መዝሙር ሰንበት ተዐቢ ነሐሴ ፳፯ እና ፳፰
(በ፭) ሰንበት ተዐቢ እምኵሉ ዕለት ሰንበት ተዐቢ እምኵሉ ዕለት ወሰብእ ይከብር እምኵሉ ፍጥረት (ሰ) አዕበያ ኖኅ በውስተ ታቦት አብርሃም አክበራ በውስተ ምሥዋዕ (ሰ) አዘዞሙ ሙሴ ለሕዝብ ያክብሩ ሰንበተ በጽድቅ (ሰ) አዝዞሙ እግዚኦ ለደመናት ያውርዱ ዝናመ ዲበ ምድር ሰንበት ተዐቢ እምኵሉ ዕለት ወሰብእ ይከብር እምኵሉ ፍጥረት።
ትጕም፦
ከዕለት ሁሉ ሰንበት ትከብራለች ከፍጥረት ሁሉ ሰው ይከብራል ኖኅ በመርከብ ውስጥ አገነናት አብርሃም በመሥዋዕት አከበራት ሙሴ ሰንበትን ያከብሩ ዘንድ ጉባኤውን አዘዛቸው አቤቱ በምድር ላይ ዝናምን ያዘሙ ዘንድ ደመናትን እዘዛቸው ከዕለት ሁሉ ሰንበት ትከብራለች ከፍጥረት ሁሉ ሰው ይከብራል።
የዕለቱ ምንባባት፦
ዕብ ፯፥፭ - ፍ፤
ያዕ ፪፥፲፬ - ፍ፤
ግብ ፯፥፩ - ፱፤
ወንጌል፦ ሉቃ ፲፪፥፲፮ - ፳፯፤
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ
የዕለቱ ምስባክ፦
ወሐመልማለ ለቅኔ እጓለ እመሕያው፤
ዘይሁቦሙ ሲሳዮሙ ለእንስሳ፤
ወለእጕለ ቋዓት እለ ይጼውዕዎ። መዝ ፻፵፮፥፱፤
ትርጕም፦
ልምላሜውን ለሰው ልጆች አገልግሎት የሚያበቅል፤
ለእንስሳትና ለሚጠሩት ቍራዎች ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው።
ምሥጢር፦
እህሉን ተክሉን የሚያበቅል እሱ ነው ያንን እየተመገበ በሥጋ በነፍስ ለእግዚአብሔር እንዲገዛ፤ አንድም ለሰው ለሚገዛ ለእንስሳ ልምላሜውን የሚያበቅል እሱ ነው፤
ለእንስሳት ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው በእንስሳ ሁሉን መናገር ነው፤
ለሚለምኑት ለዕጕለ ቋዓት - ለቍራዎች ልጆች ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው፤ እሱ ባወቀ ይለምኑታልና እንዲህ አለ፤ አንድም ለእለ ኢይጼውዕዎ ይላል ለማይለምኑት ለዕጕለ ቋዓት ምግባቸውን የሚሰጣቸው እሱ ነው። ቋዕ/አሞራ ሲወለድ ፍህም መስሎ ይወለዳል እናት አባቱ ምን ጉድ ተወለደብን ብለው ጥለዉት ይሄዳሉ ሲርበው ጧ ጧ እያደረገ አፉን ይከፍተዋል ተሐዋስያን ርጥበት ሲሹ ይገባሉ ግጥም አድርጎ ይዞ ይመገባቸዋል። አንድም ተሐዋስያን ሲያልፉ በእስትንፋሱ እየሳበ እስከ አርባ ቀን ድረስ ይመገባቸዋል ከአርባ ቀን በኋላ ጸጕር ያበቅላል በመልክ ይመስላቸዋል ተመልሰው መጥተው ያሳድጉታልና እንዲህ አለ።