቃቅሙ ይመጣሉ፤ ጓዳዬ ባዶ በሆነ ግዜ በመጡበት በር ይመለሳሉ።
እናም በባዶ ወንበሬ ላይ ተቀምጠው የነበሩ ሰዎችን አስታውሳለሁ። አዎን ቡና ከቀዘቀዘ ወዲያ ጥፍጥናው እሬት ነው። የግቢዬ አባዎች እንደኔ ተረስተው ደረቅ ቅጠል ያንጠባጥባሉ፤ አየሩ ይበርዳል ፤ሰማይ ጥቁር ደመና ቋጥሯል። ማስተዋል በቂ ነው ጎዳናዎችሁ በጠቅላላ ለሁሉም ነገሮች ፍላጎታቸውን አጥተዋል።
-ቡናው ቢመረኝ የምውጠው አማራጭ ስላጣው ነው። እንደቀዳውት ስለረሳውት ፈቃዴ መዘንጋቴ ስለሆነ..
-የውስጤን እሳት ለማብረድ የለኮስኩት ሲጋራ አልቋልና ጣቶቼን ለበለባቸው። በደንብ ልቃጠል! የጀመርኩት እሳት ነው የሚጨርሰኝ..
-ሁሌም ከዛሬ ጀምሮ እቀየራለሁ የእውነት እለወጣለሁ የሚል መሃላዬ ቀዝቃዛ ጸጸት በጭኔ ስር ይሰዳል። ይበለኝ! ስለራሴ እያወራው እራሴን የረሳው እኔ ነኝ..።
©️ imagination
ድጋፋችሁን የማዉቀዉ ላይክ👍 ስታረጉ ነዉ