#EthioTechs_News📄
📌የቻይና የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች🚻 ሌላ ታሪክ ላይ ናቸው🔥
በቤይጂንግና ሻንጋይ ከተሞች የተከፈቱት እነዚህ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች እስከዛሬ ያልተሞከረ አዲስ ነገር ይዘው በመምጣት የመጀመሪያዎቹ ሆነዋል ።
ለጊዜው ለወንዶች ብቻ የተዘጋጀው ይህ መፀዳጃ ቤት አንድ ሰው መጠቀም ሲፈልግ ፡ በስልኩ 20 የቻይና ዩአን ይከፍላል ።
ከዛም ፊትለፊቱ ያለውን ተች ስክሪን ነክቶ ልክ እንደማንኛውም መፀዳጃ ቤት በተዘጋጀው ቦታ ላይ ሽንቱን ሸንቶ ሲጨርስ በስልኩ ላይ ቴክስት ይገባለታል ።
በዚህ በስልኩ ላይ በተላከለት የምርመራ ውጤትም ፡ በሰውነቱ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ፡ የበሽታ መከላከል አቅሙን ፡ የኩላሊት ኢንፌክሽን እንዳለው እና እንደሌለው ከነገረው በኋላ ፡ በተጨማሪም ፡ ከውጤቱ በመነሳት ሰውየው ማድረግ የሚገባውን አንዳንድ የጤና ምክሮችን ይሰጠዋል ።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ታዲያ ሰውየው ሽንቱን ሽንቶ እስኪጨርስ ባለው የሰከንዶች ጊዜ ውስጥ ነው ።
🦋#Share🦋
👩💻
@ethio_techs 👨💻
@ethio_techs 👩💻