እየመራም ከግብጽ አክሱም አደረሳቸው:: አባ ሊባኖስም በዚያ በዓት ወቅረው ይጸልዩ ጀመር:: ጥቂት ቆይተውም ለስብከተ ወንጌል ተሰማሩ:: በተለይ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በስብከት ከአክሱም ሸዋ (ግራርያ) ደርሰዋል::
ተመልሰው ወደ አክሱም ሔደው: ጠበልን አፍልቀው ነበርና ድውያንን ፈወሱ:: ሙትን አስነሱ:: በዚህ የቀኑት የአካባቢው ሰዎች ግን "ምትሐተኛ ነህ" ብለው አባረሯቸው:: ጻድቁም ዶርቃ በምትባል ቦታ ለ3 ዓመት ሲኖሩ በአክሱም ዝናብ አልዘንብ አለ::
ጥፋታቸው የገባቸው የአክሱም ካህናት ወደ ጻድቁ ሔደው "ይማሩን" ቢሏቸው ዘንቦላቸዋል:: አባ ሊባኖስ ግን ወደ ሽዋ ተመልሰው በደብረ አስቦ ለመኖር ቢሞክሩ አልተሳካም:: ስሙ የአንተ: ማደሪያነቱ ግን የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ነውና ወደ "መጣዕ" ሒድ አላቸው መልአኩ::
እርሳቸውም ወደ መጣዕ (ኤርትራ) ወርደው ታላቅ ገዳም አነጹ:: ጠበሎችን አፈለቁ:: ብዙ አርድእትንም አፈሩ:: በዚያም በቅድስናና በገቢረ ተአምራት ኑረው ጥር 3 ቀን በ140 ዓመታቸው ዐርፈዋል:: የላሊበላውን ቤተ አባ ሊባኖስን ጨምሮ በርካታ አብያተ መቃድስ በሃገራችን አሏቸው::
=>የሕጻናቱና የጻድቁ አምላክ እኛን ይማረን:: ከበረከታቸውም ያሣትፈን::
==>ጥር 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."144 ሺ" ቅዱሳን ሕጻናት
2.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
3.አባ አሞን መስተጋድል
=>ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ካህናት (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አቡነ ዜና ማርቆስ
5.ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ
=> "አየሁም: እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር:: ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም: የመንፈስ ቅዱስም ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ . . . ደርዳሪዎችም በገና እንደ ሚደረድሩ ያለ ድምጽ ሰማሁ:: በዙፋኑም ፊት: በአራቱም እንስሶችና በሊቃውንቱ ፊት አዲስ ምስጋና አመሰገኑ:: ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም:: ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው:: ድንግሎች ናቸውና::"
(ራዕ. 14:1)
>