TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
Russian
Язык сайта
Russian
English
Uzbek
Вход на сайт
Каталог
Каталог каналов и чатов
Поиск каналов
Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов
Рейтинг чатов
Рейтинг публикаций
Рейтинги брендов и персон
Аналитика
Поиск по публикациям
Мониторинг Telegram
Ethiopian Customs Clearing Agents
1 Sep 2023, 20:18
Открыть в Telegram
Поделиться
Пожаловаться
🏵የውጭ ምንዛሪ ክልከላ ውሳኔ ከመተላለፉ አስቀድሞ በተሰጠ የባንክ ፈቃድ እና የባንክ ፈቃድ ማራዘሚያ ተሸከርካሪዎች ወደ አገር እየገቡ በመሆኑ አስመጪዎች ዕቃቸውን አጠቃለው _ እንዲያስገቡ በቂ ጊዜ የተፈቀደ ቢሆንም በተፈቀደው ጊዜ አጠቃለው ባለማስገባታቸው ክልከላ የተደረገባቸው ተሸhርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ በቁጥር 4/0051/16 በቀን 11/12/2015 ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡
ሆኖም ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ወደ አገር ገብተው ትራንዚት አጠናቀው በተለያዩ ጉምሩክ ክሊራንስ ስነ-ስርዓት ሃደቶች ላይ የሚገኙ በተመላሽ ኢትዮጵያውያን ስም ተመዝግበው አገር ውስጥ የገቡ ፤ በመልቲ ሞዳል ስርዓት በመግባት ላይ እያሉ በመግቢያ በሮች የሚገኙ ተሸከርካሪዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ኤምባሲዎች፣ እና መንግስታዊ መ/ቤቶች በቀጣይነት ወደ አገር የሚያስገቧቸው ተሸከርካሪዎች በጉምሩክ በኩል የሚስተናገዱበት አግባብ በግልጽ መወሰን አስፈልጓል::
1. የውጭ ምንዛሪ ክልከላ ከመደረጉ በፊት በተሰጠ የባንክ ፈቃድ፤ በባንኮች በኩል በተሰጠ ህጋዊ የባንክ ፈቃድ መጠቀሚያ ጊዜ ማራዘሚያ እና ህጋዊ ስልጣን በተሰጠው አካል በተሰጠ ፈቃድ ወደ አገር ገብተው ትራንዚት ያጠናቀቁ እና በክሊራንስ ሃደት ላይ የሚገኙ ተሸከርካሪዎች በተመለከተ አስፈላጊው ቀረጥና ታክስ ተከፍሎ ወይም አግባብ ባለው አካል በተሰጠ የቀረጥና ታክስ ነጻ ፈቃድ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ተፈፅሞባቸው እንዲስተናገዱ እንዲደረግ፤
2. በተመላሽ ኢትዮጵያዊ ስም አገር ውስጥ ገብተው በቅ/ጽ/ቤቶች የሚገኙ ተሸከርካሪዎች በተመለከተ በኮሚሽኑ በኩል በተደረገ ጥናት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ቀረጥና ታክስ ከፍለው አንድ ተሸከርካሪ ወደ አገር የማስገባትን መብት በመጠቀም ህጋዊ መብት ለሌላቸው አካላት ተሽከርካሪን ወደ አገር እያስገቡ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም ይህ ድርጊት ህጋዊ አሰራሩን ያልተከተለ ስለሆነ በተመላሽ ኢትዮጵያዊያን ስም ተመዝግበው አገር ውስጥ የደረሱ ተሸከርካሪዎች በስማቸው የተመዘገቡ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን በአካል እንዲቀርቡ እየተደረገ ዊዝሆልዲንግ ታክስን ጨምሮ የተሽከርካሪውን ሙሉ ቀረጥና ታክስ መክፈላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪነት የቀረጥና ታክሱን 10 በመቶ ቅጣት እንዲከፍሉ እየተደረገ እንዲስተናገዱ ተወስኗል
3. በመልቲ ሞዳል ስርዓት በመጓጓዝ ላይ ሆነው ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት በትራንዚት ሃደት ላይ ሆነው በመግቢያ በር በሚገኙ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ተሸከርካሪዎችን በተመለከተ ወደ መዳረሻ ጣቢያ እንዲጓጓዙ ሆኖ እንደ አግባብነቱ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1 እና 2 በተወሰነው አግባብ እንዲስተናገዱ ተወስኗል፤
4. የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ ኢምባሲዎች እና በልዩ ሁኔታ በኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ እና በጉምሩክ ኮሚሽን በህግ አግባብ በልዩ ሁኔታ ፈቃድ አግኝተው ወደ አገር ያልገቡ ተሸከርካሪዎችን በተመለከተ እገዳው የማይመለከታቸው መሆኑ ታውቆ ትራንዚት መፍቀድን ጨምሮ በቀጣይነት የጉምሩክ አገልግሎት እንዲያገኙ ተወስኗል፡
Ethiopian Customs Clearing Agents
Great Interesting Stuff Here!!
25.3k
0
92
34
×