Фильтр публикаций


⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
መልካም ዜና

ሰሞኑን ሁሉም ሰዉ Airdrop የሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ለ Airdrop ደግሞ 🐣ትዊተር(X, Twitter) በጣም አስፈላጊ ነዉ። ለዚህም እኛም ይሄን በማሰብ ለ 🐣X(Twitter) ፎሎወር እና 😎Mention ያግዛቹ ዘንድ የ Twitter Follower በቅናሽ ዋጋ አቅርበናል። አሁኑኑ ይዘዙን።

🐣1 Follower ➡️ 1.5 ETB
🐣100 Followers ➡️150 ETB
🐣1000 Followers ➡️ 1500 ETB

✅Minimum Order: 100 Followers 🐣


ለማዘዝ ያናግሩኝ👇
😏✉️@BEK_I
😏✉️@BEK_I


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❇️#ይመልከቱ #ይለማመዱ #ይዘጋጁ

✅የመውጫ ፈተና ኦንላይን አገባብ፣ አጠቃቀም እና አፈታተኑን የሚያሳይ አጋዥ ቪዲዮ

📼 3.9 MB
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📚JOIN: @Ethio_Educational_News
📚JOIN: @EUEE_TIPS
📚JOIN: @Et_Study_Notes


በአዲስ አበባ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ወጥነት ያለው የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚህም፦

- ከሰኔ 24 እስከ 30/2016 ዓ.ም ድረስ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ እና የመጽሐፍት ስርጭት

- ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም  ድረስ መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ ይደረጋል

- ከነሃሴ 21-30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የ7ተኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል

- ጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው የሚመጡ አዲስ የተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል

- መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም  ለተማሪዎች ስለ ት/ቤቱ ህገደንብና ተያያዥ ጉዳይ ላይ ገለጻ ይሰጣል

- መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም   መደበኛ ትምህርት ይጀምራል

- መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ይጀምራል

- ህዳር 16-18 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 7-9 ቀን 2017 ዓ.ም ለ6ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 19-23 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል

- ከጥር 26-29 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን ፈተና የሚያርሙበት እና ውጤት ማጠናቀሪያ ሳምንት

- ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል

- የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም  የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ይጀምራል

- ሚያዚያ 6-8 ቀን 2017 ዓ.ም  የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል

- ግንቦት 19-22 ቀን 2017 ለ6ኛ፣ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 3-4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 9-11 ቀን 2017 ዓ.ም  ድረስ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይሰጣል

- ከሰኔ 16-20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሁለተኛ  ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል

- ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መምህራን የተማሪዎችን የፈተና ውጤት የሚያሳውቁበት ይሆናል

- ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም  የውጤት መግለጫ ካርድ በመስጠት የዓመቱ ትምህርት ይጠናቀቃል።

ቢሮው በ1ኛ ወሰነ ትምህርት 103 የትምህርት ቀናት ሲኖሩ በ2ኛ ወሰነ ትምህርት 101 ቀናት በጠቅላላው በዓመቱ 204 የትምህርት ቀናት መኖራቸውን ጠቅሷል።

በተጨማሪም ትምህርት ቢሮ የትምህርት ካላንደሩና ካላሻሻለ በስተቀር ማንኛውም ትምህርት ቤት ከካላንደሩ ውጪ የትምህርትን ስራ ማከናወን የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📚JOIN: @Ethio_Educational_News
📚JOIN: @EUEE_TIPS


ለ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት አሳወቀ።


(ሰኔ 11/2016 ዓ.ም) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገልጿል ።


የክ/ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ እንደገለፁልን በክፍለ ከተማው በመንግስት ት/ቤቶች ለሚገኙ 4968 እና በግል ት/ቤቶች ለሚገኙ 3074 በአጠቃላይ ለ8 ሺህ 42 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 5 ክላስተር ማእከላትን በማቋቋም በ21 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልፀው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📚JOIN: @Ethio_Educational_News
📚JOIN: @EUEE_TIPS


#AddisAbaba

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም በአዲስ አበባ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1332 የማስተማር ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል።

43 ት/ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን አመልክቷል።

150 ት/ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

41 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑ ተመላክቷል።

የትምህርት ቤቶቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📚JOIN: @Ethio_Educational_News
📚JOIN: @EUEE_TIPS


በአረፋ በዓል ምክንያት በቀን 9/10/2016 ዓ.ም ሳይሰጥ የዋለው የሬሜዲያል ፈተና ሰኞ (በ10/10/2016 ዓ.ም) በፊዚክስ እና ማክሰኞ (በ11/10/2016 ዓ.ም) በኬሚስትሪ ፈተና እንደሚቀጥል እናሳውቃለን፡፡


ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው‼️

🗣ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)


📊በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እ
የተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Ⓒትምህርት ሚኒስቴር
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📚JOIN: @Ethio_Educational_News
📚JOIN: @Ethio_Educational_News


በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ፈተና ነገ ሰኔ 4/2016 ዓ.ም መሰጠት ይጀምራል።

በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4-5/2016 ዓ.ም እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ እንሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና በከተማዋ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86,672 ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን፣ የ6ኛ ክፍል ፈተና ደግሞ በ183 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86,222 ተማሪዎች ይሰጣል ተብሏል።

ሁለቱንም ፈተናዎች የሚያስፈፅሙ ከ2,200 በላይ ፈታኞች፣ ከ700 በላይ ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም 183 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች መመደባቸው ታውቋል።

✅ Best Educational Channels
👉 @Euee_Tips
👉@Ethio_Educational_News
👉@Oromia_Educational_News
👉@AmboIfaBoru


ማስታወቂያ
ለሬሜዲያል ተፈታኞች በሙሉ
የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3-10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ስለሆነ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11/2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር


✅ Best Educational Channels
👉 @Euee_Tips
👉@Ethio_Educational_News
👉@Oromia_Educational_News
👉@AmboIfaBoru


ዛሬ ያበቃል!

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program) የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በቻሌንጁ ላይ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፤ Cyber Security, Cyber Development, Embedded Systems, and Aerospace የታለንት መስኮች ናቸው፡፡

ምዝገባው ዛሬ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

ለመመዝገብ፦ https://talent.insa.gov.et

@tikvahuniversity




በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በተመሳሳይ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናዎቹን ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተናውን 86,671 ተማሪዎች እንዲሁም የስድስተኛ ክፍል ፈተናውን 86,217 ተማሪዎች እንደሚወስዱ በቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ከተፈቀዱ የፈተና ቁሳቁሶች ውጪ፣ ዲጂታል ሰዓትን ጨምሮ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይዞ ወደ ፈተና መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

✅ Best Educational Channels
👉 @Euee_Tips
👉@Ethio_Educational_News
👉@Oromia_Educational_News
👉@AmboIfaBoru


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከደቡብ ኮርያ ምክትል ጠቅላይ ሚ/ር እና የትምህርት ሚ/ር Lee Ju-Ho ጋር ተወያዩ።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በውይይታቸው በትምህርት ዘርፍ ስለሚኖረው ትብብር አንሥተዋል። በከፍተኛ ትምህርት፣ በአጠቃላይ ትምህርት እና በመምህራን ሥልጠና ዘርፍ ደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ እንደምትደግፍ የኮሪያ ምክትል ጠቅላይ ሚ/ር ገልጠዋል።


✅ Best Educational Channels
👉 @Euee_Tips
👉@Ethio_Educational_News
👉@Oromia_Educational_News
👉@AmboIfaBoru


ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸው ስህተትን መቀነስን ጨምሮ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የበይነ መረብ ፈተና ለስህተት በር አይከፍትም

የበይነ መረብ ፈተና አንድ ጥያቄ ሳይመልሱ ወደ ፈለጉት ጥያቄ በአንድ Click የመሔድ እንዲሁም ተመልሰው መስራት የሚፈልጉትን ጥያቄ Flag በማድረግ ተመልሶ የመስራት ዕድልን ይሰጣል።

ጊዜ ቆጣቢ ነው

በአንድ Click የፈተና ጥያቄን መልስ ለመስጠት ያስችላል። እንዲሁም ምን ያህል ደቂቃ እንደተጠቀሙ ከመፈተኛ ስክሪን ላይ ማየት ስለሚቻል ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል።

የተሻሻለ የመረጃ ቋት አለው

የበይነ መረብ ፈተናዎች በቂ የፈተና መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በማከማቸት ለተፈታኞች አመጣጥኖ ያቀርባል፡፡

የተሰሩ ጥያቄዎችን መልስ በፍጥነት በራሱ ይልካል

በፈተና ወቅት ጥያቄዎቹን ሰርተው ሳያጠናቀቁ የተሰጠው ደቂቃ ካለቀ የሰሩትን በጠቅላላ በራሱ በፍጥነት ይልካል።

ፈጣን ግብረ መልስ ይሰጣል

በበይነ መረብ ፈተናዎች ሲሰጡ ውጤታቸው ከሌላው ጊዜ በተለየ ፈጥኖ የመታወቅ ዕድል ይሰጣል።

ተማሪዎች በቤታቸው እያደሩ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣል

ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተሙከራ ካላቸውና የመፈተኛ ክላስተር ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሆነው እንዲፈተኑ ዕድል ይፈጥራል። #MoE

@tikvahuniversity


የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን የሚወስዱ ተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀ ማስፈንጠሪያ (URL) ላይ በመግባት እንዲለማመዱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
ከስር የተቀመጡት ማስፈንጠሪያዎች ተፈታኝ ተማሪዎች የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው ዕለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናሉ።

Note:
እስካሁን Username እና Password ያለገኛችሁ ተፈታኞች፤ ከትምህርት ቤት አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

➧ ክላስተር አንድ

አዲስ አበባ፦ https://c2.exam.et
ሲዳማ ክልል፦ https://c2.exam.et
ትግራይ ክልል፦ https://c2.exam.et

➧ ክላስተር ሁለት

ደቡብ ም/ኢ/ክልል፦ https://c3.exam.et
ጋምቤላ ክልል፦ https://c3.exam.et
አማራ ክልል፦ https://c3.exam.et

➧ ክላስተር ሦስት

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፦ https://c4.exam.et
ሀረሪ ክልል፦ https://c4.exam.et
አፋር ክልል፦ https://c4.exam.et
ኦሮሚያ ክልል - 1
• አዳማ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• አጋሮ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• አምቦ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ምሥራቅ አርሲ፦ https://c4.exam.et
• ምዕራብ አርሲ፦ https://c4.exam.et
• አሰላ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ባሌ፦ https://c4.exam.et
• ባቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ቤሾፍቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ቦረና፦ https://c4.exam.et
• ቡሌ ሆራ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ቡኖ በደሌ፦ https://c4.exam.et
• ዶዶላ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ባሌ፦ https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ቦረና፦ https://c4.exam.et
• ጉጂ፦ https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et
• ምዕራብ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et
• ሆለታ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ሆሮ ጉዱሩ፦ https://c4.exam.et
• ኢሉባቦር፦ https://c4.exam.et

➧ክላስተር አራት

ድሬዳዋ ከተማ፦ https://c5.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2
• ጅማ፦ https://c5.exam.et
• ጅማ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ቄለም ወለጋ፦ https://c5.exam.et
• ማያ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• መቱ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሞጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሞያሌ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ነጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ነቀምት ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሮቤ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሰንዳፋ በኬ፦ https://c5.exam.et
• ሻኪሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሻሸመኔ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሸገር ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሸኖ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ምስራቅ ሸዋ፦ https://c5.exam.et
• ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ)፦ https://c5.exam.et
• ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et
• መዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et
• ምስራቅ ወለጋ፦ https://c5.exam.et
• መዕራብ ወለጋ፦ https://c5.exam.et
• መዕራብ ጉጂ፦ https://c5.exam.et
• ወሊሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et

@ethio_educational_News


Репост из: The Scholar
National Cyber Talent Challenge registration has started

Addis Ababa: May 16/2016: The Information Network Security Administration (INSA) announced the start of registration for the 2016 "National Cyber Talent Challenge" program.

Bishaw Yeene, director of the Cyber Talent Center , said in a statement to reporters today that the registration for the 2016 "National Cyber Talent Challenge" program will be held from May 15/2016 to May 30/2016. He also said that the recruitment at the national level will be done through a portal dedicated to this program https://talent.insa.gov.et .

➡If you are interested in:
➡️ Development
➡️ Embedded
➡️ Cyber Security then this is for you.

➡ For Registration
https://talent.insa.gov.et

#INSA #Scholarship #CyberTalent #Development #CyberSecurity #Embedded

✉️https://t.me/+Dmxb4Vi2uuI5ODNk
✉️https://t.me/+Dmxb4Vi2uuI5ODNk


በ2016 ዓም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ላይ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ተወስኗል

በ2016 ዓ.ም. በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሆኑ እንደሚከተለው ተወስኗል፡፡

ከተፈጥሮ ሣይንስ (Naturals)
- English
- Maths
- Biology
- Physics
- Chemistry
- SAT (Aptitude)

ከማህበራዊ ሣይንስ (Socials)
- English
- Maths
- History
- Economics
- Geography
- SAT (Aptitude)


የፈተና አወጣጡን በተመለከተ

ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ፈተናው የሚወጣው፡

👉ከ9ኛ-11ኛ በነባሩ /በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና
👉12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል::

የኢኮኖሚክስ ፈተና ብቻ ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው ይዘጋጃል።

Join👇👇
https://t.me/Ethel_Academy94

        🎯🎯Our Aim🎯🎯

To Empower Ethiopian Students

       🇪🇹ኢትኤል Academy🇪🇹


😎 Notcoin እየገዛው ነው

✅ መሸጥ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ
✅  ከ 1000 Not ጀምሮ እገዛለው
✅ Price Depends On The Market.


ለመሸጥ ➡️ Inbox me✅@BEK_I


የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 1 ወር ከ2 ሳምንት ቀርቶታል

እንደሚታወቀው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 - 5 ዓም ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ 9 - 11 ዓም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ጊዜ ለእናንተ ወርቃማ ስለሆነ ጊዜያቹን በአግባቡ መጠቀም ይኖርባችኋል፡፡

🔹 ያነበባቹትን የምትክልሱበት
🔹 ጥያቄዎችን የምትሰሩበትን
🔹 የሚያዘናጋቹ ነገር የምትቀኑስበት መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ በየቀኑ ፊልም የምታዩ ከሆነ መቀነስ ይኖርባችኋል፡፡
🔹 ከትምህርታቹ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ሶሻል ሚዲያዎች ቀንሷቸው ወይም ከተቻለ ለጊዜው አጥፏቸው፡፡
🔹 ስራ የምትሰሩ ከሆነ ይሄንን ጊዜ መተው ይኖርባችኋል፡፡ ካልተቻለ ደግሞ የስራ ጊዜያቹን በተቻለ መጠን ቀንሱ፡፡
🔹 ቤታቹ በአግባቡ ማጥናት ካልቻላቹ በግሩፕ ወይም ላይብረሪ እየሄዳቹ አጥኑ፡፡

የኢንትራንስ ፈተና ለማህበራዊ ሳይንስ 42 ቀን ፤ ለተፈጥሮ ሳይንስ 48 ቀን ብቻ ቀርቶታል፡፡ ስለዚህ ጊዜውን በደንብ ተጠቀሙበት፡፡ ከፈተና በኃላ ለመዝናናት ብዙ ጊዜ አላቹ፡፡


✅ Best Educational Channels
👉 @Euee_Tips
👉@Ethio_Educational_News
👉@Oromia_Educational_News
👉@AmboIfaBoru
👉https://t.me/+Rc34bGHfdSs5ODQ0


ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።
። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ።

ኢትዮጵያን ወክለው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ አይሲቲ ውድድርን በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት 3 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶሰተኛውን ሽልማት ከማሌዢይ፣ ሜከሲኮ እና ኬንያ ቡደን ጋር ተጋርተዋል።
ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሶስት የውድድር ትራኮች (Innovation, Network and Computing) ተካፋፍሎ የተካሄደ ሲሆን ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በተገኙ ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ አገሩ ተመልሷል።
የትምህርት ሚኒስቴር በተማሪዎቹ ውጤት የተስማውን ደስታ እየገለጸ፣ ወደፊትም የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ከመሰል ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።




✅ Best Educational Channels
👉 @Euee_Tips
👉@Ethio_Educational_News
👉@Oromia_Educational_News
👉@AmboIfaBoru
👉https://t.me/+Rc34bGHfdSs5ODQ0

Показано 20 последних публикаций.