ለመሆኑ ልክ የዛሬ 83 አመት አዲስአበባ የማን ነበረች?
.
በግራዚያኒ ትእዛዝ ለሶስት ቀናት በቆየ አሰቃቂ ጭፍጨፋ በደም ጎርፍ ስትነከር … አስከሬን ለቁጥር ታክቶ በየመንገዱ ዳር ሲከመር … የማን ነበረች? ዛሬ “የእኔ ናት” “የእኛ ናት” የምንል ያኔ ቦንብ እና ጥይት የጦር መሳሪያው አልበቃ ብሎ ፤ በአካፋ ፣ በዶማ ፣ በመጥረቢያም ጭምር ... ገዳዩ እስኪደክመው ፤ እጁ እስኪዝል ሲጨፈጭፍ ፤ ጩኸት በርክቶ ፣ ሟች በዝቶ ፣ ባለጥቁር ሸሚዞች በአስከሬን ላይ እየተረማመዱ ህያዋንን ሲያፈራርሱ … ወንድ ከሴት ፣ ህፃን ከአዋቂ አልተለየም ነበር። ሶስት ቀንና ሶስት ለሊት ... ወደ ነነዌ ከተማ የተላከው ነብዩ ዮናስ በዓሳ ሆድ እንደቆየ ከተማይቱ የሲኦል ሆድ ሆነች። በአቅማቸው ሁሉ ... ባገኙት የመግደያ መሳሪያ ሁሉ ... እሳትም ሳይቀር በተዘጋ ቤት ውስጥ ለቀቀቁባቸው።
ምድር ቁና ሆነች። መግቢያ ጠፋ። ሮጠው የማያመልጡ፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ህፃናት ፤ ነፍሰጡር እናቶች እና አረጋውያን እንኳ ነፍሳቸውን ለማዳን መሸሸጊያ አልነበራቸውም። ቅንጣት አልራሩላቸውም ። ያኔ ኢትዮጵያዊ ሆኖ አዲስአበባ ከተማ ውስጥ መገኘት ብቻ ለመገደል በቂ ምክንያት ነበር፡፡ በ3ቱ ቀናት ጭፍጨፋ 30ሺህ ወገኖቻችን ተሰው። ከሞት የተረፉት በጅምላ እየተጋዙ ወደ በረሃ እስር ቤቶች ተወረወሩ። ተመልሰው ንብረት እዳያገኙ ፣ አንዳች እንዳይቀርላቸው የግራዚያኒ አሽከሮች "ይጠቅመናል" ያሉትን ሐብት ንብረታቸውን ዘረፉ። በእሱም ላይ የግድያ ሙከራ አድርገው ያመለጡት ወጣቶች ይገኙበታል ተብሎ የተጠረጠረው ደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሳት እና ዲያቆናት ሳይቀሩ ሲያነቡት በኖሩት መጽሐፍ እንደተፃፈው "... በመጋዝ ተሰነጠቁ ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ ፤ በእሳት ተለበለቡ ..." የግፍ ግድያውን ገፈት ቀመሱ ፡፡
ለመስማትም ለማየትም የሚዘገንን ጭፍጨፋ በሰው ልጆች ላይ ሆነ።
በኢትዮጵያውያን ላይ ሆነ።
በአዲስአበባውያን ላይ ሆነ።
ለመሆኑ ያኔ አዲስአበባ የማን ነበረች?
በጊዜው ብንኖር …. ማንኛችን እንሆን ከ3ሺህ ምንዱባኑ ተርታ 2 ማርትሬዛ እና ትርፍራፊ ምፅዋት ከግራዚያኒ እጅ ለመመፅወት የምንሰለፍ? ማንኛችን እንሆን ከ30ሺው ጋር የምንሰየፍ? ማንኛችን እንሆን ከሁለቱ አብረሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ኋላ ቅኝ አገዛዝን ተቃውመን ፣ በነፍሳችን ተወራርደን የምንሰለፍ? ማንኛችን እንሆን ባለመኪናው ስምኦን አደፍርስ ?
አይበለውና … ዛሬም የአዲስአበባ ከተማ ነዋሪ ያንን መሰል መከራ ለመቀበል ቢገደድ ፤ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ጭፍጨፋ ቢመጣ ዛሬ“የእኔ ናት” የሚለው ሁሉ ምን ይል ይሆን? ስንቱ ይሆን ዶሮ ሳይጮህ አዲስአበቤነቱን የሚክድ? 'አላውቃትም' የሚል? የአዲስአበባ ነዋሪነት መታወቂያ እየታየ ቢሆንስ ግድያው? ማን ይሆን በአዲስአበቤነቱ የሚፀና? በቤት ቁጥሩ ሲፈለግ የሚገኝ?
"አዲስ" -ንም "አበባ"- ንም አላውቅም የማይል? ማን ይሆን?
.
"መከራ ሳይመጣ ሁሉም ከተሜ ነው"
.
ይኼውልህ ወንድሜ ዛሬ ግራዚያኒ የለም (ከፋፍለህ ግዛ መርሁ ቀርቶ እንደሁ እንጂ )… ገነተ ልዑል ቤተ መንግስትም ዩኒቨርሲቲ ሆኗል …አካፋ እና ዶማውም ጊቢው ውስጥ ህንፃ ለመስራት እየተቆፈረበት ነው … የጀግኖች ወጣቶቹ አስከሬንም በቅድስት ስላሴ በክብር አርፏል… … ሰማእታቱም ፊት ለፊት ሐውልት ቆሞላቸዋል…ሆስፒታሉም በቀኑ ተሰይሞላቸዋል … እኔ እና አንተ እዚህ…ወይ ታሪክ አንሰራ ፤ ወይ ታሪክ አናውቅ ፤ ወይ ለልጃችን "ታሪኩ" ብለን ስም አናወጣ ፤ ወይ "የአዘቦት ተረክ" አንሰማ...ስንገርም!
እና አዲስአበባ የማን ነበረች አልከኝ?