🌼🌼ከምግብ በኋላ ለምን በእንተ አቡነ አቢብ እንላለን?🌼🌼
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ›› ብሎ ከምግብ ብኋላ የተማፀነውን እምርልሃለው...
እነሆ ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ምእመናን በሚቀምሱት የዕለት ምግብ አማካኝነት በነፍስም በሥጋም እንዲድኑ አስገራሚ የምሕረት ቃልኪዳን እንደተቀበሉ የሚናገር የገድል ተአምራታቸው ይህ ነው፡- ብዙዎች ስማቸውን ጠርተው በሚቀምሱት ምግብ አማካኝነት ከተለያዩ በሽታዎች የተፈወሱ አሉ፡፡ ይህ ቃልኪዳናቸው ለኹላችን ይደረግን ዘንድ ከመመገባችን አስቀድሞ የእግዚአብሔርን ስም እንጥራ (አቡነ ዘበሰማያትን ማለቱ ነው፡፡) ከተመገብን በኋላም የዕለት ምግባችንን ስለሰጠን እግዚአብሔርን እናመስግን፡፡ ዘወትር ከተመገብን በኋላ ሦስት ጊዜ ‹‹ስለ ወዳጅህ ስለ አቡነ አቢብ›› እያልን ሦስት ጊዜ እንቅመስ፡፡ አስቀድሞ ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ አቢብ ተገልጦላቸው ‹‹…ወዳጄ አቢብ ሆይ! የሰውን ልጅ ለማዳን የተቀበልኩትን ሕማማተ መስቀል እያሰብህ ይህንን ሁሉ ገድል ፈጽመሃልና ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ ንዑድ ክቡር ቅዱስ አባታችን አቡነ አቢብም ‹‹ጌታዬ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መቼም ሰው ሁሉ ሳይመገብ አይውልም አያድርምና በተመገበ ጊዜ ስሜን ጠርቶ የተማጸነውን ማርልኝ›› አሉት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አባታችን አቡነ አቢብ ለሰው ልጆች ያላቸውን ፍቅር ካደነቀ በኋላ ‹‹…ከማዕድ በኋላ ስብሃት ተብሎ የተረፈውን ‹በእንተ አቢብ› ብሎ ሦስት ጊዜ የተመገበውን ሰው ሁሉ እምርልሃለሁ›› በማለት ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ያልተጠመቀ አረማዊ አሕዛብም እንኳን ቢሆኖ "ስለ አቡነ አቢብ" ብሎ ከተማጸነ ጌታችንን ያንን ሰው ወደቀናች የእምነት መንገድ ሳይመራወና በንስሓ ሳይጠራው በሞት እንደማይወስደው ለአባታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ለማዳን ትንሽ ምክንያትን የሚፈልግ ያለ ምክንያትም የማያድን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ እስከዘላለም ድረስ ይክበር ይመስገን!
ሰው ተመግቦ እንኳን መዳን እንዲችል ይህን ድንቅ ቃልኪዳን ለአባታችን ሰጥቷቸዋልና በየቀኑ በዚህ ቃልኪዳን እንጠቀምበት፡፡ ተመግበን ከጨረስንና ስብሃት ካልን በኋላ ሦስት ጊዜ ‹‹በእንተ አቡነ አቢብ›› ብለን እንቅመስ፡፡ በምናቀርበው የስንፍና ምክንያት ለማመሰገን ጊዜ ብናጣ እንኳን ቢያንስ ከተመገብን በኋላ ከስብሃት ቀጥሎ ሦስት ጊዜ በመቅመስ ‹‹በእንተ አቡነ አቢብ›› ብንል እግዚአብሔርን በቀን ሦስት ጊዜ ማመስገን ቻልን ማለት ነው፡፡ ከጻድቁም ቃልኪዳን ተካፋዮች ሆንን ማለት ነው፡፡ በግእዝ ስብሃት ማለት የማንችል ሰዎች ካለን ደግሞ በአማርኛው የዘወትር ጸሎትን ክፍል ላይ የምናገኘውን (‹‹ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድ ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፣ ለእመቤታችን ማርያም ምስጋና ይገባል፣ ለክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል፣ ይህን ኅብስት ላበላን፣ ይህንን ጽዋ ላጠጣን፣ ምግባችንና ልብሳችንን ላዘጋጀን፣ ሀጥያታችንንም ሁሉ ለታገሰልን፣ ክቡር ደሙን ቅዱስ ስጋውን ለሰጠን፣ እስከዚችም ሰአት ላደረሰን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል፣ ለወለደችው ለማርያም ምስጋና ይገባል፣ ለክቡር መስቀሉ ምስጋና ይገባል ለዘለአለሙ አሜን›› እያልን እናመስግን።
በጥቅምት 25 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት ጻድቁና ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ከቃልኪዳናቸው ረድኤት በረከት ይክፈሉን!
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››
(ምንጭ፡- ደብረ ሰላም ቃጭልቃ አቡነ አቢብ ገዳም ያሳተመው ገድለ አቡነ አቢብ፣ ገጽ 105)
@enabib