💋💋💋ጠባሹ💋💋💋
🌹🌹🌹🌹🌹Brak Tube🌹🌹🌹🌹🌹
ቅዳሜ የቀን ቅዱስም እርኩስም ናት፤ ቅዳሜ በጣም ከምወዳቸው ቀኖቼ ውስጥ የመጀመሪያዋ ናት በእርግጥ ቀኑ እኛ ላይ ስልጣን የለውም እኛ የቀኑ ባለስልጣናት ሆነን ሳለን አንዳንዴ ቀኑ እንዲሰለጥንብን እናደርጋለን። ብዙ ጊዜ ቅዳሜዬን ፒያሳ ላይ ማሳለፍ ደስታን ይሰጠኛል ፒያሳ እና ቅዳሜ ለኔ አንድ አይነት ናቸው ሁለቱም የኔ ምርጦች ናቸው። ዛሬም እንደልማዴ ቅዳሜዬን ፒያሳ ለዚያውም አራዳ ላይ አድርጌያለሁ። ፒያሳ መቼም በካፌ ብዛት አትታማም አራዳ ደሞ ቆነጃጂት ሴቶች የሚገኙባቸው ብዙ ካፌዎችን ይዟል። እኔም አራዳ ላይ ካሉት ብዙ ካፌዎች በአንዱ ተገኝቻለሁ።
@brak_tube @brak_tube @brak_tube
ብዙ ጊዜ የፒያሳ ካፌዎች ሙሉ ናቸው አንዳንዴም ወንበር ማግኘት አበሳ ይሆናል እኔ ግን ባዶ ጠረንጴዛ ስላገኘሁ በጣም እድለኛ እንደሆንኩ እያሰብኩ በደስታ ቁጭ አልኩ፤ ማን ያውቃል ምን አልባት ወንበር ቦታ ያጣች አንዷ ቆንጅዬ አጠገቤ ተቀምጣ ቅዳሜዬን ታሳምርልኝ ይሆናል። አስተናጋጁ ወንበር ይዤ እንደተቀመጥኩ ወደኔ ፈጠን ብሎ መጣና ደስ በሚል ፈገግታ ሰላምታ ካቀረበልኝ በኋላ " ባህራን ምን ልታዘዝ" አለኝ። የቤቱ ደምበኛ ከመሆኔም በላይ ከአስተናጋጆቹ ጋር ጥሩ ቀረቤታ አለኝ። በኔ እምነት የትም ቦታ ሄደን ጥሩ መስተናገድ ከፈለግን አስተናጋጃችንንና የአስተናጋጃችንን ስራ ማክበር አለብን ፤ በተለይ እንደዚህ አይነት የመዝናኛ ቦታዎች በጥሩ ሁኔታ እራሳችንን ለማዝናናት ሄደን ባለመከባበራችንና ጥሩ የሆነ ግንኙነት ባለመፍጠራችን የራሳችንንም የአስተናጋጆችንም እንዲሁ በአካባቢያችን ያሉ ሰዎችን ቀን እናበላሻለን። ለአስተናጋጁ አበበ ሞቅ ያለ ሰላምታ በአፀፋው ሰጥቼ አንድ ቺዝ በርገር አዘዝኩና እሱ እስከሚደርስ የምወደውን የቤታቸውን ማኪያቶ አዘዝኩት ፤ እሱም ትዕዛዜን ተቀብሎ ሄደ። እሱ እንደሄደ ትንሽ ቆየት ብሎ አንድ ወፈር ያለ ድምፅ በትህትና " ይቅርታ ሰው ከሌለው መቀመጥ እችላለሁ? ቦታ አጥቼ ነው። " አለኝ እኔም ቆንጅዬ ሴት አጠምድበታለሁ ያልኩትን ቦታ ልቀመጥበት ስላለኝ በስጨት ብልም ትህትናውና ፈገግታው ብስጭቴን አስረሳኝና እንዲቀመጥ ጋበዝኩት። ፒያሳን ከምወድላት ነገሮቿ ውስጥ ብዙ ምሁሮችና በሳል አዕምሮዎች ይዛ ነው ምትገኘው። ብዙ ጊዜ ወንበር አጥተው ወይም ወንበር አጥቼ አብረን ከተቀመጥናቸው ትላልቅ እና ወጣት ሰዎች ጋር ግሩም እውቀት ተለዋውጠናል ብዙ ነገሮችም አሳውቀውኛል ይህ ሰውም ከነዛ አንዱ ይሆናል ብዬ አስቤም ነው እንዲቀመጥ የፈቀድኩለት ለነገሩ ትህትናውም ይሉኝታ ያስይዛል። ሰውዬው እውነትም እንዳሰብኩት ተጨዋችና አስገራሚ ሰው ነበር ትንሽ እንደተጨዋወትን ከፊትለፊታችን አንዱ ጠረንጴዛ ተለቀቀ ነገር ግን እኔም እንዲነሳ አልፈለኩም እሱም መነሳት አልፈለገም እንዲነሳ እንዳልፈለኩ ከፊቴ ተረድቶ መሰለኝ እሱም ዝም ብሎ ተቀመጠ። ወዲያው አስተናጋጁ አበበ
ያዘዝኩትን ማኪያቶ ይዞልኝ መጣና አብሮኝ ለተቀመጠውም ሰው ታዘዘለትና ሄደ። ትንሽ እንደተጨዋወትን አንዲት ልጅ ተለቆ ወደነበረው ቦታ በአጠገባችን ዳሌዋን ከግራ ወደቀኝ እያማታች ስታልፍ ሁለታችንም አፋችንን ከፍተን ቀረን ፤ ልጅቷ የለበሰችው ውሀሰማያዊ ሱሪና ሸሚዝ ቅርጿን አውጥቶ አሳይቶላታል።
ይቀጥላል....
ፀሀፊ ፦ Brak
በ Brak Tube ብቻ
ቻነላችንን ለወዳጆችዎ በማጋራት ቤተሰብነታችሁን አሳዩን 🙏
@brak_tube @brak_tube @brak_tube
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!! 💚💛❤
Comment @brak_s
Share & Join as @brak_tube