የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርካቶ፣ ጉለሌና ኮልፌ ዲስትሪክቶች በፊሊጶስ ዘላቂ ማረፊያ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ችግኝ ተከሉ፡፡
***
ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ዲስትሪክቶች አማካኝነት ባካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የመጨረሻዎቹ 3 ዲስትሪክቶች የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞቹ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ፊሊጶስ ዘላቂ ማረፊያ በሚባለው ቦታ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ችግኝ ተክለዋል።
በዚሁ ጊዜ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ባንኩ በተለያዩ አካባቢዎች የሚተክላቸውን ችግኞች የእንክብካቤ ስራ ከየአባባቢው ነዋሪዎች ጋር እንደሚያከናውን ገልፀው በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በፈቃዳቸው ለተሳተፉት የአካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
የመርካቶ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሸምሱ ባርጌቾ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት እንደ ችግኝ ተከላ ያሉ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ ተግባራት ላይ እንደሚሳተፍ በመግለፅ በዛሬው መርሃ ግብርም ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች በስፍራው መተከላቸውን ጠቁመዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ እንደ ችግኝ መትከሉ ሁሉ በችግኝ እንክብካቤና ጥበቃ ስራ ላይም ከባንኩ ጎን በመቆም የተተከሉት ችግኞች ለፍሬ እንዲበቁ እንዲያግዝ ዳይሬክተሮቹ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።
በባንኩ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ብቻ 5ዐሺ ችግኞች በባንኩ የተተከሉ ሲሆን ከአዲስ አበባ አስሩ ዲስትሪክቶች በተጨማሪም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ከአዲስ አበባ ውጪ በሚገኙ ሁሉም ዲስትሪክቶች እየተከናወነ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!