ዛሬ መርካቶ የተፈጠረውን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሚከተለውን መረጃ ሰጥቷል👇‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል‼️
ውዥንብሩ ከየት መጣ የሚለው ሲጣራ በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ ሲሆን በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል::
ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የሚያስቡ አካላት በሚነዟቸው ውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል፡፡
በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እየተሰራ ያለ ስራ ሲሆን ለዚህም የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ ሊሆን ይገባል::
አንዳንድ ያለደረሰኝ በመገበያየት ሕዝብና መንግሥት ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እያሳጡ የራሳቸውን ኪስ የሚሞሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡ ብልሹ አሠራርን ጨምሮ ደረሰኝ የማቆርጡ እና ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽሙ አካላትን በ7075 ላይ እንዲጠቁሙ ጥሪውን አቅርቧል።
#አዩዘሀበሻ
⬇️⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇⬇️⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s