Doctor Tena


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ጠቃሚ የጤና ምክሮች!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций
































በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,636 የላብራቶሪ ምርመራ 176 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,521 ደርሷል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 60 ደረሰ!

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 28 (17 ከጤና ተቋም እና 11 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን አንድ (1) ናሙና የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በተጨማሪ 2 በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ (60) ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ60 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ19 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

3. የ32 ዓመት ወንድ የአማራ ክልል ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

@TenaET






በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 55 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የስምንት (8) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 55 ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ34 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረች።

3. የ45 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

4. የ40 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረች።

5. የ90 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

6. (እድሜው ያልታወቀ) ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

7. የ50 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

8. የ45 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

@TenaET / https://tena.et/update


በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 3,166 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,644 የላብራቶሪ ምርመራ 268 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,166 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 177 ወንድ እና 91 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 267 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዱ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 232 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 12 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 8 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 6 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ፣ 2 ሰዎች ከአፋር ክልል እንዲሁም 1 ሰው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አርባ አራት (44) ሰዎች (28 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከአማራ ክልል፣ 4 ከአፋር ክልል፣ 3 ከኦሮሚያ ክልል እና 3 ከሐረሪ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 495 ደርሷል።

@TenaET / https://tena.et/update

Показано 20 последних публикаций.

3 253

подписчиков
Статистика канала