እርር አልኩኝ÷
(ሀብቱ ግርማ)
ቦንጋ የሚባል የምድር ገነት ላይ ነበርኩኝ፡፡ ለአለም ፀሀይ÷ ለአለም ውሃ መሆን ከሚችሉ ሰዎች ጋር፡፡
ተፈጥሮው ደግሞ ልብን ፍስሀ ላይ ያደርሳል÷
ተፈጥሮ እና ሰው ሰምረው የሚኖሩበት ምድር!
ዛሬ አዲስ አበባ ተመለስኩ÷ ሰላምና ፍቅርን ሊታጠን ብቻ ነው ውስጤ ፍቃድ ያለው፡፡ ምንም ክፉ ነገር ለማየት፤ ለመስማት አቅም የለኝም፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ አታክታኛለች፡፡
ከዘነበወርቅ ወደ ቶታል በሚወስደው መንገድ÷ መንገዱ ዳር ሶስት ሰዎች ይታገላሉ፡፡ ሁለት ሰአት ተኩል ማለፉ ነው፡፡ አንዳቸው ሰውዬ ግራጫ ፀጉራቸው፣ የደከመ ሰውነታቸው በሁለት ወጠምሻ ወጣቶች ወደ መሬት ሲፈርጥ ነብሴ ከአካሌ ወጣች!
ጡንቻቸው በታቱ ያጌጠ፣ ደረታቸው አብጦ ትንንሽ ተራራሮችን በአካላቸው የሰሩት ወጣቶች ከሽማግሌው ኪስ ሲገቡ የራይድ ሹፌሩ መኪናው ከፊታቸው አበራ÷ ትዕይንት የምንቀርፅ ነው የምንመስለው፡፡ ዱብ እዳችን ነብስ ውጪ፤ ነብስ ግቢ ውስጥ ከተትን፡፡ ሁላችንም የምናደርገውን አናውቅም÷ ሽማግሌው መሬት ላይ እንደተዘረጉ ነው፡፡ እኛ መሮጥ ያዝን÷ አለክልከን ለብዙ ያዝናቸው፡፡
ሽማግሌውን የሰረቃቸው አንድ ተራ ኖኪያ ስልክ ነው፡፡ የግራጫ ፀጉር ተምሳሌት፣ የማህበረሰቡ ዋርካነት ክብርና፣ ፀጋቸው በምሽት ተገፎ አዛውንቱ በጣም አዘኑ÷ ሰፈሬ እኮ ነው አሉን፡፡
እንዲረጋጉ ሞከርን፡፡ እኔ ግን አረርኩኝ፡፡ ክፉ ለማየትም ለመስማትም የመጨረሻው ደረጃ ላይ ነኝ፡፡ የፈራሁት ደርሶ፤ በብረቱ አየሁኝ፡፡
ሀገሩ ግን ጠባቂ የለውምን!?
አሁንም እንባዬን ወደ ሰማይ አዘራለው÷ አዲስ አበባ ለሽማግሌዎቹ መጦሪያ ሀገር እንድትሆን÷ ወጣቶቹም የጉብዝና ወራታችን እንዲባረክ እለምናለሁ!