♻ የማይጠቅም ክብርና ማዕረግ የጣት ላይ ሒና ነው::
♻ በሁለት ጣት የታለበ ወተት በአስር ጣት አይመለስም::
♻ ቅድመ ጥንቃቄ የጥበብ የበኩር ልጅ ነው::
♻አራት ነገሮች ትንሻቸው ትልቅ ነው :-
1,እሳት
2,ጠላት
3,በሽታ
4,ድህነት
♻ ስልጣን እንደ እናት ጡት ነው፤ ሲጠቡት ይጣፍጣል ሲተዉት ይመራል::
♻ እራስን መሆን ውበት ነው እንደራስ መኖር ብስለት ነው::
♻ እስከ መጨረሻ መሄድ ካልቻልክ መንገድ አትጀምር::
♻ ትዕግስት ስሩ መራራ ፍሬው ጣፋጭ ነው::
♻ ታጋሽነት የነውር ቀብር ነው::
♻ አንተን ማዳመጥ ላልፈለገህ ሰው ወሬ ማውራት ለቀብር ሰዎች ምግብ እንደማቅረብ ነው::
♻ አዳምጥ ያለበለዚያ የራስህ ምላስ ደነዝ ያደርግሀል::
♻ የሠው ወሬ የባህር ማዕበል ነው የረጋ ልብን ያናውጣል::
♻ ምላስ እንደተሳለ ቢለዋ ነው ሳያደማ ይገድላል የዝምታ ዛፍ የሠላም ፍሬዎችን ያፈራል::
♻ የማይፀፀትን ሠው ይቅርታ ብሎ ማለፍ በውሀ ላይ ስዕል እንደመሣል ነው::
♻ እንደ ንፁሕ ህሊና የለሰለሰና የሚመች ትራስ አይገኝም ::
⚠ ለብልግና ደፋር አትሁን - ሠዎች እንዳትመለስ አድርገው ይተፉሀል
⚠ዝንጉ አትሁን - መግባባት አትችልም
⚠ ቸልተኛ አትሁን - ቀጠሮና ተግባርህን ትረሳለህ
⚠ ኮስታራ አትሁን - በሩቅ ትሸሻለህ
⚠ ፈሪ አትሁን - ለመሪነት አትበቃም
⚠ ችኩል አትሁን - ማመዛዘን ይሳንሐል
⚠ ወሬ አታብዛ - ሚስጥርህን አብረሕ ታወጣለህ
⚠ ለሁሉም አስተዋይ ሁን ይበጅሀልና::
⚜ የጠላት ምራቅ መርዝ ነው::
⚜ ስስት የነፍሲያ ጠላት ነች::
⚜ የማንነት መገለጫ ድርጊት እንጂ የቃላት አደራደር አይደለም::
⚜ የማያስብ ህዝብ መኖሩ ለአምባገነን መሪዎች ጥሩ ሀብት ነው::
⚜ ሰው ነኝ እስካልክ ድረስ የማሠብ አቅምህን አለመጠቀምህ ይቅርታ የማይደረግለት ወንጀል ነው::
⚜ ታላቅ አእምሮ የተደጋጋሚ ጥረት ውጤት ነው::
⚜ በዕውቀት ብሉኬት ያልተገነባ ክብር የበጋ ንፋስ ያፈርሰዋል::
⚜ ጊዜ ሠይፍ ነው ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል::
⚜ ዕርጥብ አትሁን ትጨመቃለህ።
⚜ ደረቅ አትሁን ትሰበራለህ።
React family
JOIN
@Ethio_Sigmaa@Ethio_Sigmaa