ሰው ጊዜውን ይሆናል፣ የሚኖረው ከሰው ጋ በህብረት ነውና ስለሚጠበቁበት ኃላፊነቶች ማስተዋል ሲጀምር የጊዜውንና ጸጋውን ውድነቶች ይረዳል። ጊዜውን መሆንን ይንከባከባል፣ የተቸረውን የምናብ አቅም ለህይወቱ እርካብ እንዲጸናበት የኑሮው ግምበኛ ይሆናል።
ይህን መድረስ ለመበቃት ግን ሰው መብቴ ከሚለው የማረጠ አፍላ ሀሳቡ አልፎ መገኘት አለበት። ግዴታየ ብሎ ሲያስብ፣ ከኃላፊነቱ ማሰብን ሲደርስ ያኔ ጥሩ የህይወት ልክ ይደርሳል። ሊበቃም ንጋቱን ያያል።