የ2017 ዓ.ም የረመዳን ጾምና ኢድ አልፈጥርን ምክንያት በማድረግ በኡመር መስጂድና ኢህሳን ፋውንዴሽን አስተባባሪነት በአዳማ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ 78 ሙስሊም ወገኖቻችን የበዐል ስጦታ በባንካችን ስም ተበርክቷል። በዝግጅቱ ላይ የእምነት አባቶች፣ ተቀዳሚ ደንበኞች፣ የሼር ባለቤቶችና በከተማው የሚገኙ የሁሉም ቅርንጫፎቻችንና የጽ/ቤት ተወካይ ሰራተኞች ተገኝተዋል። በተመሳሳይ አርሲ ዞንና ምስራቅ ኢትዮጲያ ላይም በተመረጡ ከተሞች ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ይካሄዳሉ።