የዶላር ዋጋ ቅናሽ‼️
አዲሱን የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ተከትሎ ባንኮች በውጭ ምንዛሬ ላይ እስከ አስራ አንድ ብር የሚደርስ ቅናሽ ማሳየታቸው ተገለጸ‼️
ብሄራዊ ባንክ አዲስ ባወጣው መመሪያ ባንኮች በየቀኑ በሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ የመሸጫና የመግዣ መጠን ላይ ልዩነቱ ከሁለት በመቶ በላይ እንዳይሆን ማስታወቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የዶላር መሸጫ ዋጋቸው ላይ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡
በዚህ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የመሸጫ እና የመግዣ ዋጋቸውን በየዕለቱ እየወሰኑ ይፋ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ በአብዛኛዎቹ ባንኮች በዶላር መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸው መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በላይ መድረሱ ተጠቁሟል።
በመሆኑም ብሔራዊ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ባስተዋወቀው አዲስ ፖሊሲ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የመግዣ እና የመሸጫ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ወስኗል።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ባወጣው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ግብይት የዋጋ ዝርዝር ላይ የዶላር የመሸጫ ዋጋው ከትናንቱ ጋር ሲነጻጸር የስምንት ብር ቅናሽ ያሳየ ሲሆን የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ደግሞ የአስራ አንድ ብር ቅናሽ አድርጓል፡፡
ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ በተመለከተ ለሁሉም ባንኮች በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን እስከ ረቡዕ ድረስ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አዟል።
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s