#ለምን_ግን_ፈጣሪ...?
ምድርን ባጀብ ሞላት ለዱር ለገደሉ አበባን ፈጠረ፣
ጥበቡን ለማወቅ ለኛኮ አንተን ማዬት ይበቃን ነበረ።
በሰው እንዲወደድ ሁሉን እንዲያስማማ፣
ሀሳብን እንዲሰርቅ ቀልብን እንዲቀማ፣
ሸፋች ብኩን ዐይን እንዲልብህ ሰከን፣
የሰራ አካልህን ፈጥሮታል ያለ እንከን።
ሞገስ የታደለ ትከሻህ የኮራ፣
ወንዳወንድነትህ ከሩቅ የሚያስፈራ፣
በጎ ምግባሮችህ ወላድ የሚያስመኩ፣
እንዳንተ አላየሁም የተጣጣሙለት ፀባይ እና መልኩ።
ደምግባትህ ሙሉ ወዝ ወዘናህ መልካም፣
ፈገግታህ ብቻውን ያሳርፍ የለም ወይ ካለም ከንቱ ድካም?
አንደበትህ ጨዋው ዝም ብሎ ያልፋል፣
መልክህ ባለጌ ነው ሁሉን ይላከፋል።
ስንት የሄዋን ዘሮች በጎንህ ያለፉ፣
አቅላቸውን ጥለው ባንተ ፀዳል ጠፉ?
ብርሀን የተሞሉ ድምቀት የለበሱ፣
የሂወትን ፅልመት ታይተው የሚያስረሱ፣
የተሰበረን ልብ ባንዴ 'ሚፈውሱ፣
ድንቅ ግሩም አይኖች አድሎሀል እሱ።
እናታዲያ ለምን...? ለክብሩ መለኪያ ጨረቃን ፈጠረ ኮከብን ፈጠረ፣
እኛኮ አንተን አይተን በእጆቹ ፀጋ ተገርመን ነበረ ተደንቀን ነበረ።
ለምን...?
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
ምድርን ባጀብ ሞላት ለዱር ለገደሉ አበባን ፈጠረ፣
ጥበቡን ለማወቅ ለኛኮ አንተን ማዬት ይበቃን ነበረ።
በሰው እንዲወደድ ሁሉን እንዲያስማማ፣
ሀሳብን እንዲሰርቅ ቀልብን እንዲቀማ፣
ሸፋች ብኩን ዐይን እንዲልብህ ሰከን፣
የሰራ አካልህን ፈጥሮታል ያለ እንከን።
ሞገስ የታደለ ትከሻህ የኮራ፣
ወንዳወንድነትህ ከሩቅ የሚያስፈራ፣
በጎ ምግባሮችህ ወላድ የሚያስመኩ፣
እንዳንተ አላየሁም የተጣጣሙለት ፀባይ እና መልኩ።
ደምግባትህ ሙሉ ወዝ ወዘናህ መልካም፣
ፈገግታህ ብቻውን ያሳርፍ የለም ወይ ካለም ከንቱ ድካም?
አንደበትህ ጨዋው ዝም ብሎ ያልፋል፣
መልክህ ባለጌ ነው ሁሉን ይላከፋል።
ስንት የሄዋን ዘሮች በጎንህ ያለፉ፣
አቅላቸውን ጥለው ባንተ ፀዳል ጠፉ?
ብርሀን የተሞሉ ድምቀት የለበሱ፣
የሂወትን ፅልመት ታይተው የሚያስረሱ፣
የተሰበረን ልብ ባንዴ 'ሚፈውሱ፣
ድንቅ ግሩም አይኖች አድሎሀል እሱ።
እናታዲያ ለምን...? ለክብሩ መለኪያ ጨረቃን ፈጠረ ኮከብን ፈጠረ፣
እኛኮ አንተን አይተን በእጆቹ ፀጋ ተገርመን ነበረ ተደንቀን ነበረ።
ለምን...?
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha