✅በሀገራችን_በህንጻ መዋቅር ጥናት ውስጥ ጥቂት ስለ Seismic (Earthquake) ታሳቢነት
ይህ ጽሁፍ የተዘጋጀው ወቅታዊው የመሬት መንቀጥቀት ያሳደረብንን ስጋት አንጻር ጥቂት ለማለት ነው።
በሀገራችን ራሱን የቻለ የዲዛይን ኮድ አለን ካሉን የዲዛይን ኮዶች መካከል አንዱ ስለ Seismic Design የሚንመራበት ES EN 1998-1:2015 Design of Structures for Earthquake Resistance የሚለው ይገኝበታል።
የመዋቅር ዲዛይን የሚሰራው ባለሙያም ዲዛይኑን የሚያጸድቀውም መኮንን በዚሁ መሰረት ዲዛይን ተሰርቶ ወደ ግንባታ እንዲገባ ፈርመው ይሰጣሉ።
ገንቢውም በዚህ ተመስርቶ እንዲገነባ ይጠበቅበታል።
የህንጻ መዋቅር ዲዛይን ታሳቢዎች
በመዋቅር ዲዛይን ታሳቢ የሚደረጉ ጭነቶች (Action loads) መካከል መሰረታዊ የሚባሉት Dead load, Live load Wind Load እና Seismic actions ሲሆኑ እንደ ሁኔታው እየታየ የተዘረዘሩት loadዎች በጋራ የሚያመጡት ጉዳት ከግንዛቤ የሚያስገባ እንደ አስፈላጊነቱ ከ 100 load combination ይሰራል።
ወደ መሬት መንቀጥቀጡ ስንገባ ለህንጻ ዲዛይንም በሬክተር ስኬል እየተለካ ሳይሆን ቀድሞ በተጠና አካባቢያዊ ተጠባቂ ሁኔታ የተከፋፈሉ ዞኖችን ታሳቢ አድርጎ በዚያ አካባቢ የሚጠበቀውን ከፍተኛ የምድር እንቅስቃሴ (Peak Ground Acceleration) ታሳቢ በማድረግ በተሰሩ ቀመሮችና ለመቀመሪያ በተዘጋጁ Software በመታገዝ ነው።
✅ወደ ዲዛይን ታሳቢዎች ስንገባ
፩) ህንጻው የሚገባበት አካባቢ ለመሬት መንቀጥቀጥ ያለው ተጋላጭነትን ያገናዘበ ዞን (Seismic Zone) ( አዲስ አበባ ዞን 3 ሲሆን የሰሞኑ የአብዛኛው መሬት መንቀጥቀጥ መነሻ አፋር ክልል ብዙው ዞን 5 ነው)
፪) እያንዳንዱ ህንጻ ስንመለከተው በአርማታ በመሰራቱ ግትር ቢሆንም የመሬት መንቀጥቀጥን ለመከላከል እንዲችል የተወሰነ ያክል ተለማጭ እንዲሆን የሚያስችል ስሌት (Elastic Analysis) ይሰራለታል።
፫) የህንጻው መሰረት የሚያርፍበት የመሬት (አፈር/አለት)
ሁኔታ ( Ground Type) ታሳቢ ይደረጋል።
፬) የሚገነባው ህንጻ መዋቅር ዓይነት ( Structural Type and Behavioral Factor) የጥናቱ አካል ነው።
፭) የህንጻው ቅርጽና ቁመና (Structural Regularity) ከግምት ውስጥ ይገባል።
፮) የህንጻው መዋቅር አካላት Beam, Slab, Column, Wall, Number of Story, Number of Bays እና Foundation Types በልዩ ሁኔታ ታሳቢ ይደረጋሉ።
፯) ለግንባታ የምንጠቀማቸው ቁሶችና ጥራታቸው ( በተለይ የአርማታ የብረት ) በየመስፈሪያቸው የዲዛይኑ ግብዓት ሆነው ያገለግላሉ።
⭐️ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ታሳቢዎች ታክለው በተሰራው የኮምፒውተር ሞዴል በሚሰጣቸው ከመቶ በላይ load combinations የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉትን እንዲቋቋም ተደርጎ ፣ የተለያዩ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው Modifier Factors ተካተው፣ የ Stability Check ተደርጎ የስትራክቸራል ዲዛይን ድሮዊንግ ይሰራል።
✅ለምን እንንቀጠቀጣለን?
⏺እንዲህ ተሰርቶ ለምን እንንቀጠቀጣለን? ለሚለው መልሱ ከላይ የዘረዘርኩት ማስረጃዎችን ታሳቢ ተደርጎ ከተሰራ ዲዛይን ላይ ሶስት ሞዴሎች ተያይዘዋልና ተመልከቷቸው።
⏺እንቅስቃሴዎቹ በተለያዩ load combinations ህንጻው ራሱን ሲከላከል የሚያሳይ የትክክለኛ ዲዛይን animation ነው።
⏺ይህ እንቅስቃሴ በአይናችን ልናየው ባንችልም የተሰቀሉ መብራቶች ሲንቀሳቀሱ፣የተቀመጠ ዕቃ ሲወድቅ፣ የተከፈተ መስኮት/በር ሲዘጋ...እንመለከታለን እኛም ህንጻው ላይ እንደተቀመጡት ዕቃዎች ንዝረቱ ይሰማናል እንጂ የህንጻውን እንቅስቃሴ ልንመለከት አንችልም ግን እየተንቀሳቀሰ ነው።
⏺ህንጻው ተንቀሳቀሰ ማለት ዲዛይኑ ትክክል አይደለም ማለት ወይም ይፈርሳል ማለት አይደለም። ዲዛይን በተደረገው ሞዴል መሰረት እራሱን እየተከላከለ ነው።
💫ምን ያሰጋናል?
፩) የግንባታ ጥራት
፪) ከዲዛይን ውጪ የተጨመሩ ወለሎች ያሏቸው ህንጻዎች
፫) የመሬት መንቀጥቀጥ የሚነሳባቸው አካባቢ ያሉ ቤቶች
፬) ሳይት ላይ መዋቅሮች የተደረጉ ማሻሻያዎች
፭) በተኛንበት ወይም በተቀመጥንበት የተንጠለጠሉ ቁሶች አናታችን ላይ ወድቀውብን አደጋ እንዳያደርሱብን!
Via ደሳለኝ ከበደ ህንጻ መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ ሪል ስቴት አማካሪ
https://t.me/ethioengineers1