🌻🌻🌻🌻🌻
ምጽዋት
የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ፡፡ የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ፡፡ አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው፡፡ የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፡፡ ታድያ ወንድምህስ? የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነው? መሆን የለበትም፡፡ ማስቀመጫ እንዳጣ መጣያ አታርገው ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው፡፡ ከምትለብሳቸው ሁለት ልብሶች አንዱን ስጠው፡፡ የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው፡፡ ለአንተ የምትመኘውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ፡፡ “ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው” ያለውን የእግዚአብሔር ቃል መለስ ብለህ አስብና፣ የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ፡፡ ከዚሁ ጋር አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋዕት እንዴት እንደነበረ አስብ፡፡ “አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፡፡” (ዘፍ 4፣4) ለምን መረጠለት? ብትል ፣ ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ስላቀረበ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ 4፣34-35 ላይ ሠፍሮ የሚገኘውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን
ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ፡፡ ክብርን ለመፈለግ አትስጥ በአንደበትህም ይሁን በልብህ፣ በስሜትህም ይሁን በሃሳብህ የራስህ ነገር ኖሮህ እንደሰጠህ አስበህ አትኩራራ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን እንደ ትልቅ ማስረጃ ተጠቀም፡፡ “አንተ እድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልክ ከሆነ ግን እንዳልተቀበልክ የምትመካ ስለምንድር ነው?” (1 ቆሮ 4፣7) ስለዚህ ስጦታ ሁሉ ከእግዚአብሔር ተቀብለን የምንሠጠው እንጂ የራሳችን እንደሆነ በከንቱ የምንመካበት አይደለም፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
+++