የኤዶም ምድር .....#share
*እንኳን ወደ ኤዶም ምድር በሠላም መጣችሁ።ሰከላ ጥንታዊ ስሟ ኤዶም ይባላል።በዘፍጥረት ከኤዶም በስተምሥራቅ ገነት ትገኛለች።ገነትን ከሚያጠጡ አራቱ አፍላጋት አንዱ ግዮን ነው።ግዮን ከኤዶም ወይንም ከሰከላ መንጭቶ ኢትዮጵያን 7 ጊዜ ይዞራል።(ዘፍ 2፥1-13)
*አዳም ከአባቱ ከመሬት ተፈጠረ።የተፈጠረበት አፈር "ስውሩ አፈር" ይባላል።የተፈጠረበት ቦታ "ኤልዳ" ትባላለች።ኤልዳ አሁንም ጎጃም ውስጥ አስሌዳውያን ( ኤልዳውያን) የሚባል ቦታ አለ።ኤልዳ ከግዮን በቅርብ ርቀት የምትገኝ ናት።አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ኤልዳ ላይ ከተፈጠረ በኋላ በኤዶም በስተምሥራቅ ወደምትገኘው እንዲሁም የግዮን ወንዝ ወደሚያረሰርሳት ገነት በ40ኛ ቀኑ ፈጣሪው አስገባው።አዳም በገነት የኖረው ለሰባት ዓመት ነው።
*በዘፍጥረት ግዮን (አባይ) ዙሪያ የሚያበራ ዕንቁና የሚያብረቀርቅ ዕንቁም ይገኝበታል።ይኼ ቦታ በጎጃም በስተምዕራብ "ፋዞግሊ" የሚባለው የወርቅ ማውጫ ሳይሆን እንዳልቀረ ሳይንሳዊ ጥናቶች እየወጡ ናቸው።
"ፋዞግሊ" የሚባለው የወርቅ ማውጫ ቦታ ንጉሥ ድግናዣን ለመቆጣጠር 100 ሺህ የሚያህል ሠራዊት ይዞ በበጌምድር በኩል ሲዘምት በአሸዋ ተውጦ ቀርቷል። ዐፄ ካሌብ በአገዎች ያስጠብቀው ነበር።በደቡብ ገናና የነበረው የዳሞት መንግሥትም ይህንን የወርቅ ማውጫና የወርቅ ጎዳና ለመቆጣጠር ወደ ሰሜን ተጉዞ ነበረ።የዛግዌ መሥራች መራ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ የወርቅ ጎዳና ጥበቃ ላይ ከተሠማሩት ኃያላን የጦር አዛዦች መካከል አንዱ ነበረ።
*አዳም በሰባተኛ አመቱ ከገነት ከተባረረ በኋላ በአጠቃላይ በምድር ላይ የኖረው 930 ዓመት ነው። የተቀበረው ኮሬብ በሚባል ቦታ ነው።በኢትዮጵያ ኮሬብ የሚባሉ ብዙ ቦታዎች አሉ።በታሪክ የሚታወቀው ግን አምሓራ ሳይንት የሚገኘው ነው።የዮቶር (ካህን ራጉኤል) መኖሪያ እንደነበሩ አሳማኝ ማስረጃዎች እየወጡ ናቸው።ሙሴ በግ የሚጠብቅበት የነበረ ተራራ ተብሎ ይታመናል።
*ግዮን ሰከላ (ኤዶም) ከሚገኘው ግሽ ከተባለው በደን የተሸፈነ ረግረጋማ ቦታ ላይ ይመነጫል።ግሽ ተራራ 2800 ወደ ላይ ይረዝማል።ከተራራው ግርጌ 100 ሜትር ፈንጠር ብሎ አባይ ይወለዳል፡፡ግዮን በሰከላ (በኤዶም) የስያሜ ምንጭም ነው፡፡የአማራ ሕዝብ የበኩር ልጁን "አባይነህ" ይላሉ ታላቅ ነህ ለማለት ነው።
*ግሽ ላይ የጻዲቁ አቡነ ዘርአብሩክ ገዳም ይገኛል።ጻዲቁ አቡነ ዘርአብሩክ በ17ኛው መክዘ ግሽ አባይ ላይ ተቀምጠው ሲጸልዩና ሲያስተምሩ፤ሲያጠምቁበትና ሲፈውሱበት ነበረ። አቡነ ዘርዐ ብሩክ በዚህ ዓይነት የቅድስና ተግባር ቆይተው መጽሐፎቻቸውን በጨርቅ ሸፋፍነው በዓባይ ምንጭ ውስጥ ደብቀዋቸው ወደ ጎንደር ሔዱ።ከሰባት ዓመት በኋላ ወደ ቦታው ተመልሰው መጽሐፎቻቸውን ለማግኘት ከምንጩ አናት ላይ ቆመው፣ለዐራት ጊዜ ጸሎት አድርሰው ከጨረሱ በኋላ “ግሥዒ ግዮንመጻሕፍትየ” (ግዮን ሆይ መጽሐፎቼን ትፊ) ሲሉ መጽሐፎቹ አቧራ እንደለበሱ፤ ርጥበት ሳይኖርባቸው ተንኳፈው ወጥተዋል፡፡ከዚያም ለጓደኛቸው፤ “አባ ይህንን ተአምር እይ” በማለት አሳዩዋቸው፡፡ከዚህ በኋላ የቦታው ስም በግእዝ ግሥዒ ዓባይ ያሉት ቃል ተቀይሮ ግሽ ዓባይ እንደተባለ፤ቦታውም ከገነት ወደ ዓለም እንደ ቧንቧ በሚፈስሰው ጸበል የተባረከና የተቀደሰ፤ ልዩ ምሥጢርም ያለው ውኃ እንደሆነ አባቶች ያስረዳሉ።
*በዚህ ዓይነት የግሽ ዓባይ ጸበል ከውኃው አናት ላይ ሲነሣ እንደ ትንሽ ምንጭ ይሆንና እዚያው ሰከላ (ኤዶም) ትንሽ ወረድ ሲል ደግሞ ማዕበል እየሆነ የግልገል ዓባይን ድልድይ ያቋርጥና በጣና ላይ እየሰፈፈና ቁልቁል ወደ ጢስ ዓባይ እየጎረፈ፤ በደጀን በኩል ወደ ሱዳን ካርቱም፤ ግብጽና ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ወርዶ ይቀላቀላል፡፡
*ከዚህ ጋር በተያያዘ፦
1.ኖህ ከማየ አይኅ የጥፋት ውኃ ልጆቹ፣ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች የዳኑት በመርከብ ነው።የኖኅ መርከብ ማየ አይኅ መጉደል ሲጀምር በ7ኛ ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።የኖኅ መርከብ ሐመር ያረፈችበት ስሙ ሉባር ተራራ ይባላል።አራራት ተራራ ደግሞ የሚገኘው ከዚሁ ጣና ውስጥ ነው።ኖኅ መርከቧ በአረፈችበት አራራት (ዘጌ) አካባቢ ወይን ሲተክል ኖረ። አካባቢውን ሳይለቅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ።በኋላም የተቀመጠው በእንተላ፣በአይዋርካ፣በሽሌ፣በአይከል ቀሪ ዘመኑን የገፋ ሲሆን ጭልጋ ሳለ ሚስቱ እሜቴ አይከል አረፈች።የኖኅ ሚስት እሜቴ አይከል የተቀበረችው ጭልጋ ላይ ነው።በዚህም የጭልጋ ዋና ከተማ በስሟ አይከል ተባለች።ጭልጋ የአራራት ተራራ አዋሳኝ መሆኑ ይታወቃል።
2.ከእሜቴ አይከል እረፍት በኋላ ኖኅ ጎንደር ላይ ብዙ ዘመን ፈጣሪውን እያመሰገነ እየቀደሰ ኖረ።በ950 ዓ.ዓ ኖህ ሲሞት እዛው ጎንደር ላይ ተቀበረ።መቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር።ከዚያም ለኖህ መታሠቢያ ይሆን ዘንድ አምላክ በቤተመንግስት አሳቦ የኖህ የመቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ።ይህም በኋለኛው ዘመን በንጉሥ ፋሲለደስ የታነጸው የፋሲል ግንብ ነው።
3.በሌላው ዓለም በየትኛውም ስፍራ ወይም ምድር በተባለችው ፕላኔት ላይ በየትኛውም አገርና አህጉር የማይገኙ በኖኅ መርከብ ውስጥ ከነበሩት 7ቱ አጥቢ እንስሳት እንደ ዋሊያ፣ቀይ ቀበሮ፣ጭላዳ ዝንጀሮ የመሳሰሉት እና 13ቱ አእዋፋት የሚገኙት ከኢትዮጵያ 1ኛ ከአፍሪካ 4ተኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው የከፍታ መጠኑ 4620 ሜትር በሆነው በራስ ደጀን ተራራ ነው።ደጀን ተራራ በ1970 ዓ.ም.በዩኔስኮ አማካኝነት በአለም የቅርስ መዝገብ ላይ ተመዝግቧል።
4.ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ የተማረው ከአማራ ካህን ዮቶር (ራጉኤል) ነው።ልጁንም ሲጳራ አግብቶ አልአዛር እና ጌርሣም የሚባሉ ልጆችንም ወልደዋል። መሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ያረፈው በጥንቱ በጌምድር ግዛት ምድያም ነው። ምድያም በዛሬው አማራ ሳይንት ውስጥ መደጊም ተብሎ የሚጠራው ቦታ ነው።
በግ ማርባት በምድያም (በቤጌምድር) ምድር የተለመደ ነው።የአማራ ክፍል የሆነው በጌምድርም የበግ ሀገር የተባለው በግ በማርባት ስለሚታወቅ ነው።በጌምድር ወይንም ሽሜ የአማራ ሀገር ነበር።እስከ ተድባባ ማርያም ድረስ በጌምድር ይባል ነበር።በታሪከ ነገሥት "ወዘዐምሐራ ወዘበጌምድር"ይለዋል።ምድያም የሚባል ቦታ በጂዎግራፊያዊ ማስረጃዎች በሲና ሰርጥ ደቡባዊ ክፍል ይገኛል።ይኼም አካባቢ በሲና ተራራ አጠገብ በመሆኑ ግመል እንጅ በግ ሊያረባ አይችልም።
5.የሌዋዊያን ካህናት ከእስራኤል በመጀመሪያው ፓትርያርክ አዛሪያስ መሪነት የመዝሙረኛው ዳዊት የወንድም ልጅ ሳቤቅ ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ ታቦተ ጽዮንን ተከትለው ከመጡት አስራ ሁለት ሺህ ነገደ እስራል ሁለት ሺህ አመስት መቶዎቹ ተከዜን ተሻግረው ወደ አምሐራ ሳይንት መጡ።ሊቀ ካህን አዛርያስ በጣና ቂርቆስ ሊቀካህን በመሆን መንፈሳ አገልግሎት ሰጥተዋል።ዛሬም ድረስ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለውና ከአናቱ ላይ እንደ ሙቀጫ የተቦረቦረው ድንጋይ ለዚህ ህያው ማሳያ ነው።የኦሪታውያን የብረት መስዋዕት ማቃጠያም ይገኛል።
6.የጣና ቂርቆስ ገዳም ለሙሴ የተሰጠው የቃል ኪዳን ታቦቱ 800 ዓመት ቆይታበታለች።እንደገና ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ ወደ ምድረ ግብጽ በተሰደደችበት ወቅት ለ3 ወራት ከ10 ቀን በዚሁ ገዳም ከልጇ ጋር ቆይተውበታል።ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ “ፀአና በደመና” በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሀይቁ መጠሪያ ስም