Big Habesha Tech


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Технологии


This is my user name @bighabesha
በተመሳሳይ ሰምና profile እንደትጭበርበሩ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций


📱 YouTube.com/@bighabesha

በሉ በዚ አጋጣሚ ያችን ነገር አብርታችሁ ሾፋ ሾፍ አድርጓት።😆


Guys 🌐YouTube ይሰራላችኋል?


ለተለያዩ ድረገፆች ወይ የማህበራዊ ሚድያ አካውንቶች የይለፍ ቃላትን ስንሰጥ የምንጠቀመው
⚫26 Uppercase letters
⚫26 Lowercase letters
⚫10 ቁጥሮችን
⚫32 የተለመዱ (special characters)ን ነው።
ይህም በአጠቃላይ በእንግሊዝኛ ኪቦርድ 94 ካራክተሮችን ለይለፍ ቃልነት እንጠቀማለን።

እንበልና አንድ ድረገፅ ላይ መጠቀም የምንችለው የይለፍ ቃል የካራክተሮች ርዝመት 8 ቢሆን በአጠቃላይ 94^8 = 6,095,689,385,410,816 ወይም 6.1 ኳንቲሊየን ወይም 6 ቢሊየን ቢሊየን የተለያዩ የይለፍ ቃሎችን መፍጠር እንችላለን።

በሳይበር ሴኪዩሪቲ ዘርፍ የይለፍ ቃል ለመስበር ከምንጠቀምባቸው መንገዶች መካከል ዋናው Brute-force attack ይባላል።

Brute-force attack ማለት 1 user ሊጠቀመው የሚችለውን የይለፍ ቃል ለማወቅ የተለያዩ የይለፍ ቃላትን በተደጋጋሚ እያስገቡ በመሞከር መስራቱን ማረጋገጥ ማለት ነው።ይህም በጣም አድካሚና ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም ብዚ ጊዜ የተለመዱና ተገማች የይለፍ ቃላትን የሚጠቀሙ ሰዎችን በቀላሉ ሃክ ለማድረግ ይጠቅማል። Brute-force attack ተጠቅሞ የይለፍ ቃልን ለማወቅ የሚወስደው ጊዜ እንደምንጠቀመው የሃኪንግ ኮምፒውተር ፍጥነት፣ የተጠቀምነው የይለፍ ቃል ርዝመት እንዲሁም ተለዋዋጭነት (የተለያዩ ካራክተሮችን ቀላቅሎ መጠቀም) ላይ ይወሰናል።
safetydetectives.com ባወጣው ጥናት መሰረት በ2023 ብዙ ሰው የሚከተሉትን ቃላት በብዛት ለይለፍቃልነት ተጠቅመዋል።

123456, password, 123456789, 12345, 12345678, qwerty, 1234567, 111111, 1234567890, 123123, abc123, 1234, password1, iloveyou, 1q2w3e4r, 000000, qwerty123, zaq12wsx, dragon, sunshine, princess, letmein, 654321, monkey, 27653, 1qaz2wsx, 123321


አንድ ሃከር እነዚህን የይለፍ ቃላት በቀላሉ crack ማድረግ የሚችል ሲሆን ምናልባት 1ዱን ፊደል Uppercase ብናደርገው ወይም special character ብናስገባ ግን ለመስበር እጅግ ከባድ ይሆናል።


⚠️ለጥንቃቄ
ቀጥታ ፓስወርዳችሁ አታስገቡ ተመሳሳይ character በማስገባት ምክሩት።
ለምሳሌ የናንተ password "Abebe12" ቢሆን "Aster23" አድርጋችሁ።


https://www.passwordmonster.com/

እዚህ ድረገፅ ላይ የናንተ password ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነና ለመጠለፍ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅበት ግምታዊ መልስ ይሰጣችኋል።

የተለያዩ የPassword character እየቀያየራችሁ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ ሞክሩት። በዛውም ምን አይነት password መጠቀም እንዳለባችሁ ይገባችኋል።

የመጣላችሁን ጊዜ comment ላይ አሳውቁን።
©bighabesha_softwares


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በአሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ያድርግልን።🙌

ዒድ ሙባረክ !

@bighabesha_softwares


#Telegram_scam

ብዙዎችን የቴሌግራም username እንግዛችሁ በሚል ሰበብ እየተጭበረበሩ ይገኛሉ።

እንደሚታወቀው የተለያዩ የቴሌግራም usernames fragment.com ላይ መገበያየት እንችላለን። ይሁን እንጂ አጭበርባሪዎች ተመሳሳይ web app በመስራት ለማጭበርበር እየሞከሩ ይገኛሉ።

አጭበርባሪዎቹ በመጀመሪያ ትክክለኛውን የfragment ሊንክ በመላክ እና በከፍተኛ ገንዘብ (በ3,000, 5,000 ton) ሊገዟችሁ እንደሚፈልጉ ይነግሯችኋል።
እናንተም ጥሩ እድል አገኘሁ በማለት ወዲያውኑ ትስማማላችሁ ከዚያም እነሱ ከfragment ጋር ተመሳሳይ የሆነ mini app ሰርተው የናንተን username mini app ላይ ያስገባሉ። ከዚያም እዛ mini app የናንተ username በድርድር ላይ መሆኑን ትመለከታላችሁ።

ከዚያም እናንተ ክፍያውን ለመቀበል ስትሞክሩ wallet connect ማድረግ እና fee መጀመሪያ ማስገባት ይኖርባችኋል። በርግጥ ሙሉ ui ከትክክለኛው fragment ጋር ስለሚመሳሰል ገንዘቡን deposit ታደርጋላችሁ። ሿሿ ሰሯችሁ ማለት አይደል!

Username እንገዛለን በሚል የሚደረጉ የማጭበርበር ዘዴዎች ብዙ አይነት ናቸው።
አንድ ሰው username ልግዛችሁ ብሎ ሲጠይቃችሁ
⚫የኔ username ምን የተለየ ነገር ኖሮት ነው የሚገዛኝ ብላችሁ አስቡ።
⚫አንድ ተራ username ይህን ያክል የተጋነነ ዋጋ እንዴት ሊያወጣ ይችላል ብላችሁ አስቡ።
⚫Online ላይ የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች 99% የሚሆኑት የሚፈፀሙት ካልታወቁ ሰዎች የሚደርሱ መልዕክቶችን ምላሽ በመስጠት ነው። ስለዚህ አንድ ሰው መጀመርያ contact ሲያደርጋችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።

#stay_safe

©bighabesha_softwares


Telegram premium ማድረግ ከፈለጋችሁ
Inbox: @bighabesha

ለTelegram Premium አዲስ ከሆናችሁ inbox ከማድረጋችሁ በፊት ከታች ያሉትን  ሁለት የYouTube ቪዲዮዎች ብታዩ ይመረጣል።

⚫Telegram Premium እንዴት ማድረግ እንችላለን? ምን የተለየ ጥቅም አለው?
https://youtu.be/-yHOQoywkq0?si=vBoGrF5NXpqfl-tt

⚫በTelegram premium እንዴት Business ይሰራል?
https://youtu.be/YFgjiZGGcJY?si=6PZyoKHcYknTwkWS


Telegram በዛሬው ዕለት አዳዲስ update ለቋል።

Voice trimming
Voice record እያደረጋችሁ በመሀል የማይሆን ነገር ተናግራችሁ ቆርጣችሁ ማውጣት ከፈለጋችሁ Pause አድርጋችሁ trim ማድረግ ትችላላችሁ።

Direct message to channels
የቻናል owner ወይም አድሚኖችን በቀላሉ contact ማድረግ ትችላላችሁ።
አድሚኑ settings ውስጥ on ካደረገው ከቻናሉ ታች ላይ የmessaging icon ትመጣለች እሷን በመንካት መልዕክት ማስቀመጥ ይቻላል።

HD quality photo
ፎቶ ስትልኩ በHD quality መላክ ትችላላችሁ።

Split Long video for story
ረጅም Video story ማድረግ ከፈለጋችሁ telegram ራሱ ቪዲዬውን ቆራርጦ በpart story እንድታደርጉት ያስችላችኋል።

13k 0 5 8 199

የጃፓን ሳይንቲስቶች ከሁሉም የደም አይነት ጋር የሚስማማ ሰው ሰራሽ ደም መስራታቸው ተገለፀ።

ሰዎች የጤና ዕክል ገጥሟቸው ደም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ከሌላ ሰው ደም ለመውሰድ የደም አይነቶቹ መመሳሰል አለባቸው። ይህን ተመሳሳይ የደም አይነት በቀላሉ ማግኘት ስለማይቻል ብዙ ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉ።
ሰሞኑን በተሰማ ዜና ግን ጃፓናውያን ሳይንቲስቶች ከዚህ በኋላ በደም እጦት የሰው ልጅ በከንቱ ውድ ህይወቱን አያጣም ብለዋል። በNara Medical University የሚሰሩ እነዚህ ሳይንቲስቶች ደም ለሚያስፈልገው ማንኛውም ሰው የሚስማማ ደም መስራት ችለናል እያሉ ነው።

ይህ ደም የሚሰራው በሰውነት ውስጥ ፕሮቲን በመሸከም ኦክስጅን የሚያመላልሱ ሄሞግሎቢን ተብለው የሚጠሩ የደም ክፍሎችን አገልግሎት ከማይሰጥ የደም አይነት ውስጥ በማጣራት ሲሆን ይህም ከቫይረስ ነጻ በሆነና የደም አይነት በሌለው ቀይ የደም ህዋስ እንዲሸፈን ይደረጋል።

ይህ ሰው ሰራሽ ደም እስከ 2 አመት በroom temperature ምንም ሳይሆን መቀመጥ ሲችል በማቀዝቀዣ ውስጥ ከተቀመጠ ደግሞ እስከ 5 አመት ማገልገል ይችላል።

ፈጠራው በአሁኑ ሰአት ሙከራ ላይ ቢሆንም ተስፋ የሚሰጥ ውጤት ታይቶበታል ተብሏል። በ2030ም ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ ወደ ህክምና ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

✍️ይህን ፈጠራ እንዴት አያችሁት?
በተለይ በሀገራችን እናቶች በወሊድ ጊዜ ብዙ ደም ፈሷቸው ህይወታቸውን ያጣሉ ለዚህ ትልቅ ዕድል አይመስላችሁም?

@bighabesha_softwares


Samsung Phones.pdf
360.7Кб
ስልካችሁ ሳምሰንግ ከሆነ Android version እና One UI version ስንት ላይ እንደሚቆም የሚያሳይ ዝርዝር Document ከላይ ያለዉን pdf ከፍታችሁ ማየት ትችላላችሁ።


#Tech_tip

አብዛኞቻችን አንድን ቪድዮ/MP4 ፋይል ወደ ድምፅ/MP3 ፋይል ለመቀየር የተለያዩ አፕልኬሽኖችን ወይም ሶፍትዌሮችን እንጠቀማለን።

ነገር ግን ያለምንም ተጨማሪ መተግበሪያ በስልካችን ብቻ ቪድዮን ወደ ኦዲዮ መቀየር እንደምንችል ያውቁ ኖሯል?

ስልካችን ውስጥ ወደሚገኘው file manager ውስጥ ከገባን በኋላ መቀየር የምንፈልገውን ቪድዮ ጫን አድረገን ይዘን rename የሚለውን እንጫናለን (rename የሚል ከሌለ ጥግ ጋር ያለውን ሶስት ነጥብጣብ በመንካት ማግኘት እንችላለን።) ከዚያም ከስሙ መጨረሻ ላይ .MP4 የሚለውን አጥፍተን በ .MP3 እንተካዋለን።
ከዛ ቪዲዮው ወደ Audio ይቀየራል።

ለደህንነት ሲባል የአንድን file extension ከመቀየራችሁ በፊት copy አድርጋችሁ ሌላ ቦታ ማስቀመጥ አትርሱ።

©bighabesha_softwares


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
Telegram አካውንታችሁን ሀክ ልትደረጉበት የምትችሉበት መንገድ


በchina የሮቦቶች የኪክቦክስ ግጥሚያ ተካሄደ።

በአለማችን ለመጀመሪያ ግዜ የተካሄደው ይህ ውድድር እስከ 1.32 ሜትር ርዝመት እና እስከ 35 ኪሎግራም ክብደት ባላቸው ሮቦቶች መካከል ነው።

ተጋጣሚው ሮቦትም ነጥብ የሚቆጠርለት የተቃራኒውን ሰውነት አልያም ፊት ሲመታው ሲሆን አንድ ምትም አንድ ነጥብ ያሰጣል።

ተጋጣሚዎች ከወደቁ 5 ነጥብ የሚቀነስባቸው ሲሆን በ8 ሴኮንዶች ውስጥ ካልተነሱ ደግሞ 10 ነጥብ ይቀነስባቸዋል።

ሮቦቶቹን አሰልጣኞቹ remotly control የሚያደርጓቸው ሲሆን ይህም መድረክ ላይ በደንብ እንዲንቀሳቀሱ አስችሏቸዋል።

ውድድሩን በከፊል ትመለከቱ ዘንድ በሁለተኛው ቻናላችን ላይ አጭር video አስቀምጠንላችኋል። click here

©bighabesha_softwares


ስልካችሁ ላይ ፎቶ ካነሳችሁ በኋላ ብዙ ጊዜ የፎቶው File name የሚቀመጠው በቁጥር ነው።

ለምሳሌ 20241001_111509.jpg ቢሆን
ይህ ቁጥር ዝም ብሎ random ቁጥር ሳይሆን የሚነግራችሁ ፎቶው የተነሳበትን አመተ ምህረት ወር ቀንና ሰአት ነው።
ከላይ ለምሳሌ የተጠቀምነው ፎቶ የተነሳው በ2024 አ.ም በ10ኛው ወር በ01 ቀን ሲሆን ሰአቱም 11:15:09 ነው ማለት ነው።

ይህም ምናልባት ለረጅም ጊዜ የተነሳ ፎቶ ኖሯችሁ በስንት አመተ ምህረት እንዳነሳችሁት ካላወቃችሁ በዚህ መንገድ ማዎቅ ትችላላችሁ።

ይህ ግን iphone ስልኮችን አያካትትም።


እናስታውሳችሁ!!

Coding ለመማር እነዚህን ድረገፆች ተጠቀሙ።

w3schools.com
እንደ css, java script, Python የመሳሰሉ programming languages ላይ ገና ጀማሪ ከሆናችሁ በጣም ይጠቅማችኋል።

freecodecamp.org/
በሺህ የሚቆጠሩ ለጀማሪ የተዘጋጁ ቲቶሪያሎችን የምታገኙበት ድረገፅ ሲሆን ከቀላል እስከ ከባድ coding መማርም ያስችላችኋል።

kaggle.com/learn
pythone, ai, machine learning መማር ከፈለጋችሁ ይህንን ድረገፅ መጠቀም ትችላላችሁ።

https://leetcode.com/
የተለያዩ የcoding ጥያቄዎች እና challenges ያሉበት ድረገፅ ነው። ይህንን ድረገፅ የcoding እውቀት ያላችሁና ማማዳበር የምትፈልጉ በደንብ ተጠቀሙበት።

https://dev.to/
በርካታ ፕሮግራመሮችን የምታገኙበት ድረገፅ ሲሆን በተጨማሪም በርካታ ከcoding ጋር የተገናኙ topics ይዳሰሱበታል።

አስተውሉ!!
ማንኛውም ሰው የትኛውም የትምህርት ደረጃና የዕድሜ ክልል ቢሆን coding መማር ይችላል።

✍እናንተ ብዙ ጊዜ የምትጠቀሙት የትኛውን ነው? ሌሎች የምታውቋቸው አሪፍ ድረገፆችን በcomment አካፍሉን።

©bighabesha_softwares


ኢራናዊው ሃከር በአሜሪካ ከተሞች ላይ ባደረሰው የራንሰምዌር ጥቃት ጥፋተኛ ተባለ።

የ37 አመቱ ሲና ጎሊንጃድ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች (በተለይ ባልቲሞርና ግሪንቪል) ከ2019 እስከ 2024 የደረሰውን Robbinhood ransomware attack እንደመራ ፍርድቤት ቀርቦ አምኗል።

በዚህ ጥቃትም ከ19 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጉዳት ማድረሱን፣ የተለያዩ ከተሞች አገልግሎቶች መስተጓጎላቸውን፣ እጅግ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፎ መስጠቱንና በክሪፕቶከረንሲ የገንዘብ ዝውውር ማድረጉን የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስትር ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

ለዚህ ጥፋትም ፍርድቤት እስከ 30 አመት እስር እንደሚወስንበት ይጠበቃል።


Samsung የOne UI 8 beta version ይፋ አድርጓል።

በዚህኛው UI version የተካተቱ አዳዲስ updates ከታች የተዘረዘሩት ናቸው።

Productivity
🟢Easier file sharing with Quick Share
🟢Easily find downloaded files
🟢Redesigned Samsung Internet
🟢More convenient Al select

Multitasking
🟢Enhanced display support
🟢Enhanced split screen view

Reminder
🟢New Reminder interface
🟢New sample reminders
🟢Add reminders easily

Calendar
🟢Manage reminders in Calendar
🟢Add events quickly

Modes and routines
🟢New preset routines
🟢New routine actions

Samsung Health
🟢Running distance challenges
🟢Food recording reminders

Communication
🟢Improved profile cards
🟢Camera

Security and privacy
🟢Enhanced Secure Folder

Accessibility
🟢Pinch and zoom with the Assistant menu
🟢Control mouse actions with your keyboard
🟢Magnify your keyboard
🟢Easily pair Bluetooth hearing aids

More improvements
🟢Enhanced alarm groups
🟢Get quicker support
🟢Revamped weather visuals

ይህ beta version ለጊዜው የተለቀቀው ኮርያ፣ USA እንዲሁም እንግሊዝ ውስጥ ሲሆን የሚሰራውም በGalaxy S25 series ላይ ብቻ ነው።


Telegram 300 ሚሊዮን ዶላር cash ከX ሊቀበል መሆኑ ተሰማ።

የቴሌግራምን በፍጥነት ማደግና በህዝቡ ዘንድ እያገግኘ ያለውን ተቀባይነት ያስተዋለው ኤለን መስክ ከTelegram ጋር በመተባበር ለመስራት መወሰኑ ታውቋል።
ለዚህ ትብብር ቴሌግራም ከX 300 ሚሊዮን ዲላር ገንዘብ የሚያገኝ ይሆናል።

የX generative ai የሆነው grok ቴሌግራም ላይ access ማድረግ ተጀምሯል።

ከዚህ በተጨማሪ የxAI premium subscription በቴሌግራም አማካኝነት ሲሸጥ ከእያንዳንዱ ትርፍ 50% Telegram እንደሚወስድ ተዘግቧል።

ይህ ብቻ ሳይሆን Grok ለTelegram የተለያዩ AI related ፊቸሮችን የሚሰጥ ይሆናል።
ከነዚህ መካከል
⚫️Smart text editing
⚫️Document summarization
⚫️Fact checking
⚫️AI driven sticker generation

Telegram አካውንታችሁ premium ከሆነና official Grok ai ቴሌግራም ላይ መጠቀም ከፈለጋችሁ ይህን username ተጠቀሙ። @GrokAI


One UI 7 update ያላገኙ ስልኮችን የሚያገኙበት ወር
⚫Galaxy Tab S6 Lite (2024) – June
⚫Galaxy Tab Active 5 – June
⚫Galaxy Tab Active 4 Pro – June
⚫Galaxy Tab A9+ – June
⚫Galaxy Tab A9 – July
⚫Galaxy A55 – June
⚫Galaxy A54 – June
⚫Galaxy A53 – June
⚫Galaxy A35 – June
⚫Galaxy A34 – June
⚫Galaxy A33 – June
⚫Galaxy A25 – June
⚫Galaxy A16 – June
⚫Galaxy A15 – June
⚫Galaxy A14 – June
⚫Galaxy A05s – June
⚫Galaxy M53 – June
⚫Galaxy M33 – June
⚫Galaxy XCover7 – June
⚫Galaxy XCover 6 Pro – June

ነገር ግን ይህ schedule እንደየሃገሮች ሊዘገይ እንደሚችል ተገልጿል።

የስልካችሁ አይነት ምንድን ነዉ?

20.7k 0 0 229 108
Показано 20 последних публикаций.