Ateriraአጤሪራ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


Ateriraአጤሪራ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций






ሰላም የአጤሪራ ቤተሰቦች፤
ረዘም ካለ ቆይታ በኋላ እትም ሃያንአንድን ይዘን ብቅ ብለናል። ጠደፍ ጠደፍ፤ለጠፍ
ለጠፍ ተደርጋ የተሰራች ናት እና እክል አይጠፋት ይሆናል። ከተጠፋፋን ወዲያ እንደ አንገት
ማስገቢያ ትያዝልን።
ዛሬም አለሁ ላላችሁን ፀሃፊያንም ሆነ አንባቢዎቿ ምስጋናችን ከልብ ነው!
መልካም ንባብ


ዞር ዞር ብለን ተመልሰናል!
ፅሁፎችዎን ይላኩልን!
@aterira_contact_us






Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የ60ዎቹ፣70ዎቹ እና 80ዎቹ ሙዚቃ ኦሬጂናል ኤሌክትሮኒክ ሚክስ....


እንኳን ለ126ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን!


Hilawe Tesfaye
Feb 29, 2016
" አንተን ሲደላህና ሲመችህ አገርህን የምትወዳት፤ ሲጎልብህና
ሲከፋህ የምትጠላት ከሆነ አንተ የምትወደው ሀገርህን ሳይሆን
ራስህን ነው።"
.
.
እንደው እውነት ለመናገር እቺ አባባል እንደጥቅስ ታክሲ ላይና
ራስጌ ለመለጠፍ ታምራለች እንጂ ለመተግበር ትከብዳለች።
ማንም ሰው አገሩ ሲመቸው ፍቅሩ ከፍ ይላል። ሲበደል ደግሞ
ተቃራኒው...
.
.
ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በበደል ውስጥም ሆነው ይቺን ጥቅስ
የእውነት ነውንነውታል። ምንም ቢበደሉም የሚያልፈውን
መንግስት ሳይሆን ቋሚዋን አገራቸውን አርቀው አይተዋል።
.
.
'ያወራብሽ ኖሮ የሰራልሽ ሞተ' ያሉት 'ከሀይለስላሴ' ጋር
የተጣሉት 'በላይ ዘለቀ' እንኳን 'ወንድ አይውጣብሽ' ብለው
ሀገራቸውን ተራግመዋል።
.
.
(1)
-
'ደጃዝማች ጉዋንጉል ዘገየ።'
-
"እኚህ ሰው ምኒሊክ ላይ ሸፍተው ከምኒሊክ ጭፍሮች ጋር
በጦርነት የተፈታተኑ ሰው ናቸው።
-
የውጪ ጦር ሲመጣብን ግን ከግዚያዊው ምኒሊክ ፀብ ይልቅ
ሩቋን ሀገራቸውን በማሰብ ህዳር 24 ቀን ምኒሊክ 'መርሳ' ላይ
ሰፍረው ሳለ የጓንጉል መልክተኛ እንዲህ የሚል መልክት ይዞ
መጣ:
-
-
"ጃንሆይ ከርሶ ተጣልቼ በርሀ ገብቻለሁ። አሁን ግን በሀገሬ ላይ
የውጪ ጠላት ስለመጣባት የርሶና የኔ ጉዳይ ቀርቶ ይማሩኝና
መጥቼ ከእርሶ ጌታዬ ጋር ሆኜ ያገሬን ጠላት ልውጋ?" ብሎ
ሲናገር ምኒሊክ ተደስተው 'ይምጣ ምሬዋለሁ' ብለው
ተቀበሉት።
-
(ይልሀል 'ጳውሎስ ኞኞ' አጤ ምኒሊክ' በሚለው መፃፉ)
.
.
(2)
-
ክቡሩ ሰው 'ባልቻ ሳፎ (አባ ነፍሶ)'
-
እኚህ ሰውዬ ምንም እንኳን የአድዋ ጦርነትን ጨምሮ ላገራቸው
ወሳኝ ስራ የሰሩ ቢሆንም 'ንግስት ዘውዲቱን' ከሚደግፉት
ወገን ስለነበሩ የአልጋወራሽ ተፈሪን ትዕዛዝ አልቀበልም ስላሉ
ታስረውና ተግዘው ይኖሩ ነበር።
-
-
ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ ሲወረን በዚያን ጊዜ እንደሳቸው
በእስራትና ግዞት ላይ የነበሩት እነ 'ደጃዝማች አባውቃው፤ ራስ
ሀይሉ ካሳ' እና ሌሎች ነፃ በመሆናቸው ከጣሊያኖች ጋር በደስታ
ሲፈነጥዙ፤
-
-
ባልቻ ግን " ጠላቴ ሀይለስላሴ እንኳን ወደቀ" ሊሉ ቀርቶ
ጭራሽ በእልፍኛቸው ውስጥ እየተዘዋወሩ "ወይኔ እኔ ባልቻ!
አይኔ እያየ የምኒሊክ አገር ኢትዮጵያ ትውደቅ? በማለት ምርር
ብለው አለቀሱ" ይባላል።
-
-
ዕንባቸውን አፍሰው አልቀሩም ጉልበታቸው በደከመበት
በስተርጅና ሲዋጉ ደማቸውን አፍሰው ሞቱ።"
-
(ይለናል 'ብርሀኑ ድንቄ' ቄሳርና አብዬት' በሚለው መፅሀፉ)
.
.
(3)
-
'ልጅ አብዩ'
-
ይሄ 'ከራስ መኮንን' ጋር መቀሌ የዘመተው ልጅ ነው። እራስ
'አሉላን' ጨምሮ መኳንንቶቹ ምሽጉን ጥሶ ስለመግባት ሲማከሩ
አብዩ እየተቃወመ ተናገረ " ሰራዊቱን በከንቱ ከምናስጨርስ
ውሀውን እንዝጋበት እጁን ይሰጣል።" ሲል ሁሉም የአብዩን
ሀሳብ 'ፈርተህ እንዳይሆን' በሚል ሲቃወሙበት
-
-
አብዩም መለሰ " ሰራዊቱ በከንቱ እንዲያልቅ በመደረጉ
አዝናለሁ። ግን እናንተ ስትሞቱ እኔ የቀረሁ እንደሆን የዛኔ እኔ
ፈሪ ተብዬ እሰደባለሁ" ብሎ ባላመነበት ጦርነት ዘምቶ
በሚያሳዝን ሁኔታ ተዋግቶ ሞተ።
-
-
እንዳለውም ብዙ ሰራዊት አለቀ። እቴጌ ጣይቱ እሱ ያነሳውን
'ውሀውን የመቆጣጠር' ሀሳብ አምጥተው ተተገበረና ጣሊያኖቹ
ከምሽጋቸው ወጥተው እጅ ሰጡ።
-
(ይሉናል ተክለሀዋርያት 'ኦቶባዮግራፊ' የህይወቴ ታሪክ'
በሚለው መፅሀፋቸው)
.
.
ከነገ ወዲያ እሮብ የካቲት 23 የአድዋ ድል በአል ተከብሮ
ይውላልና መልካም በአል!!








ሰላም የአጤሪራ ቤተሰቦች፤
ረዘም ካለ ቆይታ በኋላ እትም ሃያን ይዘን ብቅ ብለናል። ጠደፍ ጠደፍ፤ለጠፍ ለጠፍ ተደርጋ የተሰራች ናት እና እክል አይጠፋት ይሆናል። ከተጠፋፋን ወዲያ እንደ አንገት ማስገቢያ ትያዝልን።
ዛሬም አለሁ ላላችሁን ፀሃፊያንም ሆነ አንባቢዎቿ ምስጋናችን ከልብ ነው!
መልካም ንባብ

ዛሬም ነገም ከትናት ወዲያም አጤሪራ የእርሶ ናትና ሳይሳቀቁ ስራዎትን ይላኩልን!

አጤሪራን ያንብቡ - ለአጤሪራ ይፃፉ - አጤሪራን ለወዳጆችዎ ያጋሩ!


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Aterira ISSUE 19_አጤሪራ እትም 19.pdf
1.1Мб
ሰላም የአጤሪራ ቤተሰቦች
ዘለግ ካለ ቆይታ በኋላ እትም አስራዘጠኝን ይዘን መተናል። ይሄው ሳይታሰብ ለሃያ አንድ አንድ ጎደል ደርሳለች። እንደድሮው በቀጠሮ መደረስ ቢከብዳትም በእናንተው እርዳታ አለች።
ምስጋናችን ገደብ የለውም!






Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram




ሰላም የአጤሪራ ቤተሰቦች፤
መቼም ከዚህ ወዲያስ ይቅርታ መጠየቅ በእናንተው መዘባበት ይሆናልና ይቅር። ዛሬም
አይናችንን በጨው አጥበን እትም 18ን ይዘን መተናል።

Показано 20 последних публикаций.

2 185

подписчиков
Статистика канала