"" ደብረ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ (ጎንደር) ""
☞ገድለኛው ጻድቅና ሐዋርያዊው መናኝ አባ ሊባኖስ (አባ መጣዕ፡ ሲኖዳ፡ ይስሪንም ይባላሉ) በሃገራችን ለ500 ዓመታት የተጋደሉ፡ 80 ጸበሎችን ያፈለቁ፡ 80 ገዳማትን ያነጹ፡ ምድሪቱን በወንጌል አገልግሎት ያዳረሱ አባት ናቸው፡፡
☞በደብረ ሊባኖስ፡ በላሊበላ፡ በወሎ፡ በትግራይ፡ በኤርትራ . . . ድንቅን ይሠራሉ፡፡ ይከበራሉም፡፡
☞ይህኛውን ገዳማቸውን (በርግጥ አሁን ከገዳም ሥሪትነት ወጥቶ ደብር ሆኗል) ግን የሚያስበው ያለ አይመስልም፡፡
☞በዚህ ቦታ (አበው እንደነገሩን) ጻድቁ አባ ሊባኖስ ለ10 ዓመታት በዓት ሠርተው፡ አርድእትን አፍርተው በተጋድሎ ኑረውበታል፡፡ ከተገደመም ከ1ሺ በላይ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ (ዋርካዎቹና ጥዶቹ እነሆ ምስክርም ናቸው)
☞ደስ ያለኝ ድንቅ የጻድቁን ሥራ ማየቴ፡፡
☞ያዘንኩት ዛሬ ዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ነው፡፡ ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ 10 ሰው እንኳ አልነበረም፡፡ በርግጥ ሰው ቢኖረው ምንጣፍ እስከ ማጣት ደርሶ ባልተቸገረም ነበር፡፡
"" የጻድቁን ኃይልና ክብር ግን አይተናልና ክብር ምስጋና ለወደደ ላከበራቸው እግዚአብሔር ይሁን፡፡ እኛንም በአቡነ ሊባኖስ ጸሎት ይማረን፡፡ አሜን፡፡ ""
https://t.me/enabib