Ethiopia Check


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


#FactCheck በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ላይ የሚታዩት የአፕል ምስሎች ከሌላ ሀገር የተወሰዱ ናቸው

ትናንት ምሽት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፌስቡክ እና ኤክስ (ትዊተር) አካውንቶች ላይ "የአፕል ግብርና ምርታማነታችን እድገት እያሳየ ነው" ከሚል ፅሁፍ ጋር የተለቀቁ ስድስት የአፕል ምስሎችን ተመልክተናል።

ይሁንና በምስሎቹ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው አሰሳ ሁሉም ፎቶዎች ከሌላ ሀገር የተወሰዱ እና ኢንተርኔት ላይም በፍለጋ የሚገኙ መሆናቸውን መመልከት ችሏል።

ለማሳያነት በምስሉ ላይ 1 እና 2 ተብለው የሚታዩት ምስሎች ከእነዚህ ድረ-ገፆች ላይ የተወሰዱ ናቸው:

ምስል 1: በአሜሪካን ሀገር የሚመረተውን 'ኮርትላንድ የአፕል ዛፍ' ያሳያል: https://onlineorchards.com/products/cortland-apple-tree-one-of-the-slowest-to-brown-after-slicing

ምስል 2: በላቲን አጠራሩ 'ማሉስ ሳፕ' የተባለ በአሜሪካ የሚገኝ የአፕል ምርትን ያሳያል: https://restoringeden.co/product/4-in-1-combination-apple-2/

ሌሎቹ ምስሎችም በተመሳሳይ ከእነዚህ ድረ-ገፆች የተወሰዱ ናቸው:

https://www.facebook.com/share/1BdVptkgPC/

https://www.pomonafruits.co.uk/fruit-nut-trees/apple-trees/dessert-apple-trees/apple-tree-spartan

https://www.alamy.com/sulen-apfel-malus-domestica-jucunda-image389956155.html

አፕል ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ በምስራቅ ጎጃም እና በጋሞ ዞን ባሉ አካባቢዎች እንደሚመረት የመረጃ ማጣርያ ዴስካችን ያሰባሰባቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ይሁንና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የተጋሩት ምስሎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የአፕል ምርትን እንደማያሳዩ እነዚህ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በርካታ ተከታታይ ያሏቸው ባለስልጣናት፣ ተቋማት፣ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚያጋሯቸው ፅሁፎች፣ ምስሎች፣ ቪድዮዎች እና ሌሎች መረጃዎች እውነትነታቸውን ቀድመው በማረጋገጥ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረግ ጥረትን ሊደግፉ ይገባል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

3.7k 0 29 9 143



#FactCheck ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያየ ቁስ ተገጥሞላት የተገኘችው ወፍ ምንድን ነች?

ከሰሞኑ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የተለያዩ መለያዎች (tags) እና የመከታተያ ቁስ (tracking device) የተገጠመላት አንድ ወፍ መገኘቷ በሚድያዎች ተዘግቧል።

በክልሉ ማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ፣ ጉሬ ቀበሌ ውስጥ የተገኘችው ወፍ ጀርባ ላይ የተገጠመው ቁስ የብዙዎች መነጋገርያ ሆኗል። ጉዳዩን በክልሉ ከሚገኘው የህዳሴ ግድብ ጋር ያገናኙት እንዳሉ ሁሉ የተሸከመችው ቁስ 'ምን ይሆን?' የሚል ጥያቄ ያጫረባቸውም አሉ።

ለዚህም ይመስላል በራሪ እንስሳዋ በፀጥታ አካላት ተይዛ ለተጨማሪ ምርመራ ለመከላከያ ሰራዊት ተሰጥታለች።

ወፏ ጀርባ ላይ 'ከተገኘች ulrik.lotberg@birdlife.se በሚል ኢሜይል አሳውቁን' የሚል መልዕክት ሲኖረው ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ዳሰሳ አድርጓል።

ዳሰሳው እንደሚጠቁመው በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወፎች ባደጉ አገራት ባሉ አንዳንድ የአእዋፍ ጥናት በሚያደርጉ ተቋማት ለምርምር ስራ የተለያዩ መከታተያዎች ተገጥመውላቸው ይለቀቃሉ።

እነዚህ መከታተያዎች የGPS መሳርያ፣ የመለያ ቀለበት ወይም የታተመ ፅሁፍ ሊሆን እንደሚችል እና ጥናቱን የሚያደርጉት ሳይንቲስቶች የአእዋፉን የጉዞ አቅጣጫ፣ የቁጥር ብዛት፣ የእድሜ ርዝመት እና የበረራ መስመር ለማወቅ ይጠቀሙባቸዋል።

በወፎቹ ላይ የሚታየው ቁጥር የእያንዳንዱ በራሪ እንስሳ መለያ ሲሆን የተገጠመው ቁስ ደግሞ ወፎቹ በእያንዳንዱ የአየር መለዋወጥ ግዜ በየት አቅጣጫ በኩል እንደሚበሩ እንደሚመዘግብ ጥናቶች ያሳያሉ።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገኘችውን ወፍ የለቀቀው በስዊድን ሀገር የሚገኘው BirdLife Sverige የተባለ ተቋም ሲሆን የአለም አቀፉ BirdLife International ድርጅት የስዊድን ቅርንጫፍ በመሆን እየሰራ ይገኛል።

እንዲህ አይነት አእዋፋት በኢትዮጵያ ሲከሰቱ የመጀመርያው አይደለም። የዛሬ አራት አመት ገደማ እንዲሁ አንድ አሞራ የተለያዩ ቀለበቶች ታስሮለት በኢትዮጵያ መገኘቱ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።

ፎቶ: ቱክቫክ

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck




#EthiopiaCheck ምስሎችን ለማጣራት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ሁለት መተግበሪያዎች እናስተዋውቃችሁ

መረጃዎችን እንዲሁም ምስሎችን ለማጣራት የሚረዱ የተለያዩ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ይገኛሉ። ከድረ- ገጾች እስከ ሞባይል መተግበሪያዎች ድረስ አይነታቸው ብዙ የሆኑ የመረጃ ማጣራትን ስራ የሚያቀሉ እና እውነተኝነታቸውን የሚያረጋግጡ መሳሪያዎች አሉ። ከእነሱም መካከል:

1.  ቲንአይ(TinEye):
ይህ መተግበሪያ ምስሎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ለማጣራት የሚጠቅመን ድረ-ገጽ ነው። የምንፈልገው ምስል ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ውሎ ከነበረ መቼ እና የት እንዲሁም በምን መልኩ ጥቅም ላይ እንደዋለ ያሳውቀናል። በዚህ መተግበርያ በፎቶሾፕ የተነካኩ ምስሎችንም ፈልጎ ማግኘት ይቻላል። ድረ-ገፁ www.tineye.com ሲሆን አጠቃቀሙ ደግሞ ድረ-ገጹ ላይ የምንፈልገውን ምስል ከኮምፒተር ወይም ከስልካችን ላይ መርጠን በማስገባት መፈለግ ነው። ያስገባነውን ምስል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ቲንአይ ከኢንተርኔ ላይ ከወሰዳቸው 45 ቢሊዮን ምስሎች ውስጥ ይፈለግለናል። ምስሉን እና ምስሉን የሚመስሉ በርካታ ውጤቶችን ያወጣል፣ ከወጡት ምስሎች ውስጥም የምንፈልገውን መርጠን ስንመለከት ከዚህ በፊት ይህ ምስል የት ጥቅም ላይ እንደዋለ ማየት እንችላለን። ምንም ውጤት ካልመጣ ደግሞ ምስሉ ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ አልዋለም ማለት ነው፣ ወይም ምስሉ የቲንአይ ክምችት ውስጥ የለም ማለት ነው። ይህን መሳሪያ በነጻ መጠቀም መቻሉ አንዱ ጥሩ ጎኑ ነው።

2.  ፎቶ ፎሬንዚክስ (Photo Forensics):
ይህ መተግበርያ የሚጠቅመን የአንድን ፎቶ በፎቶሾፕም ሆነ በሌላ መተግበሪያ አለመነካካቱን እና ከዋናው ፎቶ አለመቀየሩን ነው። አጠቃቀሙ ደግሞ ወደ www.fotoforensics.com ከገባን በሁዋላ በመጀመሪያው ገጽ ማረጋገጥ የምንፈለገውን ፎቶ የምናስገባበት ገጽ እናገኛለን። የምንፈልገውን ፎቶ ከኮምፒተራችን ወይም ከስልካችን መርጠን ካስገባን በሗላ ፈልጎ ሲጨርስ ፎቶው ተነካክቶ ከሆነ ምኑ ጋር እንደተነካካ ወይም እንደተቀየረ የሚያሳየን ፎቶ ይመጣል። ያስገባነው ፎቶ ላይ ወጥ የሆነ ቀለም ብቻ የምናይ ከሆነ ፎቶ እውነተኛ ፎቶ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን፣ አለበለዚያ ደሞ አንድ ቦታ ላይ በብዛት ለየት ያለ ቀለም ወይም ነጣ ያለ ቀለም አንድ ቦታ ላይ ተከማችቶ ካገኘን ያ ፎቶ መነካካቱን መረጋገጥ እንችላለን። ፎቶውም ከየት እንደመጣ(ከካሜራ ወይስ ከፎቶ ሾፕ) ማየት እንችላለን።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

7k 1 59 2 49



#FactCheck 'ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት አበድሮ ያልመለሰለት ገንዘብ 92.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ' በሚል እየተሰራጨ ያለው ዜና ከዘጠኝ አመት በፊት የተሰራ ዘገባ ነው

ሪፖርተር ጋዜጣ የዛሬ ዘጠኝ አመት ገደማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለፌዴራል መንግሥት በጀት መሸፈኛ ካበደረው ገንዘብ ውስጥ ያልተመለሰለት 92.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ዘግቦ ነበር።

ጋዜጣው በዘገባው ላይ ባንኩ በቀጥታ ለማዕከላዊ መንግሥት አበድሮ ያልተመለሰለት ገንዘብ 83.2 ቢሊዮን ብር ወይም 90.3 በመቶ ሲሆን፣ ቀሪው 9.7 በመቶ ደግሞ በቦንድ ተበድሮ ያልተመለሰለት መሆኑን ጠቅሶ ነበር።

ይሁንና ይህ የሪፖርተር ዘገባ የታተመበት ጋዜጣ የስክሪን ቅጂ (ስክሪንሾት) ከሰሞኑ በስፋት እየተጋራ ሲሆን መረጃው አዲስ እንደሆነ ተደርጎ እየቀረበ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

ይሁንና መረጃው አዲስ ሳይሆን እ.አ.አ በፌብሪዋሪ 21/2016 የወጣ ዜና መሆኑን ማየት ችለናል።

ላለፉት 16 ዓመታት ያለገደብ ከብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ሲበደር የነበረው የፌደራል መንግሥት ከአገር ውስጥ ገቢ ከ15 በመቶ የበለጠ ገንዘብ በብድር ማግኘት እንዳይችል የሚገድብ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከወራት በፊት መቅረቡ ይታወሳል።

ለምክር ቤቱ የቀረበው የብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ መንግሥት የተበደረውን ገንዘብ በአንድ ዓመት ውስጥ ካልመለሰ ከተቋሙ ሌላ ብድር መውሰድ እንደማይችልም ያስቀመጠ ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


#FakeNewsAlert ፖፕ ፍራንሲስ ህይወታቸው እንዳለፈ ብሄራዊ ቴሌቭዥኑን ጨምሮ በአንዳንድ ሚድያዎች የተላለፈው ሀሰተኛ መረጃ እንዴት ተከሰተ?

"የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል" በማለት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከጥቂት ሰአታት በፊት ያሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነበር።

ጣብያው ለምንጭነት የአለም አቀፉን የዜና ወኪል አሶሲየትድ ፕረስ (AP) በምንጭነት ዋቢ ቢያደርግም "Pope Francis rested during a peaceful night following respiratory crisis" ከሚለው አርዕስት ውስጥ 'rested' ወይም 'እረፍት አደረጉ' የሚለውን 'ህይወታቸው አለፈ' የሚል ትርጓሜ ሰጥቶት እንደነበር ኢትዮጵያ ቼክ ያደረገው ዳሰሳ እና ማጣራት ያሳያል።

በተመሳሳይ ድሬ ትዩብ የኢቢሲን ዘገባ ሳይጠቅስ ሊቀ ጳጳሱ እንዳረፉ አለም "አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡት ይገኛሉ" በማለት የተሳሳተ መረጃ አቅርቦ ነበር።

አሁን ላይ ሁለቱም ሚድያዎች ዜናዎቻቸውን አንስተዋል።

ኢቢቢ በሊቃነ ጳጳሱ ዙርያ የተሳሳተ ዜና ሰርቷል በማለት የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያስታወቀች ሲሆን "እንደውም ዛሬ ከበፊት ቀናት በተሻለ ሁኔታ ሰላማዊ እንቅልፍ ተኝተው ነው ያደሩት" በማለት ገልፃለች።

ፖፕ ፍራንሲስ የመተንፈሻ አካላቸው ላይ ጠንካራ ህመም ተከስቶባቸው ሆስፒታል ገብተው እንደሚገኙ አለም አቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።

ሚድያዎች ሰበር ዜናዎችን ለማጋራት በሚጣደፉበት ግዜ እንዲህ አይነት የትርጉም እና የይዘት ግድፈት ሊያጋጥማቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ኢትዮጵያ ቼክ ለማሳሰብ ይወዳል።

ኢትዮጵያ ቼክ!

@EthiopiaCheck

9.8k 0 32 13 92

#MondayMessage ዜጋታት ሓበሬታ ናይ ምርካብ መሰሎም ንምርግጋጽ እጃም መንግስቲ እንታይ ክኸውን ኣለዎ?

ኮምፒዩተራትን ሞባይል ስልኪታትን ምምዕባል ካብ ዝጅምራሉ ግዜ ኣትሒዙ ክሳብ እቲ ኢንተርነት ዝዓበየሉ ግዜ ቅርፅን ዋሕዝን ሓበሬታ እናተቐየረ መጺኡ ኣሎ።

እዚ ክፍለ ዘመን ድማ ብዓብይኡ ብርክት ዝበሉ ቴክኖሎጂካዊ ምዕባለታትን ዋሕዚ ሓበሬታን ዝርኣየሉ ዘሎ ብምዃኑ ናይ ሓበሬታ ዘመን ተባሂሉ’ዩ ዝጽዋዕ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/the-right-to-access-information-and-the-responsibility-of-a-government-%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. ቴሌግራም የህጻናት ወሲብ ብዝበዛን የሚያሳዩ ይዘቶችን ከፕላትፎርሙ ለማጽዳት ከኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን ጋር ስምምነት ማድረጉን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን የህጻናት ወሲብ ብዝበዛን የሚያሳዩ ይዘቶችን ከኢንተርኔት በማስቀገድ ረገድ ብዙ ቀዳሚ ተቋም መሆኑ ይነገራል። በስምምነቱም ቴሌግራም ይዘቶቹን ቀድሞ ለመለየትና ለማስወገድ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችንና ልምዶችን ያገኛል ተብሏል። ከዚህ ጋር በተገናኘ ሸጋ የተባለ የድረገጽ ሚዲያ ከቀናት በፊት ባስነበበው የምርመራ ዘገባ የኢትዮጵያውያን ሴቶችን እርቃን ምስሎች የሚያሳዩ ይዘቶች በቴሌግራም በስፋት እንደሚሰራጩ ያሳየ ሲሆን ጉዳዩ ባለፉት ቀናት የቲክቶክ መንደር ዋና መነጋገሪ መሆኑ ይታወቃል።

2. በሰውሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች እስካሁን የስርጭት መጠናቸው አነስተኛ መሆኑን ሜታ በትናትናው ዕለት አስታውቋል። በፈረንጆቹ 2024 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ በተደረጉ ምርጫዎችን በተመለከተ በፕላትፎርሞቹ ከተሰራጩ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችም በሰውሰራሽ አስተውሎት የተሰሩት ድርሻ ከ1% በታች መሆኑን ገልጿል። ይዘቶቹን ለመለየትና ለማስወገድም እንዳልከበደው አብራርቷል።

3. ሜታ በሙከራ ደረጃ ያስጀመረውን ቅጣትን በትምህርት የመቀየር አሰራር ለሁሉም የፌስቡክና የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ማስፋቱን በትናትናው ዕለት አስታውቋል። አሰራሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖሊሲ ጥሰት ፈጽመው የአካውንት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተጠቃሚዎች አጭር ትምህርታዊ ፕሮግራም በመከታተል ቅጣታቸውን እንዲሰረዝላቸው የሚያደርግ ነው። ሆኖም አሰራሩ ተደጋጋሚ ወይም ከባድ የፖሊሲ ጥሰት የሚፈጽሙትን አይመለከትም ተብሏል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች:

-ቆየት ያሉ ልጥፎችን ለማሰስ የሚረዳ መገልገያን በአፋን ኦሮሞ አስተዋውቀናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2522

-የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን የግዙፍ ኤርፖርት ፕሮጀክትን ያሳያሉ ተብለው የተጋሩ ምስሎችን አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2524

-የሴራ ትንታኔን መሰረት አድርገው ስለሚሰራጩ ሀሠተኛ መረጃዎች በትግርኛ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2525

ኢትዮጵያ ቼክ




#Explainer ግጉይን ጭብጢ ዘይብሉን ሓበሬታ መን’ዩ ናብ ብዙሓት ክባጻሕ ዝገብር?

ኣብዚ እዋን፡ ብርክት ዝበሉ ሰባት ብዝተፈላለዩ መድረኻት ማሕበራዊ ሚዲያ ዝቐርቡ ትሕዝቶታት ከም ዝከታተሉ ይገልፁ።

መዓልታዊ ፌስቡክ ወይ ካልኦት ኣማራጺታት ብምጥቃም ድማ ሓገዝቲ’ዮም ዝብሉዎም ሓበሬታት ከም ዝረኽቡን ብስሩዕ ማዕከናት ሓበሬታ ዝቐርቡ ዜናታት ምክትታል ከም ዝገደፉዎ ይዛረቡ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/the-role-of-conspiracy-theory-in-misinformation-%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/


#FactCheck እነዚህ ምስሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን የግዙፍ ኤርፖርት ፕሮጀክትን ንድፍ አያሳዩም

ከሰሞኑ በርከት ያሉ የፌስቡክ እና ኤክስ (ትዊተር) ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚያስገነባውን ሜጋ ኤርፖርት ፕሮጀክት ያሳያሉ ያሏቸውን ምስሎች እያጋሩ ይገኛሉ።

ለምሳሌም ‘FastMereja.com’ የሚል ስም ያለው እና ከ860 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ” ሲል በስክሪን ቅጂው የሚታዩትን ሶስት ምስሎች አጋርቷል።

ይህን የፋስት መረጃ ልጥፍም ከ40 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው አጋርተውታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምስልን በምልሰት መፈለጊያን በመጠቀም በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት በስክሪን ቅጂው የታችኛው ክፍል የሚታዩት ሁለት የኤርፖርት ንድፎች በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የኢንቾን ኤርፖርት ንድፍ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችሏል።

የኢንቾን ኤርፖርት ንድፎች በተለያዩ ጊዝያት ሲጋሩ የቆዩ ሲሆን ከንድፎቹ የተወሰኑትን በነዚህ ማስፈንጠሪያዎች መመልከት ይቻላል፡ https://www.gensler.com/projects/incheon-international-airport እና https://www.koreaherald.com/view.php?ud=20191119000078

በሌላ በኩል በስክሪን ቅጂው የላይኛው ክፍል የሚገኘው ምስል ‘GSAAN’ በተሰኘ ድረ-ገጽ የተጋራ ሲሆን ተቋሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚገነባው ሜጋ ኤርፖርት የቅድም ዲዛይን እና ማስተር ፕላን ጽንሰ-ሐሳብ አገልግሎት መስጠቱን ጠቅሷል፡https://www.gsaan.us/ethiopia-new-airport-logistics-industry-park-project-study-report/

ይሁን እንጂ ‘GSAAN’ ድረ-ገጽ ላይ የተጋራውን ንድፍ ከሌላ ምንጮች ማረጋገጥ አልቻልንም። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚያስገነባው ሜጋ ኤርፖርት ከዳር አል ሀንዳሽ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ጋር የቴክኒካል፣ የአርክቴክቸር፣ የኢንጅነሪንግ እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ስምምነት መፈራረሙን ባለፈው ነሐሴ 2016 በድረ-ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቆ ነበር፡ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-signs-a-contract-with-dar-al-handasah-to-develop-a-mega-airport-city

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ በዳር አል ሀንዳሽ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ይፋ የሆነ የሜጋ ኤርፖርቱ ንድፍ እንደሌለ ተመልክተናል።

በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገነባ የተነገረው ሜጋ ኤርፖርት በአመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck






የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1.ተጽእኖ ፈጣሪ ናይጄሪያውያን አርቲስቶችን ያካተተ ጥምረት በሀሠተኛና በተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ዙሪያ ንቃት ለመፍጠር ያለመ እንቅስቃሴ መጀመሩን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ጥምረቱ ናይጄሪያውያን ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች መለየት እንዲችሉ ትምህርታዊ ንቅናቄዎችን ያደርጋል የተባለ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎችንም ተጠያቂ የማድረግ ትልም እንዳለው ተገልጿል። ጥምረቱ #FWDWithFacts የሚል ሃሽታግ ይጠቀማል ተብሏል።

2. የአውስትራሊያ ፓርላማ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ህግ በዛሬው ዕለት ማጽደቁን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ታዳጊዎችን ከማህበራዊ ሚዲያ “ጉዳት” ለመጠበቅ ያለመ ነው የተባለው ህግ ተፈጻሚነቱ ከ12 ወራት በኋላ ይጀምራል ተብሏል። ህጉን የሚተላለፉ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እስከ 32.5 ሚሊዮን ዶላር እንደሚቀጡም ተደንግጓል።

3.በስሩ ከ320,000 በላይ ጋዜጠኞችን ያቀፈው የአውሮፓ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ከመጭው የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያ ወር መጨረሻ ጀምሮ ኤክስ/ትዊተር የተባለውን የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም እንደሚያቆም አስታውቋል። ፌደሬሽኑ የማህበራዊ ሚዲያውን ባለቤት በፀረ-መደበኛ ሚዲያነት የከሰሰ ሲሆን ኤክስ “የሴራ ተንታኞች፣ የዘረኞችና የአክራሪ ቀኝ ዘመሞች” መናህሪያ ሆኗል ሲል ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። በቅርቡ ዘጋርዲያን ጋዜጣን ጨምሮ በርከት ያሉ ተቋማትና ግለሰቦች ተመሳሳይ ምክን ያት በመጥቀስ ኤክስን መጠቀም ለማቆም መወሰናቸውን ማስታወቃቸው ይታወቃል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች

-የሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክቶችን ስርጭት ለመቀነስ ጋዜጠኞች ምን ማድረግ ይችላሉ፧ የሚል መልዕክት አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2515

-ወቅታዊ መረጃዎችን በምንከታተልበት ወቅት ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ የሚያስረዳ ጽሁፍ በትግረኛ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2516

-ድምጽ ማቸገን ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለ? ለሚሉት ጥያቄወች ምላሽ የሚሰጥ ማብራሪያ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/2517

-እንዲሁም ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል? ለሚሉት ጥያቄወች ምላሽ የሚሰጥ ማብራሪያም አጋርተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck




#Explainer ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል?

የአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከ3.4 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎችን ማስተናገዱን እና በዚህም ከ2.41 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በትናንትናው ዕለት አስነብቦ ነበር። ለመረጃውም በምንጭነት የክልሉን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጠቅሷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች ክልሎችም እንዲህ ያሉ ቁጥሮችን በየጊዜው ሲናገሩ ይደመጣል። ይህን የተመልከቱ ሰዎች ቁጥሮቹ መጋነናቸውን በመጥቀስ አስተያየታቸው ሲሰጡ የሚታይ ሲሆን ለኢትዮጵያ ቼክም የአጣሩልን ጥያቄዎች ይመጣሉ።

- ለመሆኑ ጎብኝ ሲባል ማንን ያካትታል? ከጎብኝዎች የተገኘ ገቢስ እንዴት ይሰላል?

የተመድ የዓለም ቱሪስም ድርጅት (UNWTO) የቃላት መፍቻ ጎብኝ ወይም ዕንግዳ (visitor) ከአንድ አካባቢ ወደሌላ አካባቢ የሚጓዝ፤ በሄደበት አዲስ አካባቢ ከአንድ ዓመት በላይ የማይቆይ፤ ጉዞውም ከቅጥር ውጭ ለንግድ፣ ለጉብኝት፣ ለግል ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ይዘረዝራል።

ተጓዡ በሄደበት አካባቢ ከአንድ ቀን በላይ ከቆየ ቱሪስት (tourist) ሊባል እንደሚችል የሚበይነው ድርጅቱ ከአንድ ቀን በታች ወይም በደርሶ መልስ ወደመኖሪያቸው የሚመለሱትን ሽርሽር አድራጊዎች (same-day visitor or excursionist) ይላቸዋል። ጎብኝ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተጓዦችን ያጠቃልላል።

ከጎብኝዎች የሚገኝ ገቢ ደግሞ ጎብኝው በአካባቢው በቆየበት ጊዜ  ለምግብ፣ ለምኝታ፣ ለአስጎብኝ፣ ለትራንስፖርት፣ ለስጦታ ዕቃዎች መግዣ ወዘተ ያወጣል ተብሎ የሚገመተው ወጭ ላይ መሰረት እንደሚያደርግ  የዓለም ቱሪስም ድርጅት የቃላት መፍቻ ያስረዳል።

- የአማራ ክልልን በሩብ አመቱ የጎበኙት እነማናቸው? ገቢውስ ከምን ተገኘ?

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በሩብ አመቱ ክልሉን ጎበኙ ያላቸውን ዋና ዋና ተጓዦችን ዘርዝሯል። በቢሮው የቱሪዝም ልማት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ አዳም በግሸን ደብረ ከርቤ በዓል አከባበር ብቻ አንድ ሚሊየን ሃይማኖታዊ ጎብኝዎች ወደ አካባቢው መጓዛቸውን የገለጹ ሲሆን በሰሜን ሸዋ የሚገኙ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ መስህቦችን ለመጎብኘትም  በየሳምንቱ መጨረሻ የእረፍት ቀናት ከአዲስ አበባ በርካታ ጎብኚዎች እንደሚመለጡ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከነሐሴ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚከበሩት የሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል፣ የመስቀል፣ የግሸን ደብረ ከርቤ በዓላትና ሌሎች ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላትንም አስረድተዋል።

ከጎብኝዎቹ መካከልም 6,328 የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ከጎብኝዎች ተገኘ የተባለው ገቢ የተሰላው አንድ የውጭ ወይም የሀገር ውስጥ ጎብኝ  እንደ አካባቢው ሁኔታ በቀን ለመኝታ፣ ለምግብ፣ ለአስጎብኝ፣ ለጫማ ማስዋብና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያወጣው ታስቦ መሆኑ ቢሮው ባጋራው መረጃ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck




#Explainer ድምጽ ማቸገን (voice cloning) ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለን?

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች ፈጣንና የማያቋርጥ እድገት ለሰው ልጆች በርከት ያሉ ዕድሎችን ይዘው ስለመምጣታቸው በተደጋጋሚ ሰምተናል፣ በአንጻሩ ቀላል የማይባሉ ጉዳቶችን እያስከተሉ ስለመሆናቸውም አድምጠናል።

ለምሳሌም በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሚፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እና ጽሁፎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን በማባባስ ረገድ በመጫዎት ላይ ያሉትን አሉታዊ ሚና መጥቀስ ይቻላል።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/disinformation-threats-posed-by-voice-clones-and-how-to-combat-them/

Показано 20 последних публикаций.