🔖የሚዲያ ሱስ……
የጫት ሱስ አለ። የሲጋራ እንዲሁም የሽሻ። በጉዳቱ ከነዚህ የማይተናነስ አንድ ከባድ ሱስ አለ። እሱም የቲክቶክ የዩቱብና የፌስቡክ ሱስ። ሱስ በባህሪው ይስባል። እንዳትላቀቀው ያደርጋል። ለትንሽ ጊዜ ካልተወሰደ ወይም ካልተገኘ ይጨንቃል። የሚዲያ ሱሰኞችም ባህሪ እንዲሁ ነው። ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እዛ ላይ ይጣዳሉ። ለአንድ ቀን ከሱ ርቀው መዋል አይችሉም። ገንዘባቸው፣ ጊዜያቸውና አቅላቸው ለማይረባ ነገር መስዋእት ያደርጋሉ። ቁርአን አይቀሩ ቂርአት የላቸው ዚክር ኢባዳ አያደርጉ በቃ አይናቸው እስኪያማቸው እዛ ላይ ያፈጣሉ። እንቅልፋቸው ራሱ ባግባቡ ስለማይተኙ ፋዞ ዝንጉ ተነጫናጭ ሆነው ይውላሉ። ይህ ነገር የጤና እክል ከማስከተሉም ጋር አሔራዊ ኪሳራም አለው። በዛላይ አብዘሀኛው ሰው እዛ ላይ የሚያየው ጤነኛ ነገር አይደለም። ሙዚቃ፣ ፊልም፣ የዘር ወሬ፣ ያማይረባ ዜና፣ የተገላለጡ ሴቶችና ሌሎችም ብዙ ጥፋቶች ይመለከታሉ። ለዛም ነው ድንገት ሰው ሲመጣባቸው ደንግጠው የሚዘጉት። በዚህ ሁሉ አላህ ፊት ተጠያቂ ናቸው።
ወጣትነትህ በኢልም በኢባዳ በሀላል ስራ አሳልፈው። በዋዛ ፈዛዛ በቀልድ በጨዋታ አትግደለው።
ሀራም ነገር የምታይበት ስልክ፣ ለዛ ብለህ የምትሞላው ረሲድ፣ የምታባክነው ጊዜ በዚህ ሁሉ ነገ አላህ ፊት ቆመህ ትጠየቃለህ። የዛኔ መልስህ ምን ይሁን?