ፋይዳን ለፖስፖርት
ከሰኔ 1 ፣ 2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያን ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ዋና ሰነዶች ውስጥ በማካተት አገልግሎት ለመስጠት ያስችል ዘንድ ከኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
@ICS ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል።
በመሆኑም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ የፋይዳ ልዩ ቁጥራቸውን በመያዝ ፣ QR ኮዱን በወረቀት አትመው ፣ ዲጂታል ኮፒውን በ "Fayda ID” application በኩል ይዘው ወይም ትክክለኛውን QR የያዘ ሌላ አማራጭ ተጠቅመው ይዘው በመምጣት ብቻ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
አገልግሎቶች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በመተሳሰራቸው አንድ ወጥ ደረጃ ያለው እና የተናበበ መረጃ በብሔራዊ ደረጃ እንዲኖረን በማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ሙሉ መግለጫውን
https://ics.gov.et/news/passport-services-require-fayda/ ላይ ያገኙታል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram:
https://t.me/Ethiopia_ICS