BDU FELLOWSHIP VLM


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ይህ የBahirDar University Evangelical Christian Student Fellowship VLM ይፍዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


📣#This_Week 🌐

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መገዛት   I    ማረፍ

Follow Us On 

👨‍💻INSTAGRAM 
👨‍💻 YOUTUBE


🗣️ Blog Monday ➥ ስኬት

በሀና ኤልያስ #ክፍል-2

እግዚአብሄር ዘላለም ለሚባለው ህይወታችን የሚሰጠውን ቦታ በድርጊት ወይንም በስራ ካየንባቸው ነገሮች ዋነኛው፣ የእኛን የዘላለም አድራሻ ይቀይር ዘንድ፣ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር መላኩ ነው። መዳናችን፣ ኢየሱስ ለእኛ በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ በማመን ብቻ ያገኘነው ስጦታ እንደሆነ እናውቃለን። ሁልጊዜ መርሳት የሌለብን ግን፣ ስጦታ የሆነው ለእኛ ብቻ እንጂ፣ ኢየሱስን ግን ያላስከፈለው ዋጋ አልነበረም። ነጻ ስጦታ የሆነው ለእኛ ብቻ ነው። ኢየሱስ ግን እያንዳንዱን የውርደት ጥግ ያየባቸው አሰቃቂ 33 አመታቶች ናቸው። እኛ ሰዎች ስለሆንን ለእኛ ሰው መሆን ቀላል ነው። መጽሀፉ ስለ ኢየሱስ ሲነግረን ግን በሰው ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፣ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ይለናል። ኢየሱስ ራሱን ማዋረድ የጀመረው፥ የሚሰቀልበት ሰአት ሲደርስ አይደለም። መስቀል ላይ ሲውል አይደለም። ራሱ ከምድር አፈር የሰራውን ሰው ለመሆን ሲወስን ነው። ራሱን ሰው ለማድረግ ከመወሰኑ አንስቶ፣ በምድር ላይ አለ በተባለው ውርደት ስቃይና መከራ ውስጥ የማለፉ ሚስጥር፥ እግዚአብሄር ዘላለም ለሚባለው ህይወት ያለውን ቦታ በትክክል ሊያስረዳን ይችላል። ክርስቶስ በምድር ላይ እያለ የተለያዩ ሰዎችን በመፈወስ፣ ከሰይጣን እስራት ነጻ በማውጣትና በተለያዩ መንገዶች የሰው ልጆችን የረዳ ቢሆንም ዋናው የመጣበት አላማ ግን የእኛን ዘላለም ለማስተካከል ነው። እንዲያውም በምድር ላይ የሰራቸው እያንዳንዱ ተአምራቶች ወደ ምድር የመጣበትን የዘላለም ህይወት ጉዳይ ሰዎች ...........

🔗  ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗
B
🌐 TELEGRAM  📱 INSTAGRAM   🖥 YOUTUBE


🗣️ Blog Monday ➥ ስኬት

በሀና ኤልያስ #ክፍል-1

ስኬት ስለሚለው ቃል ስናስብ መቼም ሁላችንም ልብ ውስጥ የሚመጡ ይሄን ይሄን ባሳካ ብለን በልባችን ውስጥ የምናስባቸው፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስኬቶች ይኖሩናል። ከዚያም በተጨማሪ ደግሞ በአካባቢያችን ላይ የምናውቃቸው ወይንም በsocial media ገጾቻችን እነሱ እንኳን ሳያውቁን እኛ የምናውቃቸውና የምንከተላቸው፣ በየቀኑ የሚያወጡትን ፎቶዎች እያየን የስኬት ምሳሌዎች ያረግናቸው ሰዎችም ይኖራሉ። ስኬት ለሁሉም ሰው የተለያየ ትርጉም ያለውና በህይወት ዋጋ ከምንሰጣቸው ነገሮች ጋር የተያያዘ ነገር ነው። ለአንዳንዱ በልፋቱ የሚያገኘው ደሞዝና ዋጋው ነው። ለሌላው ደግሞ ትምህርቱን ጨርሶ ያሰበውን ስራ መያዝ ማግባትና መውለድ ሊሆን ይችላል። ለሌላው ደግሞ አካባቢው ባሉ ሰዎች ወይንም በብዙሀኑ ዘንድ በሰራው ስራ እውቅናና ዝናን ማግኘት ሊሆን ይችላል...........

🔗  ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐 TELEGRAM  📱 INSTAGRAM   🖥 YOUTUBE


ፊልጵስዩስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤
²⁴ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።


በዚህች ምድር ላይ ስንኖር ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ጉልበታችንን እስክንሰጥ ድረስ ብዙ ትኩረታችንን የሚፈልጉ ሁኔታዎች ይገጥሙናል። ሰው እንደመሆናችን ማሰብና መጨነቃችን አዲስ ነገር ባይሆንም ጉዳዮቻችን አዕምሮአችንን ተቆጣጥረው ከዛ ውጪ ማሰብ የማንችልበት ሁኔታ ላይ ከደረስን ግን መንፈሳዊ ዝለት ውስጥ ከመክተታቸውም ባሻገር ነገን የማየት ፍላጎታችንን ሊነጥቁ ጭምር ይችላሉ።

የጳውሎስን የጭንቀት ምንጮች ስናይ አንድ ነገር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ለመሞት ሲጓጓ ኢየሱስን በመናፈቅ፣ ለመኖር ሲያስብ ደግሞ ለኢየሱስ የሚሆን ሰውን ስለማዘጋጀት ብሎ ነበር። ጳውሎስ ከእስር ቤት ወጥቶ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ስለመትከል አልተጨነቀም ይሄም ቢሆን እኮ አስደናቂ ሀሳብ ነበር ነገር ግን ጳውሎስ የሚበልጠውን ናፈቀ እርሱም ኢየሱስን በአገልግሎቱም ሆነ በሞቱ ማየት ነው። ኢየሱስ ላይ ትኩረት ስናደርግ አሁን ላይ እየተጨነቅንባቸው ያሉ ጉዳዮች በእርሱ ሀሳብ ይተካሉ። እየኖርም ሆነ እየሞትን እርሱን ስለማክበር ማሰብ እንጀምራለን። አንድ ሀሳብና ትኩረት እርሱም ኢየሱስ ብቻ ይሁንልን!

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐TELEGRAM  💻INSTAGRAM  🖥 YOUTUBE


📣ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ወደ እናንተ በቴሌግራም እና በኢንስታግራም ገፃችን የተለያዩ መንፈሳዊ ይዘቶችን የምናቀርብላችሁ ይሆናል ።

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐TELEGRAM  💻INSTAGRAM  🖥 YOUTUBE


📌 ለሁሉም የባህርዳር ፌሎውሺፕ  አባላት

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከምናውቀው የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት (Fellowship) እውቅና ውጪ የሆነ እና የቀደመውን  ህብረት በመከፋፈል አዲስ ህብረት ለመመስረት በተለያዩ ተማሪዎች እና ከFellowship ውጭ ባሉ አካላት ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

ይህ አዲስ Fellowship የማቋቋም ሂደት በ  Great Commission Ministry እየተመራ ያለ እና በህብረታችን እውቅና ያልተሰጠው መሆኑን እየገለፅን ፤  ህብረታችን እንደ ሁል ጊዜ በነበረበት  የሚቀጥል መሆኑን እናሳውቃለን።

ተማሪዎች እና ምሩቃን ሁላችሁ ከዚህ አይነት እንቅስቃሴ ራሳችሁን እንድትጠብቁ እና እንደ ከዚህ በፊቱ አንድ የተማሪዎች ፈሎውሺፕ እንዳለ ለማሳወቅ እንፈልጋለን።

ከአጠቃላይ የህብረቱ  መሪዎች

መደበኛ ፕሮግራማችን

📅 ዘወትር እሁድ
⏰ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
📍 መሀል MKC ቤተክርስቲያን


ሰላም ቅዱሳን በፈተና ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የ GF ፕሮግራም በዚህ ሳምንት ይቀጥላል ።

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐TELEGRAM  💻INSTAGRAM  🖥 YOUTUBE


ሰላም ቅዱሳን
ዛሬ የ GF ፕሮግራማችን የሚቀጥል ይሆናል ።

@bdu_fellowship


ሰርገኛው ክርስቲያን01.pdf
9.9Мб
ሰላም ቅዱሳን፣  ይህ በ Counseling Team ሰርገኛው ክርስቲያን   በሚል ሀሳብ የተዘጋጀ Pdf ነው።

ሁላችንም በያለንበት እናንብብ!!!!

ለሌሎችም ተማሪዎች ሼር በማድረግ እርስ በእርስ እንበረታታ!


FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐TELEGRAM  💻INSTAGRAM  🖥 YOUTUBE


📣ዛሬ የ GF ፕሮግራማችን የማይኖር መሆኑን እንድታውቁ ።


@bdu_fellowship




Репост из: BDU_ECSF opportunities
📢 Exciting Announcement for Christian Students at BDU!

We are thrilled to introduce BDU Fellowship Opportunity, a platform dedicated to helping Christian students bridge the information gap about opportunities that align with Christian values and principles.

🌟 Our Focus Areas:
🎓 Scholarship Opportunities – Helping you achieve your academic dreams.
💡 Startup Grant Opportunities – Supporting your innovative ideas and ventures.
💼 Freelance Opportunities – Connecting you with flexible and meaningful work.
🤝 Mentorship Programs – Guiding you through personal and professional growth.
🗣️ Experience Sharing by Experts – Learning from successful professionals in your field.

Join us to access resources, connections, and opportunities tailored to your growth and success!

📌 Let’s grow together, guided by faith and purpose!


እግዚአብሔር ባለ መድኃኒት አድርጎ ለህዝቡ የመረጣቸው እድለኞች እንደ መንደር ጎረምሳ ሸክም ሲሆኑበት ፤ የህዝቡን ጭንቀት እንዲያቀሉ የተጠሩ ይባስ ቀንበርን ሲያከብዱባቸው፤ በፍርሃት ውስጥ ላሉ የተስፋን ጭላንጭል፣ የእግዜሩ ድምፅ  ማሳያ ሊሆኑለት ሲያቅታቸው፤ መድሃንያለም አንዱን ልጁን መድኃኒት አድርጎ ለሰው ልጅ ሁሉ ሰጠው!


ይሄ የተወለደው ንጉስ መድኃኒት እና ብርሃን ነው። በክፉ ትዕቢታችን ለታሰርንበት የሀጥያት፤የሰይጣን እና የሞት እስራት ብቸኛ መፍትሔ ሆኖ መጥቶልናልና!

ከጨለማ ሊያወጣን የሚያበራ የንጋት ኮኮብ ሆኖ ፤የተቀባው መሲህ ሰላምን ይዞ መጣልን!


በነፍሳችን ሁካታ  ስንኖር ለነበርን አመፀኛ እና ተስፋ ቢስ ተቅበዝባዦች የእረፍት ስጦታ ይዞ ፤ ለህዝቦች ሁሉ የሚሆነው የአለም መድኃኒት ሊጎበኘን መጣ፤ ጌታ ኢየሱስ መጣ!

ሉቃስ 2፥10
እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

መልካም የልደት መታሰቢያ በዓል

Amanuel.T


FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ


📣#Update

በተቻለን መጠን ለሁላችሁም ለመላክ ሞክረናል ከዚህ ሰዓት ጀምሮ Postcard ለማግኘት Free Template Bot ላይ ሊንክ ስላደረግን ከዛ ማግኘት ትችላላችሁ ።

🔗🔗 Bot Link @bduvlm_bot

ቦቱን  Start በሉት ከሚመጣላችሁ ዝርዘር Get Your Postcard የሚለውን በመጫን ታገኛላችሁ ።

ተባረኩ

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐TELEGRAM  💻INSTAGRAM  🖥 YOUTUBE


( ለፕሮፋይላችሁ እና ለወዳጆቻችሁ ለመላክ ) HD
#QouteVerse #Bduvlm #Jesus
#Jesusbirth #holynight
#Jesusislove#Joytotheworld . .

የጠፋው ሊፈለግ ቃል ስጋ ለበሰ
    ጨለማን ሊያጠፋ ብርሃን ተወለደ
    ሞትን ሊየሳፍር ህይወት ተጀመረ
    በእርሱ ላመኑቱ ድነትን ለገሰ
    በዳግም ውልደት የሰው ልጅ ተረፈ
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ዮሐንስ 3፥16

“ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።”
                             ዮሐንስ 1:9

“Ifichi inni dhugaan, inni gara biyya lafaa dhufe, namoota hundumaaf in ibsa.”
                                Yoh. 1:9

“እቲ ንነፍሲ ወከፍ ሰብ ዜብርህ ብርሃን ሓቂ ናብ ዓለም ይመጽእ ነበረ።”
               ወንጌል ዮሐንስ 1፥9


FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐TELEGRAM  💻INSTAGRAM  🖥 YOUTUBE

25k 1 46 1 22

📣#POSTCARD

🎆 ሰላም ተወዳጆች   ለሚወዱት ወዳጅ
በተለይ  አማኝ ላልሆኑ ወዳጆቻችሁ የሚሆን በጣም ውብ ካርድ አዘጋጅተናል። አንድ ሰው የሁለት ሰዎች ስም ብቻ ነው መላክ የሚችለው ካርዱ ላይ የምትልኩለትን ሰው ስም አስገብተን መልሰን እናቀርባለን። የሁለት ጓደኞቻችሁን ስም  አሁን ይፃፉልን።

ስም ብቻ ነው መላክ የሚቻለው  ቦቱን start እያላችሁ ስም መላክ ትችላላችሁ ።

@BduDPs_bot

FOLLOWING THE KING
         ንጉሱን መከተል

KNOW  I   OBEY   I   REST
  ማወቅ  I   መታዘዝ   I    ማረፍ

Follow Us On  🔗

🌐TELEGRAM  💻INSTAGRAM  🖥 YOUTUBE



Показано 17 последних публикаций.