መዝሙር ዘወርኃ ጳጉሜን ከመ እንተ መብረቅ
(በ፪) ከመ እንተ መብረቅ ዘይወጽእ እምጽባሕ ወያስተርኢ እስከ ዓረብ ከማሁ ምጽአቱ ለወልደ እግዚአብሔር ምስለ ኃይለ ሰማያት በንጥረ መባርቅት (ከ) ምስለ አእላፍ መላእክት ወኵሎሙ ሊቃነ መላእክት (ከ) አክሊለ አክሊላት ዲበ ርእሶሙ ለካህናት።
ትርጕም፦
መብረቅ (ፀሐይ) ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንዲታይ የሰው ልጅም አመጣጡ እንዲሁ ነው። ከሰማይ ኃይላት ጋር በመባርቅት ብልጭታ። ከአእላፍ መላእክትና ከሊቃነ መላእክት ሁሉ ጋር። የአክሊላት አክሊል በካህናት ራስ ላይ አለ።
የዕለቱ ምንባባት
፩ቆሮ ፩፥፩ - ፲፤
፪ጴጥ ፫፥፲ - ፍጻሜ፤
ግብ ፱፥፩ – ፲፤
ወንጌል፦ ሉቃ ፲፯፥፳፪ - ፍጻሜ፤
ከቁጥር ዐሥራ አንድ እስከ ሃያ ሰባት የሚያዝ ግጻዌም አለ።
ቅዳሴ፦ ያዕቆብ ዘሥሩግ (ተንሥኡ)
የዕለቱ ምስባክ፦
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ፤
ወአምላክነሂ ኢያረምም፤
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። መዝ ፵፱፥፫፤
ትርጒም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፤
አምላካችን ዝም አይልም፤
እሳት በፊቱ ይነዳል።
ምሥጢር፦
እግዚአብሔር በሰባ ዘመን በረድኤት ተገልጦ ይመጣል፤
መጥቶም ዝም አይልም በበጎዎቹ አድሮ ይፈርዳል አንድም በበጎዎቹ ካህናት አድሮ ክፉዎችን ካህናት ይዘልፋል፤
እሳት በፊቱ ይነዳል ማለት ክፉዎች የሚጠፉበትን መቅሠፍት መናገር ነው፤
አንድም እግዚአብሔር አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም በሥጋ ማርያም ይገለጣል፤
መጥቶ ዝም አይልም ወንጌልን ያስተምራል አንድም አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን - ጻፎችና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ እያለ ይዘልፋል
አይሁድ የሚጠፉበት መቅሠፍት በፊቱ ነው፤
አንድም በዕለተ ምጽአት የተወጋበትን ኲናት/ጦር የተቸነከረበትን ቀኖት አስይዞ ይመጣል፤
ጻድቃንን ንዑ ኀቤየ ብሎ ይጠራል ኃጥአንን ሑሩ እምኔየ ብሎ ያሰናብታል፤
ጻድቃን የሚድኑበት ሕይወት ኃጥአን የሚቀጡበት መቅሠፍት በፊቱ አለ።
መልእክት፦
እግዚአብሔር በግልጥ በሚመጣ ጊዜ እያንዳንዱ እንደሥራው ፍዳውን ይቀበል ዘንድ በእግዚአብሔር እሳታዊ ዙፋን ፊት ይቆማል። የጸና ሃይማኖትና የቀና በጎ ምግባር ያለው በቀኝ ቆሞ የምስጋና ቃላትን ሰምቶ ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀለትን መንግሥተ እግዚአብሔር ይወርስ ዘንድ ሥልጣን ሲሰጠው በዚህ ተቃራኒ ያለ ሁሉ ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ወደተዘጋጀ ዘለዓለማዊ እሳት ይጣል ዘንድ ጽኑዕ የሆነ አምላካዊ ትእዛዝ ይሰማል።
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው አሜሃ መሐረነ መሀከነ ወተሣሃለነ - ያን ጊዜ ማረን ራራልን ይቅርም በለን እንዳለ ዛሬም በቤተ መቅደሱ ተሰብስበን ማረን ይቅር በለን እንበለው። በተለያየ ምክንያት የሸፈተውንና የሻከረውን ልባችንን በቃሉ እየመለስንና እያነጻን በንስሐ ሕይወት እየተመላለስን መንፈሳዊ ቤት ለመሆን እንሠራ። መተርጉማን ሊቃውንት በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ የሚለውን ሲያብራሩ በደላችንን የምታርቅልን እንደ ይቅርታህ እንደ ቸርነትህ ብዛት ነው እንጂ እንደ በደላችን አይደለም እንደ በደላችን ቢሆን በዝቶ በተደረገብን ነበር አንድም ሥጋህን ደምህን የምትሰጠን እንደ ይቅርታህ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይደለም እንደ በደላችን ቢሆን ባልተገባን ነበር እያሉ ነው። እኛም ይህንን ግሩም ምሥጢር ከልባችን ብንረዳውና አንደበታችንንም ልባችንንም አንድ አድርገን ድምጻችን እስከ ሰማይ ድረስ እንደራሄል ድምጽ እንዲሰማ አድርገን ብንጮህ ለችግሮቻን ሁሉ መፍትሔ በመጣልን ነበር።
የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል እንደተባለ እልከኛ በሆነ ልብ መጓዛችን ለእኛው እንዲብስብን ማድረግ መሆኑን መገንዘብ አለመቻላችንና በየራሳችን መንገድና ፍላጎት ብቻ መሄዳችን የዓመታት ለውጥ ብቻ እንጂ የምንፈልገውንና የሚጠቅመንን ለውጥ ማምጣትና ማግኘት አላስቻለንም። ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤል በክፉ መንገድ መሄዱን እስካላቆመ ድረስ የሚገጥመውን ሲናገር እንዲህ ብሏል። "እግዚአብሔር በዕብደት በዕውርነት በድንጋጤም ይመታሃል በቀትርም ጊዜ ዕውር በጨለማ እንደሚርመሰመስ ትርመሰመሳለህ መንገድህም የቀና አይሆንም በዘመንህም ሁሉ የተጨነቅህ የተዘረፍህም ትሆናለህ የሚያድንህም የለም" ዘዳ ፳፰፥፳፰
ሊሆን የሚገባውን አንደበታችን ይናገረዋል ስሕተት ሠሩ የምንላቸውን ሁሉ እንተቻለን እናወግዛለን ግን እኛው ደግሞ ያንኑ ስሕተት አሻሽለን እንደግመዋለን "በዘመንህም ሁሉ የተጨነቅህ የተዘረፍህም ትሆናለህ" ማለት ይሄ ይሆን? እንጨነቃለን መፍትሔ ግን የለም እንጮሃለን መልስ ግን የለም እንዘምራለን በረከት ግን ከቀን ወደቀን እየራቀን ነው...። ብፁዕ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነገን ሲያጠነቅቀን እንዲህ አለ። "መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና" ፪ቆሮ ፭፥፲
በዘወትር ጸሎታችን "አመ ዳግም ምጽአቱ ኢያስተሐፍረነ - በዳግም ምጽአቱ ጊዜ እንዳያሳፍረን/አያሳፍረን" እያልን የምንጸልየውን ጸሎት ሰምቶ እንዳያሳፍረን ማለትም አላውቃችሁም እንዳይለን ይልቁንም ንዑ ኀቤየ ቡሩካኑ ለአቡየ እንዲለን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።