ገቢዎች ሚኒስቴር የባንክ ሰራተኞች በአነስተኛ ወለድ ያገኙት ብድር እንደ ገቢ ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ሕግ አወጣ‼️
👉ይህ መመሪያ ከተተገበር 50% ገቢያችንን ለመንግሥት እየሰጠን ነው:-የባንክ ሰራተኞች‼️
የባንክ ሰራተኞች የባንክ ሰራተኛ ስለሆኑ ከሚሰሩባቸው ባንኮች ለቤት እና መኪና በአነስተኛ ወለድ የሚወስዱት ብድር ፣ ለወሰዱት ብድር የሚከፍሉት አነስተኛ ወለድ ከገበያው ወለድ ጋር ያለው ልዩነት ተሰልቶ የሚመጣው ልዩነት እንደ ገቢ ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ ሊደረግ መሆኑን የባንክ ሰራተኞች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። ይህም ከዚህ ወር ማለትም ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን መመሪያው ደርሶናል ብለዋል።
በገቢዎች ሚኒስቴር “የቅናሽ ወለድ የአይነት ጥቅም ላይ የሚከፈል ግብር” በሚል ሊተገበር የቀረበው ህግ በበርካታ የባንክ ሰራተኞች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል የባንክ ሰራተኞች “ህጉ የባንክ ሰራተኛ በመሆናችን የምናገኘውን ብቸኛ ጥቅም የሚነጥቀን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
ንግድ ባንኮች በተለምዶ ለደንበኞቻቸው ብድርን ሲሰጡ ከ12 በመቶ በላይ ወለድ ያስከፍላሉ። ሆኖም ሰራተኞቻቸው ቤትና መኪናን መግዛት ሲፈልጉ የሚያበድሯቸው በሰባት በመቶ ወለድ ነው። ይህ ማለት ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንኮች ቆጣቢዎች ያስቀመጠው ትንሹ የወለድ ምጣኔ ነው። ንግድ ባንኮችም ለሰራተኞቻቸው የሚሰጡት ዋነኛ ማትጊያ ሰራተኞቻው ቤትና መኪና መግዛት ሲፈልጉ በትንሹ መቆጠቢያ ወለድ ማለትም በሰባት በመቶ ማበደርን ነው።
የገቢዎች ሚኒስቴር በ2016 አ.ም በአነስተኛ ወለድ ብድር የሚያገኙ ሰዎች ፣ የቅናሽ ወለድ የአይነት ጥቅም ላይ የሚከፈል ግብርን መክፈል አለባቸው በሚል በዋነኝነት የባንክ ሰራተኞችን ኢላማ ያደረገ ህግ አወጣ። ይህ ማለት ፣ በሰባት በመቶ ወለድ ብድርን ያገኘ አንድ የባንክ ሰራተኛ በየወሩ የሚከፍለው ወለድ ፣ በገበያ ወለድ ቢበደር ኖሮ ሊከፍል ከነበረው ወርሀዊ ወለድ ላይ ተቀንሶ የሚመጣው ልዩነት ፣ የሰራተኛው ደሞዝ ላይ ተደምሮ ግብር እንዲከፍል ይገደዳል።
ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይውሰዱ።
✍️አዩዘበሀሻ
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s