ሰባቱ ቀለማት......#share
*ስለ ሰባት ቁጥር በተከታታይ ክፍል ብዙ ጽፈናል።ወደ 4.5 ሚሊዮን ሰው አንብቦታል።ነገርግን ስለ ሰባቱ ቀለማት አልጻፍንም ነበረና እነሆኝ።
*ኖኅ ሐመር በተሰኘችው መርከብ እግዚአብሔር ማየ አይኅን ከማዘዙ በፊት 500ኛ አመት ላይ ሳለ የወለዳቸውን ልጆችን ሴም፣ካምና ያፌትን፣ሚስቱን አይከልን ጨምሮ ከእንስሳት፣ከአዋፋት በየወገናቸው ተባትና እንስት ንጹህ ከሆኑትም ካልሆኑትም ለምድር ዘር ይቀር ዘንድ ወደ መርከብቱ አስገባ።
*ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ፦"7" ተባትና "7" እንስት፤
*ከንጹሕ የሰማይ ወፍ "7" ተባትና "7" እንስት
ወደ ሐመር አስገባ።እነኚህ "7" ንጽሕ እንስሳዎች በዓለም ላይ የማይገኙ ነገርግን አሁን ዝርያቸው በአለም ቅርስነት በ978 ዓ.ም.በተመዘገበው በኢትዮጵያ አንደኛው በአፍሪካ አራተኛው ከፍተኛ ተራራ በሆነው ደጀን ተራራ ይገኛሉ።እነርሱም ዋሊያ፣ቀይ ቀበሮ፣ጭላዳ ዝንጀሮ፣ቆርኪ እንዲሁም ሌሎች የአዋፍ ዝርያዎች ነበሩ።
*ኖኅ እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘውን ሁሉ አድርጎ በ600ኛ አመቱ ሐመርን ሰርቶ ባጠናቀቀ በ"7"ኛው አመት በ2ኛው ወር በ16ኛው ቀን ከመርከቧ ገባ።ከ"7" ቀን በኋላም የጥፋት ውኃ በምድር ላይ ሆነ።
*የታላቁ ቀላይ ምንጮች በ"7" ስቁረት ተነደሉ፣ የሰማይም መስኮቶችም ተከፈቱ፤ ከላይ ዝናብ ከታች ምንጮች አንድላይ ወጥተው ያለማቋረጥ ለ40 ቀን እና ለ40 ሌሊት መዝነብ ጀመረ።ጎርፉም ከተራሮቹ በላይ 15 ክንድ ከፍ አለ።ከሰማይ በታች ያሉ ረዣዥም ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ።በምድር ላይ የነበረው ሕይወት ያለው እስትንፋስ ሁሉ ተደመሰሰ።ለ150 ቀናቶችም ምድር ባህር ሆነች።መርከቢቱም በውኃ ላይ ተንሳፍፋ ዋለለች።ሐመርም ዝናቡ በጀመረ በ"7"ኛው ወር ከወሩም በ"27"ኛው ቀን ከጣና 15 ክንድ ከፍታ ባለው አራራት ተራራ ላይ አረፈች።
*ውሐው ከአስርኛው ወር በኋላ መጎደል ጀመረ።በ11ኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያ ቀን የተራሮቹ ራሶች ተገለጡ።ኖህ ከአርባ ቀን በኋላ የሐመርን መስኮት ከፈተ።ውሐው ጎድሎ እንደሆነ ያረጋግጥ ዘንድ ቁራን ላከው።ቁራ ግን ተመልሶ ሳይመጣ የውሐ ሽታ ሆኖ በዛው ቀልጦ ቀረ።ኖህ እንደገና ነጭ ርግብን ላካት።ርግቧም ለእግሯ ማሳረፊያ ቦታ በማጣቷ ተመልሳ መጣች።ከዚያም በኋላ ደግሞ በ"7"ኛው ቀን ላካት።ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች፤በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር።ኖኅም ከምድር ላይ ውኃው እንደጎደለ አወቀ።ደግሞ "7" ቀን ቆይቶ ርግብን ላካት ዳግመኛም ወደ እርሱ አልተመለሰችም።
ልብ በሉ...ስለ "7" ቁጥር ነው እያወራን ያለነው
1.ኖኅ ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ "7" ተባት ወደ ሐመር አስገባ
2.ኖኅ ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ "7" እንስት ወደ ሐመር አስገባ
3.ኖኅ ከንጹሕ የሰማይ ወፍ "7" ተባት ወደ ሐመር አስገባ
4.ኖኅ ከንጹሕ የሰማይ ወፍ "7" እንስት ወደ ሐመር አስገባ
5.ኖኅ መርከቧን ያጠናቀቀው በ"7"ኛው አመት ነው።
6.ኖኅ ከመርከቧ ከገባ በኋላ የጥፋት ውኃው መዝነብ የጀመረው በ "7"ኛው ቀን ነው።
7.የታላቁ ቀላይ ምንጮች በ"7" ስቁረት ነው የተነደሉት።
8.ሐመርም ዝናቡ በጀመረ በ"7"ኛው ወር ነው ከጣና 15 ክንድ ከፍታ ባለው አራራት ተራራ ላይ ያረፍችው።
9.ኖኅ ዳግመኛ ርግቧን የላካት በ"7"ኛው ቀን ነው።ወደ ማታ ስትመለስ በአፍዋም የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበረ።
10.ኖኅም ከምድር ላይ ውኃው እንደጎደለ አወቀ።ደግሞ "7" ቀን ቆይቶ ርግብን ላካት ዳግመኛም ወደ እርሱ አልተመለሰችም።
*የሐምሌ እና የነሐሴ ጉም ተገፎ፥ማየ ውኀ ጎድሎ በሁለተኛው ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን ምድር ጠፈፍ አለች።ወንዙም እየጠራ ኩል መሰለ።ሜዳው፣ ጋራው፣ ሸንተረሩ ወርቃማ የአደይ አበባ ካባ ለበሰ፡፡በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ክረምቱ አለፈ ሲባል በመስከረም ወር ዝናብ ቆሞ ፀሐይ የምትወጣበት፥ወንዞች ኩል ውሃ የሚያጎርፉበት፥አፍላጋት የሚመነጩበት፣ አዝርዕት ማለት የተዘሩት አድገው ማሸት የሚጀምሩበት፣ሜዳዎችና ተራራዎች ሸለቆዎችም በአበባ የሚያሸበርቁበትና የሚቆጠቆጡበት ጊዜ ማለት ነው፡፡እንዲሁም የጨለማ የችግርና የአፀባ ጊዜ የሚያበቃበት የብርሃን፣ የደስታ የሸት፣ የፍሬና የጥጋብ ጊዜ የሚጀምርበትና የሚተካበት ነው።
*መስከረም ሲጠባ፣ጮራ ስትወጣ ልጃገረዶች
ፀአዳ ልብሳቸውን ለብሰው፣ አሽንክታባቸውን አጥልቀው፣ሳዱላቸውን አሳምረው፣አደስ ተቀብተው፣እንሶስላ ሞቀው፣የቆረጡትን እንግጫ፣ሶሪትና አደይ አበባ ይዘው "አበባዬ ሆይ -ለምለም፣ኢዮሃ አበባዬ - መስከረም ጠባዬ"እያሉ የወርሀ መስከረም ብሩህ ተስፋና ስሜት በምድሪቱ የሚያስተጋቡበት ጊዜ ነው። በተለይ በሰሜን ሸዋ፣ በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በአዲስ ዓመት ዋዜማ ያላገቡ ልጃገረዶች እንግጫ በመንቀል የሚያከብሩት በአል ነው
*እንደገና ነሐሴ 13 ቀን የሚከበረው የደብረ ታቦር ወይንም ቡሄ! በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ተራራ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን ምክንያት አድርጎ በአገራችን የክረምቱ ጊዜ አልፎ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በቡሄ በዓል በመሆኑ ልጆች ጅራፋቸውን እዬጮሁ ያከብሩታል። ቡሄ ማለት ገላጣ፤የተገለጠ ማለት ነውና!!
* በየአመቱ ነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ የሚከበረው
በትግራይ አሸንዳ፣ በሰቆጣ ሻደይ፣ በላሊበላ አሸንድዬ፣ በቆቦ ሶለል በአል የክረምቱ ጨለማው፣ ዶፉና ብርዱ አልፎ የብርሃኑ ጊዜ መምጣትን፣የወንዙ ጥራትና የአበባው ማበብን ተከትሎ የአዲሱ አመት መድረሱን የሚያበስሩ የደውል ድምጾች ናቸው።የሰቆጣ፣የላሊበላ ልጃገረዶች ጋሜ፣ ቁንጮ፣ ግልብጭ፣ ሳዱላና ቅርድድ ተሠርተው በሕንቆ፣ አልቦ፣ ድሪ፣ ድኮት፣ ጉትቻ፣ ማርዳ፣ መስቀል አጊጠው በመልጉም /ጥልፍ ቀሚስ/፣ ሹፎን፣ ጃርሲ ለብሰው የአሸንዳ ቅጠል አሸርጠው አደባባይ በመውጣት ያከብሩታል።
*ኖኅ በ601ኛ አመቱ ምድር ስትደርቅ(መስከረም ሲጠባ፤አዳይ ሲፈነዳ) ከሐመር ውስጥ ያሉትን ሚስቱንና ልጆችን፣የልጆችንም ሚስቶች፣አብረዎት የነበሩትን አራዊት፣ወፎችንና እንስሶችን፣በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይዞ ወጣ።ኖኅም ይሄን ለአደረገ እግዚአብሔር መሠውያ ሠርቶ በአራራት ተራራ ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።የፍየል ጠቦት፣ላም፣የበግ አውራ፣ጨው፣ርግብና ዋኖስ ሰውቶ በደሙ የምድርን ኀጢአት ሁሉ ተሰረየ።እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሽትቶ ምድርን ዳግመኛ በማየ ውኃ እንደማያጠፋት ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ገባለት።የቃልኪዳኑም ምልክት(ቀስት) ደመና በታየች ጊዜ ትገለጣለች።እቺ ቀስተ ደመና "7" ምልክቶች አሏት።እነርሱም፦
1. ቀይ፣
2.ብርቱካናማ፣
3.ቢጫ፣
4.አረንጓዴ፣
5.ሰማያዊ፣
6.ወይን ጠጅ እና
7.ፈዛዛ ወይን ጠጅ ናቸው።
*እነዚህ ቀለማት የየራሳቸው ትልቅ የሆነ ትርጓሜ አላቸው።ትርጓሜውን በሌላ ቀን በሰፊ ጥናት የምዘረዝራቸው ይሆናል።ቀለማቱ በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ከሰውም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ለዘለዓለም ትውልድ የተደረገ ቃልኪዳን ነው።የቃልኪዳኑም ቀስት በምድር ላይ ደመና በሆነ ጊዜ ይታያል።እነዚህ የቃልኪዳን ምልክቶች ወይንም ሰባቱ ቀለማት በፀኃይ እና በዝናብ መሃል ብቅ ብለው፣ ቀስተደመና ሆነው ሰማይን በአንድ አይነት አሰላለፍ ያደምቃሉ።
*አሰላለፋቸው መጀመሪያ ቀይ፣ ከዚያ ብርቱካንማ፣ ከዚያ ቢጫ፣ ቀጥሎ አረንጓዴ፣ ከዚያ ሰማያዊ ከዚያ ደግሞ ደማቅ እና ፈዛዛ ወይን ጠጅ፡፡ሁሉም ትዩዩና እኩል ናቸው።ቀይ ከብርቱካንማ አይበልጥም፡፡ ሰማያዊም ከነ ወይን ጠጅ፣