ይኽውልሽ አለሜ...ከሄድሽ ጀምሮ
ሰውነት ተረት ነው ስሜቴ ተቀብሮ
ካፊያ አመል ትርጉም
አልባ ኩንቱ መኖር
እየሄድኩኝ ወደ ማላውቀው
የህይወት መስመር
የጣልኩትን የሚያነሳ
ንግግሬ የሚጥመው
ስላጣውኝ ለማወራው
ትኩረት የሚሰጠው
ብቸኛ ወዳጄ ወረቀት ሆነና
መጻፌን ነው ማውቀው
ጉዳቴን ልረሳው ልቤን ከሀዘን ላቀና
በዚያች ጠባብ የወረቀት መስመር
ህመም ስቃዬን እንባዬን ስቀብር
ቅስምን የሚሰብር አሳዛኙ ቅኝት
ግጥሜን ሳነበው እንባ ይሞላል ከኔ ፊት
ባየሽ ...ባየሽ እያልኩ
ትመጪያለሽ ብዬ ልቤን በተስፋ ስሞላው
ቤቴ ናፍቆሻል እያልኩ ስንቴ እንደማጸዳው
የሃሳብ ባሪያ ሁኜ ግዞተኛው
ለምን ሄደች እያልኩ ከዕድሜዬ አመሸው
እድሜ ላንቺ ህይወት ላይ ሸፈትኩ
ከሄድሽበት መንገድ በቁም ታሰርኩ
ዘንድሮ ከከረምኩኝ ካለውኝ በህይወት
እንዳምና አልጠብቅሽም
ግጥምም አልጽፍ እውነት!!
✍️ዳዊት
@betagitim
@betagitim
ሰውነት ተረት ነው ስሜቴ ተቀብሮ
ካፊያ አመል ትርጉም
አልባ ኩንቱ መኖር
እየሄድኩኝ ወደ ማላውቀው
የህይወት መስመር
የጣልኩትን የሚያነሳ
ንግግሬ የሚጥመው
ስላጣውኝ ለማወራው
ትኩረት የሚሰጠው
ብቸኛ ወዳጄ ወረቀት ሆነና
መጻፌን ነው ማውቀው
ጉዳቴን ልረሳው ልቤን ከሀዘን ላቀና
በዚያች ጠባብ የወረቀት መስመር
ህመም ስቃዬን እንባዬን ስቀብር
ቅስምን የሚሰብር አሳዛኙ ቅኝት
ግጥሜን ሳነበው እንባ ይሞላል ከኔ ፊት
ባየሽ ...ባየሽ እያልኩ
ትመጪያለሽ ብዬ ልቤን በተስፋ ስሞላው
ቤቴ ናፍቆሻል እያልኩ ስንቴ እንደማጸዳው
የሃሳብ ባሪያ ሁኜ ግዞተኛው
ለምን ሄደች እያልኩ ከዕድሜዬ አመሸው
እድሜ ላንቺ ህይወት ላይ ሸፈትኩ
ከሄድሽበት መንገድ በቁም ታሰርኩ
ዘንድሮ ከከረምኩኝ ካለውኝ በህይወት
እንዳምና አልጠብቅሽም
ግጥምም አልጽፍ እውነት!!
✍️ዳዊት
@betagitim
@betagitim