ታላቁ ነገድ የአማራ ሕዝብ ባህልና ቋንቋ....#share ሼር
*የአማራን ባህል ልዩ የሚያደርገው በታሪክ መረጃ ላይ የተመሠረተ፣የባህል ገጽታውን፣እሳቤውንና ጥበቡን ለሌላው የሰጠ፣አማርኛን በአገሪቱ ውስጥ ሁነኛ የጋራ መግባቢያ ይሆን ዘንድ ያመቻቸ፣በተራዛሚው የአማራ ብሔር አባላት ነገድ-ዘለል ንቃተ ህሊና እና ጽኑ አገራዊ ብሔርተኛነት እንዲያዳብሩ ያስቻለ መሆኑ ነው።
*የአማራ ባህል ለኢትዮጵያ መንግሥት መፈጠር ለአገራዊ አንድነት መዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገና አሁንም በማድረግ ላይ ያለ ነው።
*የአማራ ሕዝብ ፍትህና ርትዕ መጓደልን የሚያንፀባርቁና አገዛዝ ላይ የተነገሩ የአመጽ ትንፋሾች በየዘመኑ እየተነሡ የሚወድቁ አገዛዞችና ሥርዓቶችን ይኮንናል።በጎ ገፅታዎችና የጀግኖችን ገድለ በስንኞች ያንፀባርቃል።
"ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ
በሬሳ ላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ። (ዘመነ ዮሐንስ)
እንግዲህ ለታቦት አልሰጥም ስለት
አዴት መድሃኒዓለም ነዶ አገኘሁት።
መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኽት በረከተ
የሴቱን አላውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ።
የዳኘው አሽከሮች ሁሉም ሎጋ ሎጋ
ሲሄዱ በፈረስ ሲመለሱ ባልጋ።
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ።
የአድዋን ስላሴ ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው። (ዘመነ ምኒልክ)
አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።
ተሰቀለ ቢሉኝ ዝናሩ ነው ብዬ
ተሰቀለ ቢሉኝ ዳዊቱ ነው ብዬ
ለካስ በላይ ኖሯል ታላቁ ሰውዬ።
ላጥቢያ ዳኛ ሙክት ለጭቃው ወጠጤ
እንዲህ ሆኜ ነው ወይ ባገር መቀመጤ (ቀ.ኃ.ስ)
እንዲህ ያለ ዘመን ዘመነ ጭላዳ
አርሶ ለርሻ ሰብል ወልዶ ለጦር ሜዳ (ደርግ)