††† እንኳን ለታላቁ ኮከበ ገዳም አባ እንጦንስ እና ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አባ እንጦንስ †††
††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::
ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::
ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::
ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::
ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::
ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::
ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::
እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::
አባ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባታቸው: ለገዳማውያን ሁሉም ሞገሳቸው ናቸው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ "ኮከበ ገዳም: ማኅቶተ ገድል (የበርሃው ኮከብ: የተጋድሎ መብራት)" ተብለውም ይጠራሉ::
ቤተ ክርስቲያን ለጀማሪዎች ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች:: ለምሳሌ:- አባ ዻውሊን (የካቲት 2 የሚከበሩ) ለብሕትውና መሠረትን ስለ ጣሉ "አበ ባሕታውያን" ብላ ታከብራለች:: አባ እንጦንስን ደግሞ "አበ መነኮሳት (የመነኮሳት አባት): ቀዳሚሆሙ ለመነኮሳት (ለመነኮሳት ቀዳሚና ጀማሪ) ስትል ትጠራቸዋለች::
አባ እንጦንስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚነሱ ቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ መንገድን ይጠርጉ ዘንድ ብዙ መከራን በትዕግስትና በአኮቴት ተቀብለዋል:: ላለፉት 1,700 ዓመታት እንደ ሻማ እየቀለጡ ያበሩ አበው ቅዱሳን ሁሉ የአባ እንጦንስ ልጆች ናቸው::
ከምጥ የከፋ የዲያብሎስ ፈተናን ተቀብለው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ቅዱሳኑን ወልደዋል:: የመነኮሳት አለቃ የሆኑትን ታላቁን መቃርዮስን ጨምሮ በርካቶችን አመንኩሰው ለቅድስና አብቅተዋል::
አባ እንጦንስ ግብጻዊ ሲሆኑ የተወለዱት አቅማን በምትባል ቦታ አካባቢ ነው:: ጊዜውም በ252 ዓ/ም ነው:: የተባረኩ ወላጆች ለቅዱሱ እንጦንስና አስከትለው ለወለዷት ሴት ልጃቸው : አስቀድመው ፍቅረ ክርስቶስን: አስከትለውም ሃብት ንብረታቸውን አውርሰው ዐርፈዋል::
በዚህ ጊዜ የአባ እንጦንስ እድሜ አፍላ ወጣትነት ላይ ነበር:: በልጅነት ጊዜአቸውም አባ እንጦንስን ሲስቁ: ሲጫወቱ: አልያም ሲቀልዱ አየሁ የሚል ሰው አልነበረም:: ፍጹም ቁም ነገረኛና ታዛዥ: በዚያ ላይም አስተዋይ ነበሩና ሙሉ ጊዜአቸውንም ከቅዱስ ቃሉ በመመገብ: በትምሕርትና በማስቀደስ ያሳልፉ ነበር::
ዘወትርም ዜና ሐዋርያትን እያነበቡ በመንፈሳዊ ቅናት ይቃጠሉ ነበር:: በጊዜው የምናኔ ሕይወት ጐልቶ ባለ መገለጡ አባ እንጦንስ የሚያደርጉት ይጨንቃቸው ነበር:: ሲጸልዩም "አበው ሐዋርያት ይሕንን ክፉ ዓለም ንቃችሁ ጌታችሁን የተከተላችሁበት ጥበብ እንደ ምን ያለ ነው!" እያሉ ይደነቁ ነበር:: መሻታቸውን ያወቀ ጌታም ምሥጢርን ገለጠላቸው::
አንድ ቀን በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ካህኑ ስለ ምናኔ የሚጠቅሰውን ክፍል አነበበ:: ለአንድ ባለ ጠጋ ሕግጋትን ከነገረው በሁዋላ "ፍጹም ልትሆን ከወደድክስ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ተከተለኝ" (ማር. 10:17) የሚለውን ጥቅስ ሲሰሙ ተገርመው "ጌታ ሆይ! ይህንን የተናገርኸው ለእኔ ነው" ሲሉ አሰቡ:: በቀጥታም ሃብታቸውን ለአካባቢው ሰው አካፍለው: እህታቸውን ከደናግል ማሕበር ደምረው እርሳቸው ወደ ዱር ሔዱ::
ከዚህች ቀን ጀምረው አባ እንጦንስ ከ80 እስከ መቶ ለሚገመቱ ዓመታት ከአጋንንት ጋር በጦርነት ነበር የኖሩት:: በንጹሕ አምልኮታቸውና በቅድስናቸው የቀና ጠላት ሰይጣን በብዙ ጐዳና ፈተናቸው:: አቅም ቢያጥረው አራዊትን መስሎ ታገላቸው::
በዚህ አልሳካ ቢለው የእሳት ሰንሰለትን አምጥቶ ገረፋቸው:: በሞትና በሕይወት መካከል ጥሏቸው ሔደ:: ወድቀው ያገኟቸው ሰዎች ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋቸው አገገሙ:: ልክ ሲነቁ ግን ፈጥነው ወደ በርሃ ተመለሱ::
ሰይጣን በርሃው የቅዱሳን ማደሪያ እንዳይሆን ሰግቷልና ጨክኖ ታገላቸው:: ግን አልቻላቸውምና ተረታ:: አምላከ ኃያላን ክርስቶስ ከቅዱሱ ጋር ነበርና:: ከዚህ በሁዋላ ግን ጸጋው በዝቶላቸው ድውያንን የሚፈውሱና ሰይጣን የማይቀርባቸው ሰው ሆኑ::
በረዥም ዘመነ ቅድስናቸውም:-
1.ብዙ አርድእትን ከመላው ዓለም ሰብስበው: አስተምረው: ምናኔን ከግብጽ ማዶ በመላው ዓለም አስፋፉ::
2.በደመና እየተጫኑ ብዙ አሕጉራትንም እየዞሩ ሰበኩ:: በዚህም አሕዛብን ወደ እምነት: ኃጥአንን ወደ ንስሃ መለሱ::
3.ጊዜው ዘመነ ሰማዕታት ነበርና ወደ አደባባይ ሒደው ከሃዲዎችን ገሠጹ:: ማንም ደፍሮ ግን አልገደላቸውም::
እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን እየሠሩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ መነኮሱ:: እርሳቸውም ብዙዎችን አመነኮሱ:: አርጅተው እንኩዋ ከተጋድሎ ያላረፉት አባታችን የጣመ ነገር ቀምሰው: ገላቸውን ታጥበው አያውቁም:: በ372 ዓ/ም በዚህች ቀን ሲያርፉም ዕድሜአቸው 120 ደርሶ ነበር::
የአባ እንጦንስን በዓል ለማክበር የምትሹ ቤተ ክርስቲያናቸው ጎንደር ከተማ ከቀሃ ኢየሱስ በላይ ይገኛል::
††† ለአባታችን እንጦንዮስ /እንጦንስ/ እንጦኒ ክብር ይገባል!
††† ቅዱስ ዑራኤል †††
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል:-
1.ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጉዋታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቅድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች::