Фильтр публикаций






አበባ ደሳለኝ "ሙሽራዬ ቀረ"
በ1999 ዓ.ም የተሰራው ይህ አልበም አበባ በግል የሰራችው የመጀመሪያ ስራዋ ነበር:: ነገር ግን በጋራ ከትዕግስት ፋንታሁን ጋር የሰራችው አልበም ነበራት:: በሙሽራዬ ቀረ አልበም ጂክሳ እና አሸብር ማሞ በሙዚቃ ቅንብር ተሳትፈውበታል:: ግጥም እና ዜማ አብርሽ ዘ ጌት እና እራሷም አበባ ሰርተውታል:: በግጥም ደረጃ አዳዲስ ሀሳቦችን የያዘው ይህ አልበም ብዙ ጉዳዮችን አንስቷል:: ዳዊት ወንጭፍህን : ሙሽራዬ ቀረ : አለመቅናትህ ያስቀናኛል የሚሉት ይጠቀሳሉ:: በረከት በሚለው ስራዋም ስለ ፍቅረኛዋ በሚገርም ሁኔታ ሙዚቃ ሰርታለች:: አንድ ስራም የሂሩት በቀለ "ቤቱ ቤቴ በላይ" ብላ በሚመስጠው ድምጿ ተጫውታለች::

ዛሬ ምሽት ይህን ምርጥ የአልበም ስራ እናዳምጣለን:: ዝግጁ ናችሁ ቤተሰቦቻችን? ኮመንት ላይ ፃፉልን ❤️🙌

@cassettemusiq






ምንአሉሽ ረታ "ብያለሁ"
በ2001 ዓ.ም ለህዝብ የደረሰው ይህ አልበም በጥበቡ ወርቅዬ ኢንተርቴይመንት አሳታሚ እና አከፋፋይነት ነበር:: ሙሉ አልበም ሙዚቃ ቅንብር በኤልያስ መልካ ተሰርቷል:: ግጥም እና ዜማ ላይ ማን አንደተሳተፈ መረጃው የለንም: መረጃ ያለው ያካፍለን:: በውስጡ 12 ትራኮችን የያዘው ይህ አልበም መራክን አልወድም እና እሌላ ምሳፍር የተሰኙ ተደማጭነትን ያገኙ ስራዎች ነበሩት::

ይህ ምርጥ የሆነ የኤልያስ እና ምንአሉሽ ጥምረት ዛሬ ምሽት እናዳምጣለን:: አብራችሁን ናችሁ? ❤️🙌

@cassettemusiq





Показано 8 последних публикаций.