የብራና አሠራር........#share
*አባቶቻችን ጠቢባን ነበሩ።የፍየል ወይንም የበግ ቆዳ በውሃ ዘፍዝፈው/በርጥቡ ወጥረው፣ላጭተው አጽድተው እንዴት የተቀረጸ የጽሕፈት ወረቀት ያዘጋጁ እንደነበረ ያስገርማል።
በመጀመሪያ ቆዳው በውሃ ይርሳል፣ዳርና ዳሩ በቢላዋ ይበሳና በጭራ/ገመድ ወጥረው በመላጫ ድንጋይ ፀጉሩና ሥጋው ይራመማል/ይላጫል፤በድጋሚ ቆዳው በማፈፊያ/ቢላዋ በደንብ ይፀዳና በፀሐይ ይደርቃል።ለመያዝ እንዲያመች አጠር ብሎ በተሠራና ጫፉ ብራናውን እንዳይቀድ ዳርና ዳሩ ዘንበል ባለ መጥረቢያ ቆዳው ይላጭና በሥጋው በኩል ውሃ እየተጨመረበት ይራመማል፣በደንብ ፀድቶ ከደረቀ በሚጻፈው መጽሐፍ መጠን በጥንቃቄ እየተሠመረ መስመሩን ጠብቆ በቢላዋ ይቆረጥና በወስፌ ውግ ይሠራለታል።
ውግ ማለት ከአርእስቱ እስከ ህዳጉ ያሉት መስመሮች ጠባብና ሰፊ እንዳይሆኑ በብራናው ዳር ላይ በወስፌ የሚደረጉ ምልክቶች መጠሪያ ነው።በዚህ መልክ የተዘጋጀው ብራና በቀጭን ገመድ ይታሠርና ጥራዝ ይሆናል፤በኋላም ብራናው መድመጽ በሚባል ድንጋይ በደንብ ይለሰልስና ለጽሕፈት ሥራው የተዘጋጀ ይሆናል።
ለብራና መጽሐፍት የሚያገለግሉ ቀለማት ብዙውን ጊዜ ቀይና ጥቁር ናቸው።
ጥቁር ቀለም የተለያዩ ቅጠሎችን /የክትክታ ቅጠል፣የቀረጥ ቅጠል፣የቀርቀሀ ሽልፋፎት፣የኑግ ፍሬ፣የበግ ቀንድ፣የበሬ ሸኮና፣የብራና ፍቅፋቂ በአንድ ላይ ቀላቅሎ በማክሰልና የዳጉሳ ቅርጣን አሮጌ ፈጭቶ በማክሰልና በንጽሕ ዕቃ በማዋሀድ ማሸት ይህም ቀለሙ ውበት እንዲኖረው ያግዛል።ለ6 ወር ቢያንስ ለ3 ወር በሞቃታማ ስፍራ እያሹ ማስቀመጥና መያያዝና ስልባቦት ማውጣት ሲጀምር የግራር ሙጫ ቀቅሎ ከቀለሙ ጋር ማሸት ይህም ቀለሙ በቶሎ እንዳይለቅ ይረዳል።
ለቀዩ ቀለም ደግሞ የእንጆሪ ፍሬ፣ቀይ አበባ፣እንሶስላ፣ቀይ አፈር...ለ1 ወር ከሙጫ ጋር በማሸት ቀላቅሎ ማዋሃድና ለጽሕፈት መጠቀም ይቻላል።
ለብራና ጽሑፍ የሚያገለግለው ብዕር በቀለሙ ቶሎ እንዳይደርስ ከጠንካራ ሸንበቆ/መቃ የሚዘጋጅ ሆኖ ጭስ ባለበት ቦታ እንዲደርቅ ከተደረገ በኋላ አንጓው እየተከፈለ ለጉልህና ለረቂቅ ጽሕፈት መጻፊያ እንዲያመች ተደርጎ በተለያየ ቅርጽ ይቀርጻል።
ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ ደግሞ በቁም ጽሕፈት በተባለው የአጻጻፍ ዘዴ ይጻፋል።የብራናው ሁሉም አቅጣጫዎች የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፦
ሀ.አምድ፦ጽሑፍ የሚያርፍበት የብራናው ክፍል
ሁ.ሐውልት፦ጽሑፍን በገፅ እኩል ለሁለት የሚከፍል መስመር ነው
ሂ.ምስማክ፦ጥራዝ በሚጠረዝበት በኩል የሚገኘው ባዶ ቦታ
ሃ.አርእስት፦በመጽሐፉ አናት የሚገኝ ባዶ ቦታ
ሄ.ግሌት፦ከጥራዙ ትይዩ የሚገኝ ባዶ ቦታ
ህ.ህዳግ፦ለእጅ መያዣ የተተወ ባዶ ቦታ ማለት ሲሆን እነዚህ ባዶ ቦታዎች በአግባቡ መተዋቸው ጽሑፍ በእጅ እድፍና በቀላሉ ለእሳት ቃጠሎ እንዳይጎዳ ለማድረግ ነው።
*በመጨረሻም መጻሕፍቱ ይደጎሳል።ሲደጎስ በመጀመሪያ የመጻሕፍቱ ሽፋንና የቆዳው መሸፈኛ ሙቅ ተቀብቶ በጨርቅ እየታሸ እንዲጣበቅ ይደረጋል፤አንድ ቀን ካደረ በኋላ በማግሥቱ በማስመሪያ እየተለካና በእሳት እንዳይቃጠል ሆኖ የተለያዩ ቅርፅ ባላቸው መደጉሶች ቅርፅ ይወጣለታል፤ቅርፅ ማውጫ መደጉሶቹ 12 ናቸው።
1.መድጎስ፣
2.መርገጫ፣
3.መሳቢያ፣
4.ዓይነርግብ፣
5.የውሃእናት፣
6.ቀርነበግዕ፣
7.ባለዘንባባ፣
8.ባለገመድ፣
9.ፍየልፈለግ፣
10.ትፍትፍ፣
11.ጥምዝ፣
12.? ስያሜውን ማግኘት አልተቻለም!
ይኼን የአባቶቻችን ድንቅ ሥራ #share