"የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ሼዶች ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል"- የእሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን
በዛሬው እለት ከረፋዱ 5:57 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 11 ሎሚ ሜዳ እየተባለ በሚጠራዉ ኢንደስትሪ መንደር ላይ ተከስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን የእሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የእሳት አደጋዉ ያጋጠመዉ የእንጨትና የብረታ ብረት ዉጤቶች ማምረቻ ሼድ ላይ ሲሆን በአደጋዉ በአንድ መለስተኛ ሼድ ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።
በዚህ ኢንደስትሪ መንደር በርካታ የእንጨትና የብረታ ብረት ማምረቻ ሼዶች የሚገኙበት ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ሼዶች ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሰባት የአደጋ ጊዜ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ከ 45 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ የደረሰ ጉዳት የለም።
የእሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ ሶል መልእክቱን አስተላልፏል።