የ ጥበብ ልሳን


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


መንፅሮን ያውልቁ።
የጥበብ ልሳን ጣት ነው ለዚህም ነው ጣቴ ነው ልሳኔ የምለው። የጥበብ ልሳን ምላስ ከሆነ ጥበብ ዋጋዋን ታጣለች ብር ያለው እየገዛት እንዳሻው ዘልዝሎ ሊበላት ይችላል።
ጣት አንደበት ከሆነ ጥበብ ከደጃችን አለች ማለት ነው። የጥበብ ልሳን ጣት ነው።
-ግጥሞች
-አጫጭር ድርሰቶች በፅሁፍ እና በድምፅ(በትረካ)
-አስተማሪ እና አዝናኝ ፅሁፍ
@JGosakey

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Quxba Jummaa ❤❤

Wa'ee Obsaatii, obsii ilma namaatiif gaarii dhaa sabriin barbaachisaa dha!
የጁምኣ እለት ቁጥባ❤❤
ስለ ትእግስት የተሰጠ አስተምህሮ, ትእግስት ለሰው ልጆች በሙሉ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው!


-ግፋችን አፍጦ...
፣ ሰው ከሰው እያባላ
-ከጎጇችን ዘልቆ ፣
...መብረር ያልጀመሩ እርግብ እያስቀላ
-በረሀብ ና እርዛት..
፣ በጥላቻ ግርዶሽ ሰውሮብን መላ
-ከምድሩ ባለቤት
፣ ከሰማያዊው አምላክ አሳጣን ከለላ።

-ያለ መንስኤ ሲፈስ...
፣ ደም ከጎርፍ ረክሶ
-ህግም ጨቋኝ ሲሆን ፣
ፍትህ ተንተርሶ..
-አቤት ማለት ነው ፣
ለጌታ አልቅሶ
-የዚች አለም ማብቂያ
፣ ይሆናልና ደርሶ...።

የጥበብ ልሳን!


ታላቁ የረመዳን ፆም ነገ አሐዱ ብሎ ይጀምራል አላህ ከሚጠቀሙበት ጎራ ይመድበን!
Somannii Guddaan Ramadaanaa Boruu Tokkko Ja'ee Egala Rabbii Warra Ittii(Irraa) Fayyadamu Cinattii Nu Haa Ramaduu!
The Greatest Fasting Ramadan It will be start Tommorow May God ALLAH get round us with those who Bless with this Month Blessing!

#FriApr1
6:48pm


-ንገሯት ለዚያች ልጅ
፣ ለዚያች ብላቴና
-ፈጣሪ ለቸራት ፣
ውበት ከ ወዘና
-ውበትሽ ከረቢ
፣ ከኣለህ ነው በሉና።

#ስልጤያንስ_በሬዱ!
የጥበብ ልሳን!


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#Motivation


Simannaa Baratota Haromaya Bara 2013 Walaloodhaan Midhagsine yeroo Gaarii Dabrsaa Ture!
የ 2013 ሀሮማያ ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅበላ በግጥም ስናጅብ ጥሩ ጊዜ አሰልፈናል!

@ArtGosa
@ArtGosa


(አበበች ጎበና )
አበበች ጎበና፣ የእኔ ባለዝና
የእናቴ ምትክ ፣ የኑሮዬ ፋና

የሚስጥር አውድማ ፣ ገመና ከታቼ
አቅፈሽ ያሳደግሽኝ ፣ ብቸኛ አጫዋቼ

በእሳት ዙሪያ ሆነሽ፣ ተረት ያወራሽኝ
ከብራና ዓለም ፣ ፊደል ያስቆጠርሽኝ

መንፈሰ ብርቱ ፣ ትሁት አገልጋይ
በመከራ ግዜ ፣ እንጀራ አቀባይ

በሄድሽበት ሁሉ ፣ ለእኔ እንደለፋሽ
አንድ ቀን ሳያምርብሽ፣ ይኸው ተደፋሽ

አንቺ ነበርሽ፣ የእኔ መገለጫ
የኑሮዬ ቅመም ፣ የሕይወቴ ማጣፈጫ

ሆዴም ተከፋ፣ መረረ ሀዘኔ
አወየው ዘንድሮ ፣ ተበላሸ ቀኔ

እንባዬም ሳይቀር፣ ከፊቴ ፈሰሰ
የሚያብሰው አጥቶ፣ እራሱን ወቀሰ

እንግዲህ ፈጣሪ፣ ነፍስሽን ይማረው
ከጀግኖቹ ጋራ ፣ በገነት ያኑረው። 😭😭😭
✍️ ቤዚቾ

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


-የብዙሃን እናት ፤
አበበች ጎበና
-ተሰናብተው ሄዱ
፤ እውነት መረጡና።

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


✍ሰው ያለ ሰው✍

-የ'ፖለቲካ ጥበብ ፣
ጥለቱ ጣል ጣል
-ቁጭቱ እስር ነው
፣ የዳር ዳሩ ፈትል።


-አንበሳን ሲፈጥረው፣
ፀጉሩን አጎፍሮ
-ንግስናም ሲሾመው
፣ ድንበሩን አስምሮ
-ወንድሙን ሲያስገፋው ፣
በትምክት አስክሮ
-ለዝንብ ይደፋዋል ፣
በአፍፂሙ አዙሮ።

-ለዱር ለ'አራዊቱ
፣ ለአለም ግዛት ሳይቀር
-አንብሳ መሪ ነው ፣
ተፈርቶ 'ሚከበር።

-ቅርንጫ'አፍ ተማምኖ ፣
እራሱን ካታለለ
-የክፉ ቀን ዘመድ
፣ ቅጠሉን ከጣለ
-ዛፉም እድሜ አይኖረው ፣
ደርቋል እየተባለ።

-እናም ባለጊዜ ፣
ባለተራው ጌታ
-ሀቂቃው ይህ ነው
፣ ይህ ነው እውነታ
-ሰው ያለ ሰው
፣ ግቡ ግብ አይመታ
-የጠፈርከውን አላልተህ
፣ ያሰርከውን ፍታ
-ፍትህ ዘሯ በዝቶ ፣
ታሳቅፈን መንታ።


-Waliin Wal taane;
harka walqabannee
-Jiruu hegaretiif haa
;Kaanuu Jabaannee.


✍ጎሳ ሙሳ(ጀሙ)
የመይሙና ልጅ

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


-ሀገር ማለት ሰው ነው ፣
ሲባል እሰማለው..
-መስማት ብቻ አይደል
፣ እውነት ነው አ'ምናለው..
-ታድያ ወገን ታስሮ ፣
ለምን ፀጥ ብዬ ዝምታ መርጣለው..
-ሀገር ታስሮ ደስታ ፤ሰው ሞቶ ፌሽታ ፣
ዘበት ነው አውቃለው።

የጥበብ ልሳን!

እኔም ድምፅ ነኝ!

እናንተም ድምፅ ሁኑ።

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


✍✍ሸዋ'ዬ✍✍

-አዲስ ነኝ እንግዳ ፣
ፀጉረ ልሙጥ
-ሸዋ'ዬን አይቼ
፣ ፍቅርን ስትሰጥ
-ወድጄ ቀረብኳት፣
ወንድ ሆኜ ቆራጥ።
:
የዛኔ...
:
-ስትመጣ ስጠጋት ፣
ስትይዘኝ ሳቅፋት
-ስታውቀኝ እኔን
፣ እኔም እሷን ሳውቃት
-ፍቅሯ አዳልጦኝ ፣
ሳትለ'ቀኝ ወደኳት።

✍ጎሳ ሙሳ(ጀሙ)
የመይሙና ልጅ

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


-ጠላ ጠላ ሲሉ ፣
ያዘ'ልቅ መስሏቸው
-አፍቅሮ አረፈው
፣ ጠጁን ዘር'ፎባቸው።

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


-ይጠጣል ወተት፣
ይበላል አሬራ
-ሀረርጌን አትንኳት ፣
ፅንፈኞች ሀደራ።

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


ተቅበዥ ባዥ ሲቀበዘበዝ፣
ሀገር ይገነባል ጎበዝ።

ለሀገራችን ተስፋ፣
ስትደክም ስትለፋ፣
ሀቅ ነግሰች በይፋ።


የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa


(ቀልቤን ባትሰርቀው)
ካፈቀርኩህማ ዘመናት አለፈ
ወተቱም እረግቶ ፣ ለቅቤ ተረፈ

እሳቱም ባነደው ፣ አመድን ወለደ
ደግሼም ሳልጠራህ፣ ኑሮተወደደ

ይኸው በትረካ፣ ስምህን እያወጋሁ
ስንቱን አቀበት ፣ በሀሳቤ ወጣሁ

የሆዴ ማጀትም ፣ ቅኔውን ቢሰፋ
ወርቁን አላገኘ፣ ሚዛንም አልደፋ።

ሰውነቴም ቢሆን አቅሙን ተነጠቀ
ፍቅርህን ተርቦ፣ በናፍቆት አለቀ።

ድሮም እኮ - - -
ያለቤቱ አይነድም እሣቱ
ማሩም ይቀርና ይበዛል እሬቱ

እህልም እኮ ካልዘሩት በወቅቱ
አረም ይከበዋል አያምርም ውጤቱ

ስለዚህ አለሜ - - -
በታሪክ ጀበና ፣ ስማችን ይቀዳ
ከራሳችን አልፎ፣ እንትረፍ ለባዳ

እንኳንስ የሰው ልጅ ፣ የተማረው ቀርቶ
እንስሳም ይኖራል ፣ በህብረት ተስማምቶ

እንደው ምን አለበት ፣ ቀልቤን ባትሰርቀው
አብረኸኝ ብትሆን ልቤን ባሳርፈው።
# ቤዚቾ

የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa
@ArtGosa




-ትላንት አቅርቅሬ ፣ ሳነባ ፤ ሳለቅስ ነበረ..
-ዛሬ ትላንት አልፎ ስስቅ ፤ ሀዘን ተሰበረ።

የሀገሬ ድል ሁሌም የኔ ነው። ካልቀመስቁ አልጠግብም ባይ እንዳይደለው 100 በ መቶ እርግጠኛ ነኝ እና የሀገሬ ድል የኔ ነው።



የጥበብ ልሳን!

@ArtGosa
@ArtGosa
@ArtGosa




አንዲት ምስል አለች

የጥበብ ልሳን!

✍🎤ጎሳ ሙሳ(ጀሙ)
የመይሙና ልጅ

@ArtGosa
@ArtGosa
@ArtGosa

Показано 20 последних публикаций.

219

подписчиков
Статистика канала