** የወባ በሽታ ስርጭት**
የወባ በሽታ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ በሆኑ የአየር ፀባይና አካባቢዎች በቀላሉ ሊስፋፋ ይችላል፡፡ በተለይ ቆላማ በሆኑ ቦታዎች ለወባ መስፋፋት ምቹ የሆነ ሙቀትና የአየር ርጥበት ያለባቸው ሲሆን
👉 በዝናብ ምክንያትና አንዳንዴም በድርቅ ወቅት ወንዞች በመቆራረጣቸው የተነሳ
👉 በየአካባቢው ውሀ ያቋቱ ስፍራዎች መበራከትና
👉 በአግባቡ ያልተያዙ ረግረግ መሬቶች መፈጠር እንዲሁም ከደጋማው ለወባ ተጋላጭ ካልሆኑ አካባቢ ወደነዚህ ቆላማ ስፍራዎች የህብረተሰብ እንቅስቃሴ መጨመር ለወባ መስፋፋት ምቹ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
👉 የወባ በሽታ መከላከያ መንገዶች
👉 ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ስራዎችን መስራት
👉 የጸረ ትንኝም ሆነ የጸረ ዕጭ ኬሚካል መጠቀም
👉 በኬሚካል የተነከረ አጎበር ሁል ጊዜ መጠቀም
👉 የወባ በሽታ ምልክቶች
በትንኝ ንክሻ ወቅት ተሀዋሲው ወደ ደም ዘልቆ በመግባት የደም ሴሎችን በማጥቃትና በሌሎች የውስጥ አካላት ላይ ጉዳት በማድረስ በሽተኛውን ለከፋ ጉዳት ብሎም ለሞት ይዳርጋል፡፡
አንድ ሰው የወባ በሽታ አምጭ ተህዋሲውን በያዘች ትንኝ ከተነከሰና የበሽታ ተሃዋሲ በደሙ ውሰጥ ከገባ በኋላ በሽታው በደም ዝውውር አማካይነት በጉበቱ ውስጥ ይገባል፡፡ ጉበት ውስጥ ገበቶ ተራብቶ አስፈላጊውን ሁኔታዎችን ባሟላ ከ7- 14 ባሉት ቀናት ውስጥ አንድ ሰው የበሽታውን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡ ከእነዚህም ምልክቶች ውስጥ
👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣
👉 ብርድ ብርድ ማለት፣
👉 ማንቀጥቀጥ፣
👉 የመገጣጠሚያ አካላት ህመም፣
👉 ቁርጥማት፣
👉 የራስ ምታት፣
👉 የምግብ ፍላጎት መቀነስና
👉 ማስታወክ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ምልክቶቹ በየ2 ቀኑ እየተመላለሱ የሚያሰቃዩ ሲሆን በተለይም ህመሙ ኘላዝሞዲየም ፋልሲፓረም በተባለው የበሽታ አምጭ ተህዋሲ የመጣ ከሆነና በቂ ህክምና ካልተገኘ ከዚህ በከፋ ሁኔታ ማለትም እንደ ራስን መሳት፣ እንደሚጥል በሽታ አይነት መንፈራገጥ፣ እንዲሁም በከፋ ደም ማነስና የጉበት፣ የኩላሊትና የሳንባ ጉዳት ሊያደርስና ለሞት ሊዳርግም ይችላል፡፡
እነዚህን ምልክቶች ካዩ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ!
አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።
ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ
አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦ https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC